የእኔ የዘመዴ ስጋትና ኑዛዜዬ ።
★ ★ ★ ★ ★
ጎበዝ አደጋ ላይ ነኝ ✔ የልጆቼን ነገር አደራ.! ገዳዮቼ ጀርመን ገብተዋል ፤ መረጃው ለጠበቃዬ ደርሷል ፣ ጉዳዩ በህግ ተይዟል ። ነገር ግን ምንም አይመጣም ፣ በእኔ በኩል ሁሉን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ። እናት ቤተከርስቲያን ፍርሃትን አላስተማረችኝም ። የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስን ገድሉን ሳነብ ስባረክበትም ኖሬ ደግሞ ልፍራ.!! ወጊድ በለው ።
✔Share ~ Share ~ Share ~ Comment✔
✔ልብ ብላችሁ ስሙኝ አድምጡኝም ። ስተፈልጉ ቅዠት ስትፈልጉም ትንቢት ብነው ብላችሁ አድምጡኝ ።
✔ በተለይ የትግራይ ልጆች ጆሮ ሰጥታችሁ ስሙኝ ።
✔ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳሳት የነበሩት ታላቁ የሃይማኖት ገበሬ ብፁዕ አቡነ ሰላማ በረከታቸው ይደርብንና ከታች የተናገሩት ቃለ ምዕዳን ሰምተን እንጠቀምበት ።
ውድ ኢትዮጵያውያን ይልቅ ከወራት በፊት ቀመር ተሠርቶለት የተጠናቀቀውን የአባ ኃይለማርያምንና የአባ ተክለሃይማኖትን በመንግሥት ትዕዛዝ ቀድሞ መመረጥ እያነሳን በከንቱ ጨጓራችን መላጡንና ጊዜ መፍጀቱን አቁመን ዳይ.! ዳይ.! ዳይ.! ወደ ቀጣዩ አጀንዳ በአስቸካይ እንግባ ።
ልብ በሉ ፈረንጆቹ መጀመሪያ እንዲህ አሁን ኢየሱስ ጌታ ነው የሚል ፉከራ በየአደባባዩ ሊያሰሙን እኛን እምነት የፋራ ነው ፣ እግዚአብሔር የሚባል ነገር የለም ፣ አሉንና እኛንም ፋራ አትሁኑ እግዚአብሔር የለም በሉ ብለው ሰበኩን ፣ ፍልስፍናቸውንም ጫኑብን ። አዳሜ እውነት መስሎን እግዚአብሔር የለም እንድንል አደረጉን ፤ ፓጋንም ሆነን እንደ እንስሳም መኖር ጀመርን ። ጾም ቀረ ፣ ጸሎትም ተረሳ ፣ ማስቀደስ ፣ ካህን ማክበርም ተተወ ፣ መስቀል ተናቀ ፣ ፀበል ተጠላ፣ መዕተብ ተበጠሰ ።
ቀጠሉና ኢትዮጵያውያን ሞትን የማይፈሩት ፣ ለሃገራቸው ሲሉ ባዶ እጃቸውን ሽመል ይዘው ሚሳኤል ከጫነ ሠራዊት ጋር ተዋግተው የሚያሸንፉት.?? ምን ቢሆኑ ነው.?? ብለው ተመራምረውና አጥንተው ሲያበቁ አስኳሉን አገኙት ። ይኸውም ምንድ ነው ያልን እንደሆነ ፤ ኢትዮጵያውያን ጀግና የሆኑት ፣ በእግዚአብሔር ማመናቸው ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን መመርመራቸው፣ ገድለ ጊዮርጊስን ፣ ገድለ መርቆሬዎስን ፣ ገድለ አቡነ አረጋዊን ፣ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ፣ ገድለ ክርስቶስ ሠምራን ፣ ገድለ እስጢፋኖስን በማንበባቸው ምክንያት የሰማዕታት ህይወት ስለተዋሃዳቸው ፤ ልምምዱም ስላላቸው ነው ሞትን የማይፈሩት የሚል ሆኖ አገኙት።
ከዚያማ ምን ይጠየቃል ትውልድ ፈጠሩ ፣ ገድል ከቤተክርስቲያን ይውጣ ፣ ድርሳን ምን ያደርጋል ፣ አዋልድ መጻህፍት ምን ይሠራሉ ፣ የሚሉ ትውልዶችን ፈጠሩ ። ይኸው ዛሬ ወጣቱ የዚህ ተንኮል ምርኮኛ ሆኖ የራሱ የሆነውን ጥሎ አናንቆና ሰድቦ አረፈው ። አሁን እድሉን አጥተው እንጂ እድሉን ቢያገኙ በአንድ ቀን ሁሉን ነገር ድምጥማጡን አውጥተው መጻህፍቱን በሙሉ አቃጥለው ቢጨርሱ እንዴት ደስተኛ በሆኑ ነበር ።
ደግሞ እንዲህ አሉን ፤ ጤፍ መብላት አይጠቅምም ፣ በጤፍ ውስጥ ምንም አይነት ለሰውነት የሚጠቅም ማዕድን የለበትም ፣ ዝም ብሎ ሰጋቱራ ነገር ነው ፣ የፈረስና የከበት ምግብ እንጂ የሰው ልጅ ሊበላው የሚችለው ምግብ አይደለም። እግር ኳስ ተጫዋቾቻችሁ እንዲህ ቀጫጭን የሆኑት የማይረባውን ጤፍና የጤፍ እንጀራ በመብላታቸው ምክንያት ነው ተባለና ሰው ጤፍን እንዲንቅ ተደረገ ፣ ጤፍ ተጠላች ትውልዱ ፈረንጅ ለመሆን ሲል የፈረንጅ ምግብ ነው ወደ ተባለ ነገር ፊቱን አዞረ ። ጤፍ ይመገብ በነበረ ጊዜ ጤነኛ የነበረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አሁን የፈረንጅ የተባለ ምግብ ሲመገብ ጊዜ የሚፈልገውን ውፍረት አገኘ ፣ ፊቱም ወዛ አለ ፣ ቀላም አለ ፣ ፈረንጁንም መሰለ ፤ ነገር ግን በተቃራኒው ደግሞ በሽተኛ ሆነ ። በኢትዮጵያ ታሪክ በምንመገበው ምግብ እና በአመራረት ዘይቤያችን ምክንያት ሰው ሁሉ በከንሰር ፣ በጉበት ፣ በኩላሊት ፣ በስኳር እና በጨጓራ ምክንያት ይረግፍ ጀመር ፣ የሆስፒታል አልጋዎች ጠፍተው ዜጎች ኮሪደር ላይ ተሰቃይተው የሚሞቱባት ሀገር ሆነች ።
እና አሁን ጤፍን ከዘረፉን በኋላ ዛሬ የእነሱ ሰዎች ጤፍን በመመራመር ፕሮፌሰር ተባሉበት ፣ በጤፍ ውስጥ ያለውንም አስደናቂ ንጥረ ነገሮች በሙሉ እየተደነቁ መልሰው ይተነትኑልን ጀመር ፣ ዛሬ በአውሮፓና በአሜሪካ ጤፍን መመገብ በጤና ለመኖር እንደዋስትና ተቆጠረ ። እኛ ግን እንረግፋለን ። እነሱ አንድ ኪሎ ጤፍ የወርቅ ዋጋ ተምነውለት መልሰው በውድ ይሸጡለታል ።
እነሱ ፊደል መቁጠራችንን ፣ በቄስ ትምህርት ቤትም ማለፋችንን እንደ ፋርነት እንድንቆጥረው አደረጉን ። ግዕዝ ማጥናት ፣ መነጋገር ፣ መጻፍ የፋሮች ፣ የኋላ ቀሮችም ነው ብለው እኛን አስጣሉን ። በጎን ግን ዘረፉን ፣ አስዘረፉን ፣ ቋንቋውንም የሚያስተምሩበት ዩኒቨርስቲዎችን ከፍተው ግእዝን ያጠናሉ ፣ በግእዝ የተጻፉ መጻህፍትንም በመመርመር የተደበቁ ጥበቦችን ያፈልቁበት ጀመር ።
እኛን ጤና አዳምን እና ዳማከሴን አስጥለው እነሱ ጀሶና ከኖራ የተሰራ እንክብል አዋጡን ። በጦርነት ያልጠፋን ህዝቦች እነሱ በሰው ሰራሽ ችግሮች ፈጁን ።
2ሺ ዘመን የቆየውንና ስንታመም የሚጸልይልን ፣ ስንጣላ የሚያስታርቀንን ፣ በ40 እና በሰማንያ ቀናችን ከምስጢረ ጥምቀት የሚያካፍለንን ፣ ወንጌል ሰብኮ ፣ ቀድሶ አቁርቦ ስንሞት በጸሎተ ፍትሃት የሚሸኘንን የራሳችንን ካህን እንድንጠላ ፣ እንድንንቀው ፣ እንዳንሰማው አደረጉን ፣ እነሱ ግን ፓስተር የሚባል ስያሜ የተሰጠውን ጎረምሳ እንደ ኳስ የሚያንቀረቅበንን ፣ በአደባባይ የሚያዋርደንን ፣ የሚጫወትብንን ፣ የሚቀልድብንን ፣ ከኮሜዲያን በላይ የሚያስቀንን የእኛን ካህን የሚተካ አምጥተው አስቀመጡብን፣ አለማመዱን ፣ አሁን ትውልዱ እንደ ፓስተር የሚፈራው እና የሚያከብረው ሰው በዚያች ምድር ላይ ያለ ማንም የለም ።
የባህል ልብሳችንን አስወልቀው ታይትና ጅንስ አስታጠቁን ፣ የጸጉር አሰራራችንን ሳይቀር እንድንጠላው ተደረግን ፣ ትውልዱ ከራሴ ጀምሮ ፣ ጠጪ ፣ አመንዝራ ፣ ጫታም እና ሰካራም እንድንሆን አደረጉን ። ነፈዝ ሆንን ፣ ጀዘብን ፣ ከንቱና የማንረባ ሆንን ፣ አሁን በቁማችን ሞተናል ። ስለ ሀገር መጠየቅ ፋርነት ነው ። ማጨስ ፣ መጠጣት ግን ፋሽን ፣ ነው ዘመናዊነት ሆኖ ትውልዱ ላሽቆ እንዲቀመጥ ተደረገ ። ሐሰት ነገሠች ፣ እውነት ሀገር ለቃ ተሰደደች ። መሪዎች ሳይቀሩ ፣ ሚዲያው ሳይቀር ፣ የሃይማኖት አባቶችና ታላላቅ ሰዎች ሳይቀሩ ሐሰተኞች ሆነን ተገኘን ።
አሁን ትውልዱ ለምለሟን እና ውስጧ አረንጓዴ የሆነውን ሀገር ጠልቶ እግሬ አውጪኝ ብሎ እየተሰደደ ነው ። ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ መነኮሳት ፣ ባህታውያን ፣ ማየት የሚያስጠላው ትውልድ እንዲፈጠር በብርቱ ደከሙ ። ለጊዜው ሲያዩት የተሳካ መስሎ ታይቷል ። እግዚአብሔር ግን አሳልፎ አይሰጠንም ።
አደዋ ላይ ፣ ገጉንደት ላይ ፣ ምጽዋ ላይ ነጮቹን ድል መንሳታችን ቂም አስቋጥሮብን ይኸው ዋጋ እያስከፈለን ነው ። ሀሰት የሚል ካለ ይምጣ. ፣ ።
የምንወደውን ነገር ሁሉ እንድንጠላ እየተደከመ ነው ። ባንዲራውን ብትሉ ፣ አንድነትን መመርጥ ብትሉ ፣ እጅግ አይወደድም ፣ የተበታተነ ፣ የማይግባባ ፣ የማይተማመን ዜጋ እንዲፈጠር በብርቱ ተለፋ ፣ እናም እየተሳካ ነው ። በኢትዮጵያዊነቱ ሳይሆን በብሄሩ የሚመካ ትውልድ ተፈጠረ ፣ ጠቡ አሁን ፍሬ እያፈራ ነው ። ሰሞኑን በመቀሌ ያየነው የባህርዳር ከነማና የመቀሌ ስፓርት ደጋፊዎች ጠብ የጤና አይመስልም ። ከተለመደው እና በእስፓርት ሜዳ ከምናየው ጠብ የተለየ ነው ። ማንነትን መሰረት ያደረገ ጸብ ነው ።
ፈረንሳይ ፣ ቤልጂየም ፣ ጣሊያን ፣ ስዊዘርላንድ ፣ ኦስትሪያ እና ሆላንድን አይቻለሁ አሁንም በጀርመን እገኛለሁ ። አንዳቸውም መታወቂያቸው ላይ በጎሳው የሚጠራ አላየሁም ፣ ተሳስቼ ከሆነ እታረማለሁ ። የእኛ ግን አሰቃቂ ነው ። እግዚአብሔር ይጠብቀን ።
የመጨረሻው ታርጌት ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ ነው ። ትውልዱ እንደፋሽን የያዘውን ነገር ተመልከቱልኝ ከደቡብ ክልል የጀመረው ሃይማኖትን የማስቀየር ዘመቻ አሁን አሁን መሃል ሀገሩን ጥሶ የአማራውን ክፍል አልፎ ትግራይ ገብቷል ። ኤርትራ አስቀድማ እንድትገነጠል ተደርጓል ። አሁን ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ሙልጭ አድርገው አጥበው አዲስ የጎሳ ማንነት የተላበሰ ፣ አዲስ ሃይማኖት የሚከተል ፣ ሀገር ፣ ባህል ግድ የሌለው ትውልድ ተፈጥሯል ።
መቀሌ በተሃድሶ ፕሮቴስታንቶች እየታመሰች ነው ። ሽሬ ተሃድሶዎቹና ኦርቶዶክሶቹ የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ነው ። አዲግራት ደግሞ " አዲግራትን ለኢየሱስ " የሚል ፕሮጀክት ቀርጸው የሚንቀሳቀሱ ዲያቆናትና የሰንበት ተማሪዎችን በመመልመል በሱዳን ካርቱም ተመልምለው በአዲስ አበባ ሰልጥነው አዲግራት ድረስ ሄደው ስልጠና የሚሰጡ የተሃድሶ አባላትን ማሰማራት ጀምረዋል ። የሚገርመው አዳራሹን የሚፈቅድላቸው መንግሥት ሲሆን ፈቃዱን የሚጠይቁላቸው ደግሞ ፕሮቴስታንቶች ናቸው ። መረጃውን ሰሞኑን ጠብቁኝ ። በአይናችሁ ታይቱላችሁ ።
አሁን የቀረው ማነው ያልን እነደሆነ አክሱም ጽዮን ማርያም ። በመጨረሻም ሀገሩ በሙሉ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንዲጠላ ይደረግና ፣ ሃይማኖቱንም በሙሉ ወደ ፕሮቴስታንትነት ይቀይርና ፣ ታቦት አያስፈልግም ፣ ይውጣ የሚል ትውልድ በንደንብ ከፈጠሩ በኋላ ታቦተ ጽዮንን ከአክሱም በመውሰድ ሦስተኛውን መቅደስ ሠርተው ሲጨርሱ የለ ግርግር ታቦት የሚጠላው ትውልድ በክብር ያስረክባቸዋል ማለት ነው ።
ስለዚህ በቀጣይ በኢትዮጵያ እንዲህ ይሆናል ። በዋነኝነት ማኅበረ ቅዱሳን በውድም ሆነ በግድ እንዲፈርስ ይደረጋል። በአረጋውያኑ ጳጳሳት ምትክ አዳዲስ የተሃድሶ አራማጅ የሆኑ ወጣት ጳጳሳት ቦታውን እንዲይዙ ይደረጋል ። የሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲፈርሱና በፕሮቴስታንታዊ ቅኝት በተቃኙ የተሃድሶ ሰራዊት ይተካል ።
የካህናትን ክብር የሚያጎድፉና ካህናት እንዲጠሉ የሚያደርግ በአደባባይ የሚሰክር ፣ የሚጠጣ ፣ የሚዘርፍ እንግዳ መነኩሴና ካህናት ይፈጠራሉ ።
በዚህ መሃል ግማሹ በአዲሱ እምነት ይማረካል ። ቤተመቅደሱ ላይ የጥፋት ርኩሰት ይቆማል ። ይህንን ጉድ የሚጋፈጡ ጥቂቶች ፣ ይታሰራሉ ፣ ይገደላሉ ፣ ይሰደዳሉ ። አንዱ ሌላውን እንዳይረዳው እንኳ አስቀድሞ በግልፅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጎሪጥ እንዲተያይና እንዳይተማመን በመረረ የዘር ጥላቻ እንዲዋጥ ተደርጓልና ማንም ማንንም አይረዳም።
በአሩሲ አኖሌ በፈጠራ ታሪክ የአያቶችሁን ጡት የቆረጠው ይሄውልህ ተብሎ ያደገው ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ ለበቀል ከመሮጥ በቀር ሌላ የሚያቆመው ያለ አይመስልም ። ለረጅም ዘመናት በአንድነት ኢትዮጵያን የገነቡት ጎንደሬ ኢትዮጵያውያንና የትግራይ ኢትዮጵያውያን በግድ ጥላቻን እየተጋቱ እንዲያድጉ ስለተደረጉና አሁን ደግሞ ይበልጥ ዙሩን እያከረሩት በመምጣታቸው አያድርስና በትግራይ አንድ ችግር ቢፈጠር ፣ ደግሞም በጎንደር አንድችግር ቢፈጠር ለመረዳዳት የሚደረግ ነገር እንደ ቀድሞው ፈጣን አይመስለኝም ። ይሕ ሁሉ ሲሆን የፕላኑ አውጪዎች ግን ቁጭ ብለው ይሳቃሉ ። እዚህ ጀርመን ከህዝቡ መሃል ሃይማኖት አልባው ይበዛል ። ፓስተሮቹ ግን ህዝባቸውን ሃይማኖት አልባ አድርገው እነሱ ሻንጣቸውን ጠቅልለው ከእነ ፓስተር ዳዊት ጋር ለመሥራት ኢትዮጵያ ከትመዋል ።
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ሃብታም ለመሆን ከፈለግክ ፕሮቴስታንት መሆን ብቻ ነው የሚጠበቅብህ ። ሥራ የለም ግን ሀብት አላቸው ። ንግድ ቀዝቅዟል ፕሮዎቹ ግን የናጠጠ ኑሮ ይኖራሉ ። የእኛዎቹ እነ በጋሻውና ያሬድ አደመን እንኳ ተመልከቱልኝ ፣ የ53 ሚልየን ብር ፋብሪካ በአንድ ጀንበር ከፍት. አድረዋል ። ተሃድሶና ጴንጤ ከሆንክ የሚገጥምህ እጣ ይኽ. ነው ።
ወዳጆቼ መፍትሄ ግን አለው ።
መፍትሄውም በመጀመሪያ ልባችንን ክፍት አድርገን በዙሪያችን ምን እየተካሄደ እንደሆነ ማየት ይገባናል ። ከዚያም ለፍቅርና ለእርቅ እንዘጋጅ ። ውይይቱን በቤተሰብ እንጀምር ።
አሁን በተፈጠረው ነገር አኩርፋችሁ ከቤት እንዳትቀሩ አደራ ፣ እናንተ ከቀራችሁ ፤ ቤተክርስቲያኑን ባዶውን ስለሚያገኙት ይወርሱናልና በምንም ተአምር እንዳትቀሩ ። አደራ ከቤተክርስቲያን እንዳትቀሩ ። በምንም መልኩ ቢሆን ድንጋይ መወርወር ፣ ጮክ ብሎ መሳደብ የተዋሕዶ ልጆች መገለጫ አይደለምና እንዳታደርጉት ተጠንቀቁ ። ዝም ብሎ እውነትን ይዞ መሟገት ብቻውን በቂ ነው ። አሸናፊም ያደርገናል ። ከሁሉ አስቀድመን ግን ሁላችንም ንስሐ እንግባ ፣ ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት እንቅረብ ። እንወያይ እንደማመጥ ፣ እንከባበር ፣ እንዋደድ ።
ከመካከላችን አንድ ሙሴ እንምረጥ ። ወይም መርጦ እንዲሰጠን ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ ፣ ሱባኤ እንግባ ፣ አባቶቻችንም እኛም በድለንሃል ብለን እናልቅስ ። አይናችን እያየ በታሪክ እርስ በእርስ በሃይማኖት ምክንያት አደጋ ላይ ከመውደቃችን በፊት እንምከር ፣ እንመካከር ።
እንደ አርቲስት ቴዲ አፍሮ አይነቱን ህዝቡን በኢትዮጵያዊነት የፍቅር ገመድ አስተሳስሮ አንድነትን የሚሰብክ የፍቅር ሰዎችን ያብዛልን ።
በእኔ በኩል የትግራይ ልጆችን አደጋው ከባድ እንደሆነ ለማስረዳት ብዙ ደክሜያለሁ ፣ ቀላል የማይባሉ የትግራይ ልጆችም ይህንን ተንኮል የምትሠራው ህውሓት ናት የሚል ሃሳቤን በማቅረቤ ምክንያት በብዙዎች ዘንድ የትግራይን ህዝብ እንደምጠላ ተደርጌ ፕሮፓጋንዳ ስለተሠራብኝ ሊሰሙኝ እየፈለጉ ነገር ግን ዘረኛ እየመሰልኳቸው ጆሮ ዳባ ልበስ ሲሉኝ ቆይተዋል ። እኔም ድርቅ ብዬ ህዝብና ፓርቲ አንድ አይደለም ። እናም እባካችሁ ግድየላችሁም ብዬ ተጨቃጭቄ ዛሬ ላይ ቁጥሩ ቀላል የማይባል የትግራይ ልጆች ከጎኔ ቆመዋል ። መረጃዎች በሰነድ የተደገፉ ወደ እኔ በመጉረፍ ላይ ናቸው ።
አሁንም የትግራይ ልጆች ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ከልባችሁ ስሙኝ አድምጡኝም ። ከአነጋገሬ ስህተት ሳትረዱኝ ቀርታችሁ የተቀየማችሁኝ ካላችሁ ፤ እንዲያው በተሰቀለው መድኃኒዓለም ፣ በታቦተ ጽዮን ፣ በአክሱሟ ማርያም ፣ በጻድቁ አቡነ አረጋዊ ፣በአብርሃወአጽብሃ ይዣችኋለሁ ፣ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም እግራችሁ ስር ተደፍቼ እለምናችኋለሁ ። አጥፍቼ ከሆነ ማሩኝ ፣ ይቅርም በሉኝ ።
ፖለቲካ ሃላፊ ነው ። ፖለቲከኞችም እንዲሁ ። የማታልፍ እና ጌታ እስኪመጣ የምትቆየው ሀገር ናት ። እባካችሁ እባካችሁ ተለመኑኝ ፣ ኢትዮጵያን ታደጓት ።
ስለ እኔ ኢትዮጵያዊነት ለማወቅ ከሀገር እስክወጣ ድረስ በአክሱም ከተማ ውስጥ ከመንግሥት ተረክቤ አስተምራቸው የነበሩትን የአክሱም የድሃ ልጆች ቤተሰቦችና የከተማውን ከንቲባ ጽ/ቤት ጠይቁ ። ደብረ ዳሞ ሂዱና ፣ አቡነ መድኃኒነ እግዚም ሂዱና ፣ አብርሃ ወአጽብሃ ፣ ገርአልታ አቡነ ይምአታ ፣ ማኅበረ ዶጌና ራሷ አክሱም ጽዮን ሄዳችሁ ዘመድኩን ማነው ብላችሁ ጠይቁ ። በሊቢያ የተሰውትን ሰማዕታት ቤተሰቦች ኢንቲጮና ገዛ ገረሥላሴ ሄዳችሁ ስለ እኔ ጠይቁ ። ይነግሯችኋል ።
እኔ አሁን ብዙም የደኅንነት ስሜት አይሰማኝም ሆኖም ግን ሌላ አማራጭ ስለሌለኝ የማይቀረው ነገር እስኪመጣ ድረስ እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ የቻልኩትን ያህል ለመታገል እሞክራለሁ ። እይታዎቼንም ወደ እናንተ አቅም በፈቀደ መጠን ለማድረስ እሞክራለሁ ።
በስልኬ ላይ ስለምጽፍ እንጂ በቻልኩት መጠን ቶሎ ቶሎ በመጻፍ ወደ እናንተ ባደርስ ምንኛ በወደድኩ ነበር ። ለመድረስ እሞክራለሁ ። የሚፈጠረው አይታወቅምና ድንገት የማያምር ነገር መጥፎ የሆነም ዜና በእኔ ላይ ቢፈጠርና ብትሰሙ የለጆቼን ነገር.! አደራ.! አደራ.! አደራ.! አደራ በሰማይ አደራ በምድርም አደራ ። የእናንተ ልጆች ናቸው ። አሳድጉልኝ ፣ አስተምሩልኝ ፣ ለቁምነገር አብቁልኝ ። አሁን እየደረሱኝ ያሉት ዛቻዎች ደስ አይሉም ። ነገር አንድ ጊዜ የነብሩን ጭራ ይዧለሁና መልቀቅ ብሎ ነገር አይታሰብም እዚህ ጀርመን ድረስ እዚሁ ሆነው የተቆጡብኝ ስላሉ ምንም። ምንም አይነት ነገር በእኔ ህይወት ላይ ቢፈጠር አደራ ሃይማኖታችሁን ከመጠበቅ ወደ ኋላ እንዳትሉ ። ታቦተ ጽዮንም በእኔና በእናንተ ዘመን እንዳትነጠቅ ። ቅዥት ቢመስልም ግን እውነታው ይሄው ን. ።
በቀጣይ ጽሑፌ በእስከ አሁኑ ሂደታችን ተሸንፈናል ወይስ አሸንፈናል የሚለውን ለማየት እንሞክራለን ።
የኢትዮጵያ ቡናና ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በሚያሰሟት የጋራ ዜማቸው እንሰነባበት ።
አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
እንኳንም ተሰደድኩ ፣ እንኳንም አስጨንቀው ከሀገሬ አስቀሩኝ ። ስለእውነት እንነጋገር ከተባለ አሁን እንደምፈነጨው በሀገሬ ብሆን እፈነጭ ነበርን? ። መንፈራገጤ አይቀርም ነበር ። ነገር ግን ኮማንድ ፖስቱ ዋጋዬን ሰጥቶ አደብ ያስገዛኝ ነበር ። ወይ አንቀጽ ጠቅሶ ሸዋሮቢት ፣ ወይ ደግሞ አከናንቦ ሰማይ ቤት ይልከኝ ነበር ። አሁን ግን ለጊዜው ሰላም ወረዳ ነው ያለሁት ፤ እናንተ መረጃዎችን ላኩልኝ እኔ እንደሚሆን እንደሚሆን አደርገዋለሁ። እስከ ጊዜው ድረስ ።
" እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
አንቺ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሆይ.! ጌታ በደሙ የመሰረተሽ ነሽና ደሙ ይፍረድልሽ ። አከተመ በቃ.!
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ፌስ ቡክ What's on your mind? ስላለኝ ይህንንም ራሴው ከአእምሮዬ አቅንቼ በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 11/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
ግንቦት 11/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
No comments:
Post a Comment