★ ★ ★ ★ ★
✔Share ~ Share ~Share በማድረግ ይኅንን መልእክት ላልሰማ አሰሙ ። ላልደረስው አዳርሱ ። ✔ Comment ~ Comment ~ Coment በመስጠት ደግሞ አዳዲስ ሃሳብ አፍልቁ ።
✔እባካችሁ አትደውሉልኝ ። መልእክት በቻ ጻፉልኝ ። እረ ልፈነዳ ነው ። ተባበሩኝ ጓደኞቼ.!!
✔በመሃል እየገቡ ያልሆነ የብስጭትና ከርእሳችን ውጪ አጀንዳውን ለመጠምዘዝ የሚሞክሩትን እንደበፊቱ አልታገሳቸውም ። መብቱ በእጄ ስለሆነ ይህን ከመሰለ ጮማ የሆነ ጦማት ከሚኮመኩሙበት ገበታ አስወግዳቸዋለሁ ። እመ አምላክ ምስክሬ ናት ።
✔ አሁን እኛ ስለ ራሳችን የምንመካከርበት ግዜ እንጂ የእነሱን ቅርሻት የምንጠርግበትና እሱንም ለማጽዳት ጊዜ የምናጠፋበት ወቅት ላይ አይደለንም ። አራት ነጥብ ። እስቲ ወንድ የሆንክ አሁን እኔ ፔጅ ላይ አፍህን ክፈት ። አሳይሃለሁ ። Block በተባለ ሰይፍ ነው ቆርጬ ከፔጄ ላይ የማስወግድህ ። ሰምተሃል.!
✔ትግላችሁ እንዳይቆም.! በፍፁም ኦርቶዶክሳዊ ጨዋነትና ጥበብ አጠናክራችሁ ቀጥሉ ተብላችኋል ።
✔ ብረትን መቀጥቀጥ እንደጋለ ነውም ብለዋል ። እናም የእምዬ ልጆች ዝግጁ ናችሁ. !???
የተከበራችህ ውድ የእምዬ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ ። የቅድስት የቤተክርስቲያናችንም ሆነ የኢትዮጵያ ሀገራችን ትንሳኤ የቀረበ መስሎ ይሰማኛል ። ደግሞም እንደዚያም ነው ።
በሰሞኑ በእኔና በእናንተ የተቀናጀ እና ውጤታማ ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ ትግል የተነሳ አስደናቂ እና የሚያኮራ ተግባር መፈጸማችን ይታወቃል ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ እንዲህ አይነት የሚያስደንቅ ፣ የሚያኮራ ፣ እንባና ሲቃ ፣ እልህና ቁጭት ተፈጥሮ በያገባኛል ባዮችና ፣ መብቴነው በሚሉ የተዋህዶ ልጆች አስደማሚ ተሳትፎ ምክንያት ታሪካዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ወርቃማ ገድል ፈጽመናል ።
በዘህ እንቅስቃሴ መንግሥት ደንግጧል ፣ መናፍቃን ተበሳጭተዋል ። ሌላው ቢቀር የጀርመን ዜግነት ያላቸው ነጭ ጸሐፊዎች እንኳን " የዘመድኩን ውሸት " በማለት በአካል ባያውቁኝም በስማበለው በሰሙት መጥፎና ወሽመጥ ቆራጭ ዜና አማካኝነት ተናደው አርቲክል አዘጋጅተው ለንባብ አብቅተዋል ። ከመናፍቃኑ ወገን አባ ኃይለማርያም እና አባ ተክለሃይማኖት እንዲሾሙ ፕሮቴስታንቶችና ፓስተሮች ሳይቀሩ የፆም አዋጅ እስከማወጅ ደርሰዋል ። ለጊዜውም ቢሆን አባ ኃይለማሪያ በሴራና በተንኮል ። አባ ተክለሃይማኖት በጠመንጃ አፈሙዝ በግልጽ መሾማቸው በተሰማ ጊዜ በእኛ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ የድንጋጤ ፣ የተስፋ መቁረጥ ፣ የሀዘን ፣ የመከዳት ፣ የመሸጥ ፣ ስሜት ሲያድርብን ፣ በአንጻሩ ደግሞ በተሃድሶዎቹና በመናፍቃኑ ዘንድ ስሜታቸውን መቆጣጣጠር አቅቷቸው በድስታ የዓለም ዋንጫ እንደበላ ሀገር ሲፈነጥዙ ታይተዋል ።
ለማንኛውም ይህ የመናፍቃኑ ደስታ እና የእኛም ሀዘን ብዙም አልቆየም ። ወዲያው በድርጊቱ የተበሳጩ የተዋሕዶ ልጆች ለእረፍት ለምሳ ወጥተው የነበሩትን አባቶች በስልክም በአካልም መቆሚያ መቀመጫ በማሳጣት በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አንድ በሐሰትና በቁማር ያውም በጨበጣ የተሾመን ጳጳስ ሹመቱ ይቆይ አስብለናል ። በዚህ ነው ፈረንጆቹ ፣ ተሃድሶዎቹና ፕሮቴስታንቶቹ የተበሳጩት ። እኛ ግን ደስ ቢለንም ገና ትግላችንን አልጨረስንም ። አይደለም እንዴ.??? ዋሸሁ እንዴ.???
አሁን አብዛኛዎቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሁኔታችን ፣ በምእመናን ትብብር ፣ ጫና መፍጠር ፣ በእጅጉ ኮርተዋል ። በተለይ ልጅ እግሮቹ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከሚገባው በላይ ደስተኞች ሆነው ተገኝተዋል ። እናም በዚህ ምክንያት ምእመናን ድርሻቸውን እንዲህ አውቀው ፍፁም በሆነ መንፈሳዊ ስነስርዓት አሁን ካለው በበለጠ ሁናቴ ተጠናክረው ከቀረቡ የማይለወጥ ነገር የለም ብለዋል ።
ትናንት ተሰባስበው መረጃ የሰጡኝና መልእክቱን ለህዝብ አስተላልፍልኝ ያሉት ብፁዓን አባቶች አንተ ዘመዴ አንደበት ስለሆንከን ፣ መተንፈሻችንም ስለሆንክ እጅግ አድርገን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን ብለዋል ።
አሁን ከዚህ ፖስት በመቀጠል በእዚህ ጉባኤ ትልቁን ሴራ በመሥራት ዶር አባ ኃይለማርያምና አባ ተክለሃይማኖት እንዲመረጡ ግፍ የሰሩ በተለይ ሁለት አባቶችን አዳፋሪና አንገት የሚያስደፋ ተግባር ለህዝብ ይፋ አድርገው ብለው ልከውልኛል ። ያበጠው ይፈንዳ ።
እኔም ይሄን እንደመግቢያ አድርጌ የተንኮለኞቹን አባቶች ስምና ፎቶ ፣ መጀመሪያ የእጅ ስልካቸውን እሱን አላነሳ ካሉና ከዘጉ ደግሞ የቢሮና የቤት ስልካቸውን እለጥፈዋለሁ ። አሁን ይህን 2009 ዓመተ ምህረትን ቤታችንን ጽድት አድርገን 2010 ዓመተ ምህረትን ተንኮለኛ ፣ ሴረኛ ፣ ሙሰኛ ፣ ዘማዊ ፣ ፖለቲከኛና ፣ ካድሬ ካህናትና መነኮሳትን መስመር አስይዘን የደስታ ፣ የፍቅር ጉዞ እንጀምራለን ።
ከእንግዲህ ወዲያ መደራደር የለም ፣ እስቲ 60 ሚልዮን የሚገመተውን የእምነቱን ተከታይ የመንግሥት ወታደሮች ሲያስቆሙት እናያለን ።
ይሄ ሌባ ሌባው ወንበዴና ዘራፊ ሆኖ ሳለ በደብር አስተዳዳሪነት ፣ በፀሐፊነት ፣ በገንዘብ ቤት ፣ በቁጥጥጥር ስም ተመራርጠው በየደብሩ የተሰገሰጉ ሌቦችንም መንጥረን እናወጣለን ። አንዳቸውንም አትፍሯቸው ። እያንዳንዳቸውን እናውቃቸዋለን ። ትናንት ከገጠር ሲመጡ ምን ይመስሉ እንደነበሩ እናውቃቸዋለን ፣ ፎሮፎር የወረሰው ጭንቅላት ፣ ወርጭ ያደረቀውና ጭርት ያበላሸው ፊት ፣ የተበጫጨቀ ኮትና ነጠላ ፣ ሙጀሌና የሞላው ባዶ እግር ፣ እንቅፋት የነቀለው ጥፍር ፣ መግል የቋጠረ እግር ፣ እከክ የወረሰው ገላ ይዘው ነው ወደ እኛ የመጡት ። እያንዳንዱን እናውቀዋለን። ከሁሉም ጋር እንተዋወቃለን ። ከሁሉም ጋር ። አዳሜ እከኩን ካራገፈ በኃላማ ፣ ሙጀሌውን ካወጣ በኋላማ አሁን በዘረፈን ገንዘብ ተንደላቅቆ መኖሩ ሳያንስ የክህደት መርዙን አያቀረሽብንም ። በፍፁም ። ቱ ሞተናታላ. ። በእኛ ዘመን ቤተክርስቲያን አትፈርስም ። እንዲህ አይነት ቆሻሻ ታሪክም በዘመናችን አይፈፀምም ።
አሁን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ እንደየ አደገኝነታቸው እና እንደነበራቸው አፍራሽ ሚና ያርፉ እንደሆን እንዲያርፉ ፣ የማያርፉ ከሆነ ግን ቀልድ ስለሌለ እረፍት የሚነሳ ተቃውሞ የምናነሳባቸውን የከዱንና ከመንግሥት የደኅንነት ኃይሎች ጋር እስከ ሌሊቱ 8 ሰዓት በመዶለት በጥርነፋ ገብተው ሌሎቹ በፁዓን አባቶች ላይ ተፅእኖ የፈጠሩ አባቶችን ክፉ ስራ ተራ በተራ ለማየት እንሞክራለን ።
ጎበዝ ጨከን ብለን በድፍረት ካልተነጋገርን ለፀላ ምንም አይነት መፍትሄ እንደሌለን እወቁ ። አማራጭ የለንም ። ቤተክርስቲያን የህእብ ናት ። እናም ለህዝቡ የሚሾሙትን አባቶች መምረጥ ያለበት ህዝቡ እንጂ ኢህአዴግ አይደለም ። ኢህአዴግ ከፈለገ ዶር አባ ኃይለ ማርያምንም ሆነ አባ ተክለሃይማኖትን በለመደው መንገድ ይጠቅሙኛል ብሎ ካመነበት ለፓርላማ አቅርቦ ያወዳድራቸው ። አለቀ ። በቃ ይኸው ነው ። አከተመ።
ምነው ሸዋ.! አለ ሌሊን ። ሆሆይ!
" እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
አንቺ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሆይ.! ጌታ በደሙ የመሰረተሽ ነሽና ደሙ ይፍረድልሽ ። አከተመ በቃ.!
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ፌስ ቡክ What's on your mind? ስላለኝ ይህንንም ራሴው ከአእምሮዬ አቅንቼ በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 11/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
ግንቦት 11/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
No comments:
Post a Comment