Thursday, 25 May 2017

ማን በቀደሰው ማይ ማን ይጠመቃል? ( በዲን አባይነህ ካሴ)


Share ~በማድረግ ላላየ እናሳዩ ፤ ላልሰማም እአሰሙ ።
Comment ~በመስጠት በድርጊቱ ላይ ተወያዩ ።
Tag ~ በማድረግ በፉጨት የተሻሉ ሰዎችን እንጥራ ።
...ዛሬ ደግሞ ተረኛው ዲን አባይነህ ካሴ ነው ። አንደበተ ርቱዕ ነው ። ሲጽፍ በብዕሩ ፣ ሲናገር በአንደበቱ ገዢ ነው ። ጀግና ጀግና ልጆችን በላይ በላዩ መውለድ የማይታክታት እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይኸው ዛሬ ደግሞ ልጇ ዲን አባይነህ ካሴ እኔም ጥያቄ አለኝ ብሎ ከተፍ ብሏል ።
ከዚህ ቀደም በፀረ ተሃድሶው ትግል ወቅት ግንባር ቀደም ታጋይ የነበረ መሆኑም በሁላችን ዘንድ ይታወቃል ። ለእነ " ታዴ " ተሃድሶ " የቀደመ የክብር ስማቸውን ከመዝገብ ቤት አቧራውን አራግፎ አውጥቶ ፤ ከኪዳነወልድ ክፍሌ መዝገበቃላት ውስጥ ፈልጎ " ሐራ ጥቃ " የሚለውን የቀደመ ስማቸውን ይጠሩበት ዘንድ ያስታወሰን ወንድማችን ነው ።
ዲን አባይነህ ካሴ ፦ በሙያው ኢንጂነርም ነው ። በገዛ ገንዘባችን ፣ ረቡብን ፣ በሚለው ስብከቱም ይታወቃል ። ለቅድስት ቤተክርስቲያን በርካታ መጻሕፍትን ያበረከተ ምርጥ የተዋሕዶ ልጅ ነው ።
አሁን ጀነራሎቹ እየመጡ ነው ። እንደኔ አይነቱ ከ " ፈንጅ ማምከን " ያልዘለለ ሙያ የሌለው ሰው አሁን ከሜዳው ላይ ገለል የሚልበት ጊዜም እየመጣ ነው ። በእኔ ቀፋፊ ጩኸት አንገታችሁን የደፋችሁ ወገኖች አሁን የጠላት ወረዳን ነጻ የማድረጉ ሥራ በመልካም ሁኔታ እየሄደ ስለሆነ ሥፍራውን ለሚመለከታቸውና ለሚገባቸው ሰዎች የመልቀቂያ ጊዜዬ እየደረሰ ነው ። እናም ትንሽ ጊዜ ነው የምትታገሱኝ ።
በአባ ኃይለማርያም ሺህ ሞት ላይ ጥያቄያችን ይቀጥላል ። አናቋርጥም ። የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት በድጋሚ እንዲያጤኑትም እንመክራለን ።
"ኤጲስ ቆጶስ በሚሾምበት ቀን ሰዎች ሁሉ ይገኙ። ሕዝብና ካህናት መስክረውለት ይሾም።..."ፍትሐ ነገስት በእንተ ኤጲስ ቆጶሳት ፤ አንቀጽ ፭፡፻፩ በሚለው መሠረት ህዝብና ካህናት ያልመሰከሩለት ግለሰብ አይሾምብንም ። አከተመ ።
በተለይ ይህ የህዝብ ፍላጎት ተጥሶ ይሄ መቅደሳችንን ያስደፈረ ግለሰብ በእንቢተኝነት ቢሾም ። በተለይ
ብፁዕወቅዱስ አባ ማትያስ
 ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ
 ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
 ብፁዕ አቡነ ገብርኤል
 ብፁዕ አቡነ ቀለሚንጦስ
የሕዝቡን ጩኸትና ተማጽኖ በመናቅ መቅደስ አርካሹ ዶ/ር አባ ኃይለማርያምና በመንግሥት ትእዛዝ እንዲሾሙ የሚፈለጉት አባ ተክለሃይማኖት ንጉሤ እንዲሾሙ እንዲያ መድከማችሁና ቤተ ክርስቲያንን ለውድቀት የሚዳርግና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚያሳዝን ድርጊት እንዲፈጸም አብዝታችሁ ስትታትሩ የታያችሁ በመሆኑ በዚህች ቤተ ክርስቲያንና ተከታዮቿ ላይ በጠላትነት የተነሣችሁ መሆናችሁ ይታወቅ ። እናም አዝነንባችኋል ። ሆኖም ግን አሁንም አልረፈደም ሥርዓተ ሲመቱ ከመፈፀሙ በፊት የሕዝብ ቅሬታ ተሰምቶ ጉዳዩን በድጋሚ እንዲታይ እንጠይቃለን እያልን በተቃውሞአችን እየቀጠልን በቀጥታ ወደ ዲን ኢንጅነር አባይነህ ካሴ ጦማር እንገባለን ። መልካም ንባብ ።




.......የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጁ አጥማቂ ፍለጋ ከአባቶቻቸው ይልቅ ወደ ፕሮቴስታንቶች ማዘንበላቸውን በራሳቸው አንደበት ተናገሩ፡፡ በሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደተከናወነ የተነገረው ቅብዓት አይሉት ጥምቀት በእርሳቸው ብቻ ሳይኾን በፓትርያርኩ ቡራኬ ሰጪነት የተከናወነ መኾኑ አነጋጋሪ ነው፡፡
እኛ እነርሱን ስናጠምቅም ይሁን ስንቀባ ብንገኝ ደግ በኾነ፤ አንድ ፓስተር ብድግ ብሎ አንድን በቁምስና ማዕርግ ያለ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛው አስተዳደር ውስጥ ተዋናይ የኾነን ሰው ሲቀባም ይሁን ሲያጠምቅ ማየት ከየት እንደመጣ እስካሁን ማንም አልነገረንም፡፡ ለጊዜው የነገሩ ሙሻዙር ወደ ም/ሥ/ አስኪያጁ ያጠንጥን እንጂ ዋናው ተጠያቂ መኾን ያለባቸው ፓትርያርኩ ናቸው፡፡ ሰውየው አድርግ የተባሉትን አድርገው ይኾናል፡፡ ይህም መለካዊነታቸውን ከሚያሳብቅባቸው በቀር ከተጠያቂነት ነፃ ያደርጋቸዋል ማለት አይደለም፡፡
እንኳን በማዕርገ ቁምስና በምእመን ደረጃም እንዲህ ያለ የሚፈጽም በሌለባት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይህን የኃፍረት ካባ ሊያከናንቡን መቁረጣቸው ብርቱ ጽዩፍ አድራጎት ነው፡፡ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለማን እንዴት መቼ እንደሚፈጸም በጉልህ የምታስተምርን ቤተ ክርስቲያን በቅጽሯ ውስጥ ነውረኛ ሥራ በማድረግ መሠማራት አደጋው ቀላል አይደለም፡፡ "የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል" ያለውን ልብ እንበል፡፡ ማር ፲፫፥፲፬።
ለመኾኑ እርሳቸው አሉ እንደሚባለው ጉዳዩ የተከናወነው በውኃ ነው ከተባለ፤ ጥምቀቱ ለልጅነት ነው ወይስ ለፈውስ? ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን ልጅነት የት ጥለውት ይኾን? አሞኝ ነው ካሉ ደግሞ ጠበል ቤት እንጂ ኪታ ለባሽ ፓስተር ይዞ ወደ መቅደስ መግባትን ምን አመጣው? ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በየትኛው አንቀጽ እንደሚወድቅም ሊነግሩን ይገባል፡፡ ኢኩሚኒካል ግንኙነትን ስለማጠናከር ነው ከተባለም በምሥጢር ተካፋይነት የሚፈጸም አይደለም፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንኳን ለመናፍቅ ትምህርተ ክርስትናን በመከታተል ላይ ያሉ ባለ ተስፋዎችን በቅዳሴ ጊዜ ምሥጢር ለመካፈል የበቁ አይደሉምና (ማለትም አልደረሱምና) ፃዑ ብላ ታሰናብታለች፡፡ እኒህን ጳጳስ አደርጋለሁ ብሎ . . . መነሣት ነገ ደግሞ ማንን አምጥተው በማን እንዲቀቡ ይኾን? ከአባቱ ውጭ ሌላ አባት መፈለግ . . .
በሰውየው ላይ ብዙ ችግር እንዳለ እየታወቀ ብዙ ጊዜ በዝምታ ታለፉ፡፡ አሁን ብለው ብለው በአደባባይ ቤተ ክርስቲያንን የማይመጥኑ መኾናቸውን በይፋ አጋለጡ፡፡ የሰውን ዲዘርቴሽን ግጥም አድርገው ገልብጠው ፒኤች ዲ አለኝ ሲሉ ኖሩ፡፡ ዝም ተባሉ፡፡ በሆለታ ገብርኤል አካባቢ ያለባቸውን ብዙ ነውረኛ ሥራ ሲሠሩ ኖሩ ዝም ተባሉ፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ . . .
በቅርቡ ቅዳሴ ረዘመ ብለው በሸገር ሬድዮ ሲነዛነዙ የነበሩት ፓትርያርክ አሁን ደግሞ እንዲህ ባለ ተግባር ላይ መሰለፋቸው ሒደቱን በጥሞና የሚያየው አካል ይፈልጋል፡፡ የእናት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንዲህ በዋዛ በዋዛ እየታለፈ መቀጠል የለበትም፡፡ የሃይማኖት ጉዳይ ቀስ በቀስ እንዲሸረሸር ብርቱ ጥረት የሚደረግ ይመስላል፡፡ በሰዓሊተ ምሕረት በተደረገው ይህ ኩነትም እንደ ደኅና ነገር ጳጳስ አስከትለው የደብር አለቆችን ጠርተው ታዳሚ ኾኖ መገኘት ምን ይሉታል? ቅዳሴው እንዲያጥር የሚከራከሩት ሰው ቀድሞም ቢኾን ምክሩን ያገኙት ከአንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር እንደነበር ነግረውን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ፓስተሮቹን ወደ ቤተ መቅደስ ይዘዋቸው ገቡ፡፡
በአሁኑ የግንቦቱ (፳፻፱) ሲኖዶስ ጉባኤ መካከል አንዱ ተነሥተው "መሠረት ስብሐት ለአብ መናፍቅ አይደለም" ብለው ድምፅ አሰምተዋል መባሉ ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው፡፡ አለማወቅ እንዲህ ካለ ድፍረት ያደርሳል፡፡ ክርስቶስ አማላጅ ነው ብሎ የቅዱሳንን ሥራ ለእግዚአብሔር ሰጥቶ የተናገረን ሰው መናፍቅ አይደለም ብሎ መከራከር ምን ይሉት ጥብቅና ነው፡፡ ሰውየው ሔደው የሙጥኝ ብለው የተጣበቁበት ድርጅት ምን ብሎ የሚያስተምር እንደኾነ በገሃድ እየታወቀ ለክርክር መሰናዳት ምን ይባላል?
የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን አቋም የሚሸራርፉትን በጥብቅ የሚቃወሙት አቡነ ቄርሎስ የሰጡት ምላሽ አንጀት አርስ ነው፡፡ የሚቅበዘበዝ ሀሳብ የሚያመጡትን እዚያው መገሠፁ የተገባ ለመድረኩ የሚመጥን ነውና፡፡ ግን እንዲሁ በቀላሉ መታየት አለበት ተብሎ መወሰድ የለበትም፡፡ ያንን ቃል የተናገሩት ጳጳስ ናቸውና በሀገረ ስብከታቸውም ብዙ ሃይማኖታዊ ውዝግብ እየፈጠሩ የሚገኙ ናቸውና ጉዳያቸው ለብቻ መታየት ይገባዋል፡፡ እኒህን ጳጳስ ሰውየው ራሱ ቢሰማቸው እንዴት በሳቀባቸው፡፡ ጥብቅናውን አይፈልገውም፡፡ ይብላኝ ለእርሳቸው እንጂ በአደባባይ ማንነቱን ደጋግሞ የተናገረ "ምስጉን" መናፍቅ ነው፡፡ ታዲያ ለሞተ ሰው ጥብቅና መቆሙን ምን አመጣው? ነገር ዝም ብሎ አይመዘዝምና ደጋግሞ ማጤኑ ይበጃል፡፡
እነዚህ ሦስት ጉዳዮች በለበጣ የሚታዩ አይደሉም፡፡ ይታሰብባቸው!
ይለናል ዲን ኢንጅነር አባይነህ ካሴ.!! ማነህ ባለ ሳምንት ጅግና የተዋሕዶ ልጅ ተረኛ ቀጥል.! ቀጥል.!
ያዝ እንግዲህ. ምድረ ግሪሳ ሁላ.!
"እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ይህንን ጦማር ዲን ዳንኤል ጻፈው መግቢያውንና ወቀሳውን እኔው ራሴ በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 ደግሞ የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 17/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ ።

LikeShow More Reactions
Comment

No comments:

Post a Comment

አዝማሪ ትዝታው የራሱንና የቤተሰቡን የአንገት ማዕተብ ከበጠሰ ቆየ ።

ግሪሳ ትዝታው ( ሉንጎ )  መቅሰፍት ሊወርድበት  ነው ★ ★ ★ ✔  Share ~ Comment ~ Like ~ Tag ★ አዝማሪ ትዝታው የራሱንና የቤተሰቡን የአንገት ማዕተብ ከበጠሰ ቆየ ። ★በኮሎራዶ.! ...