Thursday, 25 May 2017

የመርሕ ጥያቄ ? ? ? በዲን ዳንኤል ክብረት

የመርሕ ጥያቄ
? ? ?
በዲን ዳንኤል ክብረት
★ ★ ★
በዚህ 15 ቀን ብቻ ፔጄን ያዩ የተመለከቱ ሰዎች ቁጥር 9 ሚልየን ሊገባ መሆኑን ፌስቡክ እየነገረኝ ነው ። ታዲያ በዚህ መጠን ሰው ማግኘትና መድረስ ከቻልን የምን EBC. ን መለማመጥ ነው ። ዳይ ወደ ዘመዴ ገጽ መረጃ መላክ ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ ።
Share ~በማድረግ ላላየ እናሳዩ ፤ ላልሰማም እአሰሙ ።
Comment ~በመስጠት በድርጊቱ ላይ ተወያዩ ።
Tag ~ በማድረግ በፉጨት የተሻሉ ሰዎችን እንጥራ ።
እስይ ደስ ሲል ይኸው አሁን በስተመጨረሻም ቢሆን እነ ዳኒም መጡልኝ.! እንዴ ብቻዬን ልፈንዳ እንዴ.!? ሆሆይ.! ደግሞም ባይመጡም ጉዳዬ አልነበረም ። እንደውሻ ለመጮህ ማን ብሎኝ.??? እንደ እብድ ፣ ደግሞም እንደ ውሻ እጮሃለሁ ።
በነገራችን ላይ.! የዛሬን አያድርገውና ደያቆን ዳንኤል ክብረትና ባለቤቱ ወይዘሮ ጽላት ፤ እኔ ቃሊቲ በታሰርኩ ጊዜ ልጆቼን አርብ አርብ ከቤቴ ወስደው ቅዳሜና እሁድ ከልጆቻቸው ጋር አውለው ፣ አጫውተው ፣ እሁድ ማታ ወደ ቤቴ ይመልሱዋቸው ነበር ። ምክንያቱን ባላውቀውም ያ ሁላ ነገር ግን አሁን የለም ። እንዲያም ሆኖም ግን ዳኒ በእኔ ልብ ውስጥ " ልዩ " ስፍራ ነው ያለው ።
የሚገርማችሁ ነገር ዲን ታደሰ ትናንት የግድያ ሙከራ ከተደረገበት በኋላ አርፎ ይቀመጣል ብዬ ስጠብቀው ብሶበት ቁጭ ብሏል " ። ታዴ አረ እንዴት ነው ስለውም ፤ አይደለም በመኪና ከፈለጉ በአውሮፕላን ለምን አይገጩኝም ከእንግዲህ ወዲህ መላቀቅ ብሎ ነገር አይታሰብም ብሎ አስደስቶኛል ። እናም ይኽን የዲን ዳንኤል ክብረትን ከዶክተር አባ ኃይለማርያም ጋር የገጠመውን ሙግትና የሚያቀርበውን ጥያቄ እያነበብን ከቆየን በኋላ ጊዜ ሲገኝ የታዴ አዲሱ ጦማርም ይለቀቅላችኋል ። እናንተ ብቻ ፀባይ አሳምራችሁ በያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ፦
 በፓትርያርክ አቡነ ማትያስ.!
 በአቡነ ቀውስጦስ
 በአቡነ ቄርሎስ
 በአቡነ ገብርኤል
 በአቡነ ቀሌሜንጦስ
በእነ ዚህ አባቶች ጨጓራችሁን እየላጣችሁ ፤ እርር ድብን እያላችሁ ፣ ትንፋሻችሁን ቁርጥ ቁርጥ እያደረጋችሁ ። ጠብቁኝ ። እነዚህ አምስት አባቶች ቅድስት ቤተክርስቲያንን ተማምለው ጉድጓድ ሊከቷት ያሰፈሰፉ አባቶቻችን ናቸው ። እናም አንድ እግራችሁን ከመቃብር አፋፍ ከትታችሁ ሳለ ፤ ቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ ዶር አባ ኃይለማርያምን የመሰለ 666 መልእክተኛ ፤ አባ ተክለሃይማኖትን የመሰለ የመንግሥት ቅጥረኛ ጳጳስ ለማድረግ ያሴሩ ፣ የቅዱስ ሲኖዶሱንና የመንፈስ ቅዱስን ልዕልና የተዳፈሩ አባቶች ናቸው ። ጉዳዩን እስኪያስተካክሉ መቃብር እስክገባ ድረስ በየምክንያቱ እያነሳሁ ስወቅሳቸው ዘላለሜን እኖራለሁ ።
ዲን ዳንኤል ክብረት እስከ አሁን ዝም ጭጭ ትንፍሽም ሳይል ከርሞ አሁን በስተ መጨረሻ ቢሆን ብቅ ያለ ወንድማችን ነው ። ቢሆንም አልረፈደም ። ደግሞም ከመቅረት ይሻላል ። ልክ እንደ ዲን ዳንኤል ሁሉ አሁንም ቢሆን ዝም ጭጭ ያሉ የሰላም ጊዜ ሐዋርያዎች ሞልተዋል። ዘላለም ወንድሙ የተባለ በሰላሙ ጊዜ በየአውደ ምህረቱ ምስኪን ካህናትን እየዘረጠጠ " ቄሶቹን ልክ ልካ ቸውን ነገራቸው " እየተባለ በጴንጤዎቹ ጭምር ተወዳጅ ለመሆን የበቃና አሁን ቀጭን ኢንቬስተር የሆነው አፈ ጮሌ ሰባኪ ፤ በዚህ ሰዓት ሰማይ ይውጣ ምድር የሚታወቅ ነገር የለም ። እኔ ግን እመጣበታለሁ ።
ዶር ዘበነ የተባለው ወንድማችን ፣ በሰላሙ ጊዜ ከማይመለከታቸው ጴንጤዎች ጋር በመሟገት ፤ ያንንም ሙግት ሲዲ ቪሲዲ እያደረገ መልሶ ሸቀጡን ምእመናን ላይ ሲያራግፍ የኖረ ነጋዴ አሁን ዶርበሆንኩ ካለ በኋላ የት እንደደረሰ መድኃኔዓለም ይወቅ ።
ትንሽ ውር ውር ይል የነበረው መምህር ምህረተ አብ አሰፋም አሁን ድምፁን አጥፍቷል ። መምህር አስቻለው ከበደም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከገባ በኋላ ጎመን በጤና ያለ ይመስላል ።
መር ጳውሎስ መልክዓሥላሴ ፣ ዲን ተስፋዬ ሞሲሳ ፣ ዲን ደንኤል ግርማ ፣ ቀሲስ ሱራፌል ወንድሙ ፣ መ/ር በላይ ወርቁ ፣ ዲን ታዲዮስ ግርማ ፣ ቀሲስ ያሬድ ገብረመድኅን ፣ ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ፣ ቀሲስ ብርሃኑ ጎበና ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ፣ ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ ፣ ዲን ምትኩ አበራ ፣ መጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ፣ መጋቤ እሸቱ አለማየሁ ። ለዛሬ ያልሆናችሁ ለመቼ ልትሆኑ ነው ?? ። የማንን ጎፈሬ እያበጠራችሁ ይሆን ። አንተ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያስ ትግሉን ተቀላቅያለሁ ካልክ በኋላ ምነው የበላህ ጅብ አልጮህ አለ.?? አቡኑ ማሞ የተባልክ ሰባኪስ ዝም ብለህ ፊልም እየሠራህ ብቻ መሸቀል ነው እንዴ ሥራህ.?? ተናገር እንጂ.?? አንተ የማለዳ ኮበብ የጥንት የጥዋቱ የወንጌል አርበኛ መምህር ተስፉ ግርማ (አንድምታ) የትደረስክ ። ሊቀሊቃውንት ስምዓኮነ በእውኑ በሀገር ውስጥ አለህን.!??
እመኑኝ ቅድስት ቤተክርስቲያን ምንም አትሆንም ። በመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፈ አስቴር ላይ መርዶክዮስ አክራትዮስን ወደ አስቴር ሲልከው ያለውን ነገር ላስታውሳችሁ።
" በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? " አስ 4 ፣14
ዳታንና አቤሮን ሙሴና አሮንን ከመቅደሱ አስወጥተው በሌላቸው ስልጣን ቤተመቅደስ አጥነው የርኩሰት ሥራ ፣ የድፍረት ሥራ በፈጸሙ ጊዜ ምድር ተከፍታ እንደዋጠቻቸው ዘኁል 16 ማንበብ ይቻላል ። ዮዲት ጉዲት 40 ዓመት ፣ ግራኝ አህመድ 15 ዓመት ኢትዮጵያንም ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማውደም ያልፈነቀሉት ተራራ አልነበረም ። በሰይፍ ልጆቿን ፣ በእሳት ቅርሶቿን ለመውደም ሌት ተቀን ባዘኑ ። እነ ሱ ጠፉ የለምም ፣ ቤተክርስቲያን ግን በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተች ናትና ይኸው አለች ፣ ወዲፊትም መስሯቿ ክርስቶስ ኢየሱስ በክብር እስኪወስዳት ድረስ ትኖራለች ።
ግን ትዝብት ነው ትርፉ ። ሁላችንም የመናጢ ደሃ ልጆች ነበርን ። ይሄን ጉዳይ ሰይጣንም እግዚአብሔርም እኛም እናውቀዋለን ። አንቱ የተሰኛችሁትም በዚህች ቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ ታይታችሁ ነው ። እናም የእንጀራ ቤታችሁ የሆነችው ፣ የክብር አዳራሻችሁም የሆነቻችሁ ፣ ግርማ ሞገሳችሁ የሆነች እናት ቤተክርስቲያን በዚህ መጠን ስትወጋ ጮጋ ማለታችሁ በእውነት ዝምታችሁ ያስፈራል ። ደግሞ ተወቀስን ብላችሁ ቡራ ከረዩ በሉ አሏችሁ ። ማንም አይሰማችሁም ። ደግሞስ እኔ ታናሽ ወንድማችሁ ያልወቀስኳችሁ ማን እንዲወቅሳችሁ ፈለጋችሁ ። ማንስ ይውቀሳችሁ ። በጭባጫ ሁላ.! በሉ አትንበጫበጩ ። ቱ እውነቴን ነው እናንተ ከአሰግድ ታንሳላችሁ እንዴ .?? ተብታባው ከፍያለው ቱፋ እንዲህ በነጻነት ሲፏልል እያያችሁ ከእሱ ታንሳላችሁ በማርያም.??? ሰው እሳት የሚተፋ ብእርና አንደበት ይዞ እንዴት ይፈራል ። በእውነት ያሳፍራል ። ለማንኛውም እንጠብቃችኋለን ።
አሁን ወደ ዳኒ ጦማር ልውሰዳችሁ.???

......ሰሞኑን ዶክተር አባ ኃይለ ማርያም ኦርቶዶክሳውያን ካልሆኑ አካላት ጋር ያከናወኑትን ‹የጠበልና እምነት› ጉዳይ በተመለከተ አያሌ ጥያቄዎች ሲነሡ ነበር፡፡ ነገሩን ከየምንጮቹ ብሰማቸውም በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን የነበረው የቂሣርያው ገዥ ፊስጦስ ‹ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም፣ ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጥ የሮማውያን ሥርዓት አይደለም› (የሓዋ.25፣16) ብሎ የተናገረውን መሠረት በማድረግ አባ ኃይለ ማርያም ለጉዳዩ የሚሰጡትን መልስና ማብራሪያ ጠብቄ ነበር፡፡ መልስና ማብራሪያውንም ሰጡ፡፡
አባ የድርጊቱን መከናወን አምነው የክንውኑን ዓይነት ከተወራው የተለየ መሆኑን አብራሩልን፡፡
መልሳቸውን ስናጠቃልለው፡-
1. መርሐ ግብሩ ‹ውኃ ለሁሉም› በሚል መርሕ እንደተዘጋጀ
2. ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳት እንደተገኙበት
3. ተበጥብጦ ከመጣው ውኃና እምነት ጠቅሰው በተሳታፊዎቹ ግንባር ላይ ምልክት አንዳደረጉ
4. ሰውዬው ጣቱን አስጠጋ እንጂ አንዳልቀባቸው
መርሐ ግብሩ ‹ውኃ ለሁሉም በፍትሐዊነት እንዲዳረስ› ከሆነ እንዴት ነው እምነትና ውኃ በመበጥበጥ ውኃ ለሁሉም ሊዳረስ የሚችለው፡፡ ‹ውኃ ለሁሉም› የሚለው ጉዳይ የዐውደ ጥናት፣ የምክክርና ምናልባትም የጸሎት ርእስ ሊሆን ይችላል እንጂ እምነትን በውኃ በጥብጦ በመቀባት ‹ውኃ ለሁሉም› እንዴት ለማዳረስ ይቻላል? እምነት በውኃ በጥብጦ መቀባት ለፈውስ ያገለግላል እንጂ እንዴት ከውኃ ፍትሐዊ አጠቃቀም ጋር ተገናኘ? ደግሞስ እኛ ከሌሎች እምነቶች ጋር አንድነታችንን ማምጣት ያለብን በክርስቶስ እንጂ እምነት በውኃ በመበጥበጥ ነው እንዴ?
አባ ኃይለ ማርያም በሰውዬው (የሌላ አምነት መሪ መሆኑ ከፎቶውና ከመረጃው ይታወቃል) ግንባር ላይ ሲቀቡት ምን እንዲያደርግ አስበው ነው? እንዲፈወስ የቀረበ በሽተኛ ነው? ለበረከት የመጣ ደጅ ጠኚ ነው? እንዴትስ ነው የተበጠበጠው እምነት ከ‹ ውኃ ለሁሉም› አስተሳሰብ ጋር የሚሄደው?
ሌላው አስገራሚ ነገር ደግሞ ‹ሰውዬው ጣቱን አስጠጋ እንጂ አልቀባኝም› ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹ ሁሉ የሚያሳዩት ግን ሲቀባዎት ነው፡፡ ደግሞስ ሰውዬው ለመቀባት ካላሰበ እጁን ለምን ወደ እርስዎ ያስጠጋል? ሊባርክዎ ነው? አስቀድማችሁ የተስማማችሁበት ሥነ ሥርዓት ይህንን የማይፈቅድ ከሆነስ እንዴት እጁን ወደ እርስዎ አስጠጋ? ‹እጁን አስጠግቶ ነበር› ካሉን ደግሞ ከተበጠበጠው እምነት እንደ እርስዎ ጠቅሶ ነበር ማለትዎ ነው? ለመሆኑ ኦርቶዶክሳዊ ክህነት የሌለው ሰው ከእምነት ጠቅሶ ሌላውን ሰው መቀባት፣ ያውም ቆሞሱን ይችላልን?
ሥነ ሥርዓቱ ሲከናወን ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደነበሩ አባም ነግረውናል፣ ፎቶውም አሳይቶናል፡፡ ምን ወስነው? ምን ሊያደርጉ ሄዱ? ውኃ ለሁሉ እንዲዳረስ ሊጸልዩ ወይስ ውኃ ለሁሉ እንዲዳረስ እምነት በውኃ ሊበጠብጡ? ለመሆኑ ይህንን እንዲያደርጉ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይፈቅድላቸዋል? ወይስ ሥልጣን ከቀኖና ስለሚበልጥ?
አባን ለዚህ ሁሉ ነገር የዳረጋቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ መርሕ እየተጣሰ ስለመጣ ነው፡፡ ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎችን እናንሳ፡-
ቤተ ክርስቲያናችን ኢኩሜኒካል ግንኙነትን የምትመራበት ፖሊሲና ደንብ አላት?
ቤተ ክርስቲያናችን ኢኩሜኒካል ግንኙነቶችን የምታከናውንበት ተቋምስ አላት?
የሁለቱም መልስ የላትም የሚል ነው፡፡ በሌሎች እኅት አብያተ ክርስቲያናት የኢኩሜኒካል ግንኙነትን የተመለከተ ፖሊሲና ደንብ ሲኖዶሱ ያጸድቃል፡፡ ከነማን ጋር ምን ዓይነት ውይይት ይደረጋል፣ ምን ዓይነት ውይይቶች በምን ደረጃ (በሊቃውንት፣ በጳጳሳት) ይደረጋሉ፣ ስምምነቶች እንዴት ይጸድቃሉ፣ የጸደቁት እንዴት ለሕዝብ ይገለጣሉ፣ የጸደቁትን እንዴት መተግበርና መከታተል ይቻላል፣ ስምምነት እስኪደረስ ድረስ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ምን ዓይነት ግንኙነቶች ይኖሩናል? በምን በምን እንተባበራለን? በየደረጃው ያሉ አካላት (ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን) ያላቸው ድርሻ ምንድን ነው፣ የሚሉትን የሚወስን የፖሊሲ መዝገብ አላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ግን ይህ ፖሊሲ የላትም፡፡ ፖሊሲውንም መሠረት አድርጋ የምትመራበትን ሕግ አላጸደቀችም፡፡ ስብሰባ ስትጠራ መሄድ ብቻ ነው፡፡
በሌላ በኩልም የኢኩሜኒካል ግንኙነትን የሚያካሂድ፣ ባለሞያዎችን የሚሰባስብ፣ መረጃዎችን የሚመዘግብ፣ በዓለም ላይ የሚደረጉ የኢኩሜኒካል ግንኙነቶችን የሚከታተል፣ ግንኙነቶቹን በፖሊሲውና በደንቡ መሠረት የሚመራ፣ ስሕተቶች ሲፈጠሩም የሚያርም ተቋምም የለም፡፡ ያለው የውጭ ግንኙነት መምሪያ ነው፡፡ እርሱ ደግሞ ብዙ ጊዜ እንግሊዝኛ ይችላሉ ተብሎ ስለሚታሰብ አሜሪካ በኖሩ ሰዎች የሚመራ ነው፡፡ የኢኩሜኒካል ግንኙነት ግን የአሜሪካን እንግሊዝኛ በመቻል ብቻ የሚሠራ አልነበረም፡፡ የውጭ ግንኙነት መምሪያው ወደ ውጭ ለሚሄዱ ሰዎች ሂደቶቻቸውን መከታተል፣ ከውጭ አጥቢያዎች ጋር ‹መገናኘት› የሚላኩ ሰዎችን መላክ እንጂ ራሱ እንኳን የሚመራበት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ያለው አይመስልም፡፡
ይህ በሆነበት ሁኔታ አባ ኃይለ ማርያም ያንን ነገር ቢያደርጉት የሚገርም አይደለም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በዕለቱ የነበሩት ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን መርሕ እየጣሱ ያዘዟቸውን ነው የተገበሩት፡፡ እርሳቸው ቢሆኑም ግን ፖሊሲና ሕግ በሌለበት ይህንን ተግባር ከሚያከናውኑ ‹ዱክትርናቸውን› ተጠቅመው ፖሊሲውና ሕጉ እንዲዘጋጅ ቢያደርጉ ኖሮ ይመሰገኑ ነበር፡፡ ነገ ጳጳስ የሚሆኑትን አባት ማንም እየተነሣ እጁን ወደ ግንባራቸው አይልክም ነበር፡፡ በሃይማኖት መሥመር የበላይ ያመጣውን ሁሉ በእምነት መመርመር ያስፈልጋል፡፡ የበላይ አዞኝ ነው ብሎ ቀኖና መጣስና እምነት ማፋለስ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
በጉባኤ ኬልቄዶን የክህደቱን ውሳኔ አልቀበልም ያለው ዲዮስቆሮስ በሮም ቤተ መንግሥት ተጠርቶ ‹ለምን አትቀበልም? ልዮንኮ አለቃህ ነው› ሲባል ‹ልክ ነው ልዮን አለቃዬ ነው፡፡ ነገር ግን ከእምነቱ ሲወጣ አልቀበለውም፡፡ ሳጥናኤልም ለቅዱስ ሚካኤል አለቃው ነበር፤ ከእምነቱ ሲወጣ ግን አልተቀበለውም› ያለውን እዚህ ላይ ማስታወሱ መልካም ነው፡፡ አሁንም ቤተ ክርስቲያናችን ኢኩሜኒዝምን የተመለከተ ፖሊሲና መመሪያ ካላወጣች፣ ጠንካራ ተቋምም ካልመሠረተች ነገ ከዚህ የባሰ ነገር ማየታችን አይቀርም፡፡ ከዚህ ተግባር የተማርነው ግን የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ በነቃ ኅሊና መከታተል እንዳለብን ነው፡፡
ያሳወቁንን እያመሰገንን፣ ያላወቅነው እንዲገልጥልን እንለምናለን፡፡
ይላል ዲን ዳንኤል ክብረት ከአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ፣ ማነህ እዚያ ጋር ተረኛ ቀጥል ። አሳየው ላላየው ። አከተመ ።
ያዝ እንግዲህ. ምድረ ግሪሳ ሁላ.!
"እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ይህንን ጦማር ዲን ዳንኤል ጻፈው መግቢያውንና ወቀሳውን እኔው ራሴ በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 ደግሞ የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 16/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ ።

No comments:

Post a Comment

አዝማሪ ትዝታው የራሱንና የቤተሰቡን የአንገት ማዕተብ ከበጠሰ ቆየ ።

ግሪሳ ትዝታው ( ሉንጎ )  መቅሰፍት ሊወርድበት  ነው ★ ★ ★ ✔  Share ~ Comment ~ Like ~ Tag ★ አዝማሪ ትዝታው የራሱንና የቤተሰቡን የአንገት ማዕተብ ከበጠሰ ቆየ ። ★በኮሎራዶ.! ...