
★★★
የተከበረው የመቅደሳችን ስፍራ
በሁለቱ ኃይለማርያሞች ተደፈረ ።
በሁለቱ ኃይለማርያሞች ተደፈረ ።
" እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥" ማቴ 24፣15


★ደፋሪዎቹ አንዱ መነኩሴ አንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናቸው ።
★ደፋሪዎቹ አንዱ በኢትዮጵያ አንዱ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን መቅደሳችንን ነው የደፈሩት ።
★ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ቅዱስ ሲኖዶሳችን ደክሞት ለሽሽ ብሎ ተኝቶልናል ። አትቀስቅሷቸው ፣ አትረብሿቸው ። ይተኙበት ፣ ይረፉበት ።
★
★
★
★
★
..... ነቢየ እግዚአብሔር ኤርሚያስ እንዲህ ይላል ።" የመቅደሳችን ስፍራ ከጥንት ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው። " ኤር 17፣12 ። አዎ እውነት ነው የመቅደሳችን ሥፍራ ከጥንት ጀምሮ ከፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው ። አሁን ግን ይህ የክብር ዙፋን የሆነ ሥፍራ በዘመናችን ከኢትዮጵያ ማኅፀን በበቀሉ ጉደኞች የተነሳ ከጥንት ጀምሮ ከፍ ያለው የክብር ዙፋን የሆነውን መቅደሳችንን በሚያረክሱ ጉደኞች ተወርሯል ።
ደክተር አባ ኃይለማርያምና ፓትሪያርክ አባ ማትያስ በአዲስ አበባ የሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ድንግል ማርያምን ቤተክርስቲያን እንዲደፈር ሲያደርጉ ፤ በኢየሩሳሌም ደግሞ እነ አባ ፍስሐ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሚስቱና ከአምባሳደሩ ከውጭ ጉዳይ ሚንስትሩና ከሚንስትር ደኤታዎቹ ጋር ከፍ ያለውን መቅደሳችንን በጫማ ጠቀጠቁት ። ይሄ ንቀት ነው ። ይሄ ድፍረትም ነው ። ምን ታመጣላችሁም የሚል መልእክት ማስተላለፋቸውም ነው ።
አሁን ሌላው ድፍረት የተፈጸመው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሱልጣን የኢትዮጵያ ገዳም ውስጥ ሲሆን የድፍረቱ ፈፃሚ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ነው ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከነጫማው በመግበት ቅድስት የተዳፈረው መቅደሳችን ደግሞ በዴር ሱልጣን ውስጥ ከሚገኙት ሁለት ቤተ መቅደሶች መካከል አንደኛው በሆነው በአርባዕቱ እንሰሳ የመድኃኔአለም ቤተ ክርስትያን ውስጥ ነው።
ቦታው የቱሪስቶች መተላለፊያ ቢሆንም መቅደሱ ውስጥ ያውም ምንጣፉ ላይ እንዲህ በድፍረት ከነጫማው መንግሥቱ ኃይለማርያምም ቆመ የሚል አልሰማሁም ። አላነበብኩምም ።
እንደ አንድ የዚህች ታላቅ ሀገርን የመምራት እና አጋጣሚውን የማግኘታቸው ይህን የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ኩራት የሆነን ገዳም መጎበኘት መብትም ግዴታውም ነው ። በዚያ ያለውን የገዳሙን አስከፊ ይዞታ በመጎብኘት ለመፍትሄው ከግብፅና ከእስራኤል መንግሥታት ጋር ተነጋግሮም ለመፍታትም ቢሞክር ቢያስመሰግነው እንጂ አያስወቅሰውም ። ነገርግን የሚጎበኘው ገዳም ህግና ስርዓት መከበር አለበት ።
በገዳ ስርዓት ላይ ተገኝቶ ቡሉኮ መልበሱ ። በሀረሬዎች በዓል ላይ ተገኝቶ የእስላም ቆብ ማጥለቁ ፣ ትግራይም ጎንደርም ተገኝቶ የአካባቢውን ማኅበረ ሰብ ባኅል እንደሚያከብር ያሳየ መሪ ። እንዴት ዛሬ የተከበረውን መቅደሳችንን እንዲህ በጫማው ከእነ ሚስቱ ሊጠቀጥቀው ድፍረት አገኘ ።??? ፕሮቴስታንት መሆኑን አሳይቶ ኦርቶዶክስን ለማዋረድ ፈልጎ ከሆነ በፍፁም ተሳስቷል ።
ልብ እንበል.! እነ አሰግድ ፣ እነ በጋሻው ፣ እነ ያሬድ አደመ የሚደገፉት በእነዚህ ሰዎች ነው ። አከተመልን ።
አሁን ይህንም ፖስት አይቶ የፓርቲው ክብር ከእግዚአብሔር ክብር የሚበልጥበት ፤ እኔንም ዘረኛ ፣ ምናምን የሚለኝ ጉደኛ አይጠፋም.!!
እናም ይህን ሁሉ ድፍረት ባየን ጊዜ ልክ እንደ መዝሙረኛው ዳዊት እንዲህ እያልን ወደ እግዚአብሔር እንጮሃለንለን ።
1፤ አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፤ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ፥ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት።
. . .
4፤ ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና ዘበት።
4፤ ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና ዘበት።
. . .
10፤ አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ያወቁ፤
10፤ አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ያወቁ፤
. . .
12፤ አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።
12፤ አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።
ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው ። ባለቤቱም ወይዘሮ ሮማን እንደዚያው ። በእውነት አቶ ኃይለማርያም መስጊድ ቢገቡ እንዲህ በድፍረት ይገቡ ነበርን.?? ወሮ ሮማንስ ሰዐውዲ አረቢያን ቢጎበኙ እንዲህ ሆነው ተገላልጠው በድፍረት ከነጫማቸው በቤተመቅደስ ይታዩ ነበርን. ???
አቶ ብርሃነ ፣ አምባሳደሩ አቶ ፣፣፣፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ፤ ሦስቱም ጥብቅ ሃይማኖተኛ ከሆነው ከትግራይ ሕዝብ ማኅፀን የፈለቁ ሰዎች ናቸው ። እናም ምን ይሰማችሁ ይሆን እንዲህ ኦርቶዶክስን ስታዋርዱ ።
ለነገሩ.! አቶ ስብሐት ነጋ በግልፅ ተናግረዋል ። ቀደም ብለውም ነግረውናል ። የኦርቶዶክስ ሃይማኖትና የአማራውን የጀርባ አጥንት አድቅቀን ሰብረነዋል ።
ይሄው እየሰበሩት ነው ።
በአዲስ አበባ በሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ውስጥ ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስና ዶር አባ ኃይለማርያም መቅደሳችንን በእምነት በማይመስሉን ሰዎች እንዲደፈር አደረጉ ። መቅደሳችን በመናፍቃን ጫማ ተጠቀጠቀ ፣ ንዋየተ ቅዱሳኑ ወጥተው በሴት ፓስተሮች ጭምር እንዲባረኩ ተደረገ ። እናም እኛም ብንጮህ ሰሚ የለም ሳንል ይኸው እስከዛሬ እንጮሃለን ።
አሰግድ ሳህሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ቢወገዝም ፤ የውግዘቱ ደብዳቤ በቅዱስ ፓትሪያርኩ አንደበት ተነብቦ በመላው ዓለም ለሚኖሩ ክርስቲያኖች በቴሌቭዥን ቢታይም " አቶ አባይ ፀሐዬ " ማን አባቱ ነው የሚያወግዘው ብለው በነፃነት ፤ ጥበቃ ተደርጎለት እንደልቡ እንዲፊነጭ ማድረጋቸው ነው እየተነገረ ያለው ። እንዲያውም ከዚህም በላይ ፓስተር አሰግድ በመንግሥቱ ድጋፍ የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን ፕሮግራም በናይል ሳት ከመጪው ሐምሌ አንድ ጀምሮ ሊጀምር እንደሆነ በይፋ ተናግሯል ።
ይህ ሁሉ ሲሆን በተለይ በሥርዓቱ ውስጥ የምትገኙ ለትግራይ ልጆች መልእክቴ በቅንነት ይድረሳችሁ ።
መቀሌ በተሃድሶ እየታመሰች ነው ። አዲግራት ምን አይነት ጭንቅ ውስጥ እንዳለች በነገው እለት በምለቀው ፖስት ማየት ትችላላችሁ ፣ ሽሬዎች ከተሃድሶ ጋር የሞት ሽረት ትግል ውስጥ መሆናቸው የሚታይ ነው ። አክሱም የችግር ጭምጭምታ እየተሰማ ነው ። አሁንም ይህ ሁሉ እየሆነ እያያችሁ የፓርቲ ፍቅር ከሀገርና ከሃይማኖት በላይ ሆኖባችሁ ፤ ውስጣችሁ እየሆነ ባለው ነገር ማረሩ እያስታወቀ በተግባር ግን ጥፋቱን እያጠፉ ያሉት ከፓትሪያርኩ ጀምሮ እስከ የመንግሥት የሥልጣን ስፍራ ያሉት የሀገራችሁ ልጆች የሚፈፅሙትን ድፍረት የተሞላበት ድርጊት እያያችሁ ዝምታን በመምረጣችሁ ስለ እውነት ከልብ አዝናለሁ ።
እንዲያውም ከዚህ በከፋ ሁኔታ በስመ ደኅንነት ለአሰግድም ሆነ ለውርጋጡ ከፍ ያለው ቱፋ የጥበቃ አገልግሎት እየሰጡት ጭምር መሆኑን ስናይ እኔ በበኩሌ እጅግ አድርጌ አዝናለሁ ።
ኢትዮጵያንም ሆነ ተዋሕዶን የሚታደግ እግዚአብሔር ነው ። አሁን ጊዜው በሰጣችሁ ሁሉን የማድረግ ስልጣን ተጠቅማችሁ ሀገሪቱንም ሆነ ቅድስት ቤተክርስቲያንን መታደግ ስትችሉ ፤ነገር ግን በቸልተኝነት ፣ በፍርሃት ፣ በይሉኝታ ተሸብባችሁ ዝም ብትሉ የቅድስት ቤተክርስቲያን አምላክ ይፋረዳችኋል ። ከፍያለው እንኳ ከአቅሙ ሽጉጥ ታጥቆ እንዲዞርና ለዘመድኩን መረጃ የሚሰጠውን አካል ባገኘው እደፋዋለሁ እያለ እንዲፎክር የልብ ልብ ስትሰጡት ሳይ አፈርኩባችሁ ።
በአኔ እምነት ሀገሬንም ሃይማኖቴንም የሚታደግ ሰው እግዚአብሔር ሳያስነሳ አይቀርም ። ትርፉ ትዝብት እንጂ ስለ እውነት እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለሀገሬ መዳንን ከሌላ ሥፍራም ቢሆን ማምጣቱ እንደሁ አይቀርም ። መርዶክዮስም እንዲህ ነበር ያለው ።
" መርዶክዮስም አክራትዮስን። ሂድና ለአስቴር እንዲህ በላት አለው። አንቺ። በንጉሥ ቤት ስለ ሆንሁ ከአይሁድ ሁሉ ይልቅ እድናለሁ ብለሽ በልብሽ አታስቢ።
.....በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? "
እግዚአብሔር ይመስገን ቁጥራቸው ጥቂት ሆነብኝ እንጂ ከእኔ ጋር የሚታገሉ የትግራይ ልጆች የሉም ማለቴ ግን አይደለም ። በሽሬ ፣ በአክሱም ሆነው ፣ በመቀሌና በአዲግራትም ተቀምጠው አይዞህ ዘመዴ ፣ ከአንተው ጋር ነን የሚሉ ወንድሞች አሉ ። እግዚአብሔር እናንተን አያሳጣን ፣ ሺህ ያድርጋችሁ ።
ለዛሬ አበቃሁ.! ።
"ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ፤ ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ሁሉ ፤ ክብሩን አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 ደግሞ የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 28/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ ።
ግንቦት 28/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ ።
No comments:
Post a Comment