Tuesday, 6 June 2017

አዝማሪ ትዝታው የራሱንና የቤተሰቡን የአንገት ማዕተብ ከበጠሰ ቆየ ።

ግሪሳ ትዝታው ( ሉንጎ )  መቅሰፍት ሊወርድበት  ነው
Image may contain: 4 people, people smiling, outdoor

★ ★ ★
 Share ~ Comment ~ Like ~ Tag
★ አዝማሪ ትዝታው የራሱንና የቤተሰቡን የአንገት ማዕተብ ከበጠሰ ቆየ ።
★በኮሎራዶ.! አለ ነገር.! የሚሰማ.! የሚነገርም አለ ነገር ።
 በጀመሪያ መልእክቱን በደንብ አንብቡትና በኮመንት ገባ ገባ በሉላቸው!!
★ እንዲህ ያለውን ጦማር Share ~ Share  ማድረግ በፀረ ተሃድሶው ትግል እጅግ ወሳኝ ነገር ነው ። መረጃው ብዙ ሰው እጅ ገብቶ የመወያያ አጀንዳ ይሆናል ፣ ብዙዎችንም ያነቃል ፣ ጥንቃቄም እንዲወስዱ ያደርጋልና ነው። Comment መስጠትም ሌላው ወሳኝ ነገር ነው ። ደግሞ አስተያየት ስትሰጡ አትልመጥመጡ ፣ አትቅለስለሱ ፣ ወንድ ወንድ የሚሸት አስተያየት ስጡ ።
★ ሚሊዮኖች የእኔን ፔጅ ያነባሉ ፤ በተለይ አገልጋዮችና ወግ አጥባቂ ምዕመናንን እንደ ጉድ ያነቡኛል ። ነገር ግን ጦማሩን ሼር አያደርጉም ፣ ኮመንት አይሰጡም ። ምክንያት ሲባሉ " ዘመዴ በጽሑፎቹ ውስጥ ግሪሳ ፣ በጥራቃ የሚል ቃል ስለሚጠቀም አናደርገውም ይላሉ ። እነዚህ አስመሳዮች ናቸው ። እርቃኗን የቆመች ሴት ፎቶ ሼር እያደረጉ የእኔ ግሪሳ የሚል ጽሑፍ ዘገነናቸው ። እነዚህ የፌስቡክ ላይ ክርስቲያኖች ፣ ናቸው ። የፌስ ቡክ ላይ ጧሚ ፣ ጸሎተኛና ትሁቶች ። እናም እንኳን ሼር አለማድረግ አይደለም ለምን ሳያነቡት አይቀሩም ። ምድረ በጥራቃ ሁላ.!!!
አሁን ወደ ግሪሳው አዝማሪ ትዝታው( ሉንጎ ) ዜና እናልፋለን ። መልካም ቆይታ.! ።
......በመጀመሪያው የ1997 ዓም ምርጫ ወቅት የፖለቲካው ትኩሳት በጋመበት ሰዓት አዲስ መንግሥት ይመጣል በሚል ተስፋ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እያለ እሱን ራሱን ሉንጎን ጨምሮ 11 ልጆች በመሆን ኢህአዴግን በመቃወም ለቅንጅት ድጋፍ በመስጠት ፤ በድፍረት የወያኔን አገዛዝ በመቃወም ለተባበሩት መንግሥታት ፣ ለአፍሪካ ኅብረት ፣ ለአረብ ሊግ ፣ ለአሜሪካና እንጊሊዝ መንግሥታት ሳይቀር የተቃውሞ ደብዳቤ ካስገቡት ግለሰቦች መካከል የነበረ ግለሰብ ነው ። ትዝታው ( ሉንጎ)
እኔ ራሴን ጨቅጭቀውኝ ድርጅቴ ድረስ በመምጣት " ዘመዴ!! "ኢህአዴግን ተቃውመን መግለጫ የምንሰጥበት ሚዲያ ፈልግልን ባሉኝ መሠረት በወቅቱ ተነባቢ ጋዜጣ የነበረችውን " ነፃነት " የተባለችው ጋዜጣ ላይ መግለጫ እንዲያወጡ ጋዜጠኛ " ደረጀን በመጥራት ኦዳ ራመት በተባለ ሆቴል ውስጥ በግዋሻው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሰጥ አስደርጌው ነበረ ። በወቅቱ ከ" ንክር ፋራና ሰገጤ የገጠር ልጅነት በመውጣት በዝግመተ ለውጥ ወደ አራድነት መጠጋት የጀማመሩበት ወቅትም ስለነበር " እርዳን አግዘን " ባሉን ነገር ሁሉ ሳግዛቸው ነበር ።
የቅንጅት አሸናፊነት ሲከሽፍ እነ ትዝታው ሉንጎ ከመንፈሳዊ ኮሌጅ በደብዳቤ ተባረሩ ። ወዲያውም የሚበሉት ሲያጡ በአዋሽ ባንክ አካውንት ከፍተው እርዳታ መለመን ጀመሩ ። የሚገርመው የባንክ አካውንቱ እስከዛሬ አልተዘጋም ። የዚህን ጊዜ ነው ኢህአዴግን መቃወም እንጀራ እንደሚያስገኝ የተረዱት እነ በግዋሻው ወዲያውኑ ከፓስተር መለሰ ወጉ የተገለበጠውን " የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች " የምትል አነስተኛ ፓፍሌት መሳይ የመጽሐፍ ስም የተሰጣት ፓፍሌት በማሳተም አገር ምድሩን አንቀጠቀጡት ። መጽሔቷ በበጋሻው ስም ትውጣ እንጂ ትዝታው ሉንጎም የበረሃ ጓዱ ስለነበር ጥቅሙ የጋራቸው ነበር ። በወቅቱ በፓፍሌታ የተናደደው ወያኔ በጋሻውን ይዞ ማእከላዊ አሰረው ።
ያኔ ነው እኔም ጌቱ ከሚባለው የአብ መዝሙር ቤት ባለቤት ጋር በጋሻውን ለመጠየቅ ማእከላዊ ስሄድ የበጋሻውን እናት ለመተዋወቅ የበቃሁት ። የበጌ እናት በንዴት ኒያላ የተባለውን ሲጋራ በላይ በላዩ እያጨሱ " ተው ብዬህ ነበረ ። አልሰማ አልከኝ ፣ ውቃቢዬ አውሊያዬ ነግሮኛል ። እረፍ ብዬህ ነበር እያሉት ሲቆጡት የደረስኩት " የበጌ እናት በለአውሊያ መሆናቸውን እና በቤታቸው ለብዙዎች የሚፈርዱ በለዛር ሴት መሆናቸውን የዚያን ቀን ነበረ በአይኔ ያየሁት በጆሮዬም የሰማሁት ። አቤት በግዋሻው እንዴት እንደአበደ ። " ማን ጠይቂኝ አለሽ? ፣ ማን ነይ አለሽ? ፣ ሁለተኛ አትምጪብኝ እያለ ሲያለቃቅስ አሳዘነኝ ። እናቱን እንኳ ከአጋንንት አሰራር አውጥቶ ወደ ህይወት መንገድ ያልመለሰ ሰባኪ ያውም ሳይማር መጋቤ ሀዲስ የሚባል ማዕረግ የተሸከመ ፍልጥ እና ዥልጥ ያለ " ሀ " ገደሉ የሆነ ሰው ነው እንግዲህ ሌሎችን አስተምሬ መንግሥተ ሰማያት ካላስገባሁ ሞቼ እገኛለሁ የሚለው በጥራቃ ።
እንግዲህ ከዚህ ከማዕከላዊ እስር በኋላ ነው በግዋሻው ከተቃውሞ ትእቢቱ ተንፍሶ በመውጣት ከመቅስፈት ትዝታው ሎንጎን ጨምሮ ብዙዎቹ የደኢህዴን ኢህአዴግ ደጋፊና አባል ለመሆን የበቁት ። ሉንጎ ከመናፍቁ " አባ " ሰረቀ ጋር በመሆን ከኢህአዴግ የተሰጣቸውን ተልእኮ ለማስፈፀምና ማኅበረ ቅዱሳንን የማፍረስ ፕሮጀክት ከበጋሻው ጋር ሓለፊነት ወስዶ ይንቀሳቀስና እንዲንቀሳቀስ የተደረገ ግለሰብ ነበር ።
የሁሉም መሪና ጠርናፊ ደግሞ በፊት የማኅበረ ቅዱሳን አባል ሆኖ ራሱ ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲሰልል ኃላፊነት ወስዶ የነበረውና አሁን በሀገረ አሜሪካ የሚገኘው ቀሲስ ሰሎሞን ሙልጌታ ነበር ። ዱባይ ላይ ቤተክርስቲያን እንዲከፈት ያደረገ ፣ የሚሊንየሙ ጉባኤን ከጀርባ በመሆን ለያሬድ አደመ ትእዛዝ በመስጠት በቤተክርስቲያን ስም ምእመናን ገንዘባቸውን እንዲዘረፉ ያደረገው ግለሰብ ነው ሰሎሞን ማለት ። ይሄው ሰሎሞን ሰሞኑን ዘማሪ ወንደሰን በቀለና ዲን ዳዊትን ይዞ ሲያለቃቅስብኝ መክረሙን አይቻለሁ ሰምቻለሁም ። ወንዴና ዴቭ ፣ አካሉና እስክንድር በጊዜ ሚናችሁን ለዩ ። መረጫጨት ከተጀመረ ለእናንተ ጥሩ አይመጣም ።
በከፍተኛ የስኳር ህመም የሚሰቃየው ግሪሳ ትዝታው (ሉንጎ ) በኢትዮጵያ በተለይ በዲላ ከተማ የማኅበረ ቅዱሳን ቢሮዎችን ለጊዜውም ቢሆን እንዲታሸጉ ያደረገም ግለሰብ ነው ። የድምፅ ቅጂውንም" አርማጌዶን " በተሰኘው ቪሲዲዬ ላይ ተመልከቱት ። እንዲህ እንዲህ እያለ እንደምንም ብሎ በሴት ጀርባ ላይ ተንጠልጥሎ " ገሌ " በመሆን አሜሪካ የገባው ሉንጎ ፤ አሜሪካ እንደገባ ወዲያውኑ የወያኔነት ካባውን አውልቆ የስደተኛውን ሲኖዶስ በመቀላቀል ዋነኛ የወያኔ ተቃዋሚ ሆኖ አረፈው ። በኢትዮጵያ ሳለ እኔን ለመደበቅ ሲል የሟቹን ፓትሪያርክ የአብነ ጳውሎስን ኃውልት አሰሪ ኮሚቴ የነበረ ሰው አሁን ደግሞ በአሜሪካ ከአቡነ መርቆሬዎስ ሥር ተለጥፎ ያሽካካልኛል ። ምደረ አረፊ ፖለቲከኛ ነኝ የሚለውን የድሮ አራዳ ሁሉ ይጫወትበታል ።
አሜሪካን ከገባ በኋላ የውጪውን ሲኖዶስ እንደ መደበቂያ ሽፋን በመጠቀም ያለፉትን ጥቂት ዓመታት በዴንቨር ኮሎራዶ ደግማዊት ግሸን ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ መሽጎ የስህተት መርዙን በተናጥል በየግለሰቦች ላይ በመዝራት ፤ እሱ ከመምጣቱ በፊት ፍቅር በፍቅር የነበሩትን ግለሰቦች ሆድና ጀርባ አድርጓቸው ቆይቷል ። በተለይ አሁን ቤተክርስቲያኒቱን የሚያስተዳድሩት አባት ጥበብ በተሞላበት አካሄድ ውልፍት እንዳይል ሰቅዘው በመያዝ አላላውስ ብለው በጥበብ ያዙት እንጂ ልጁ ዋና አላማው የቤተክርስቲያኒቱን አስተዳደር በመያዝ የግሪሳዎቹ መፈንጫ ለማድርግ ነበር ዋና ፍላጎቱ ። በዚህ በኩል ቦርዱ ፊት በለመስጠት ያደረገው በጎ ነገር ያስመሰግነዋል ።
የቤተክርስቲያኒቱ ቦርድ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ለግሪሳው ጥብቅና በመቆም ይከራከርለት የነበረ ብቻ ሳይሆን ከ 3500 ዶላር በላይ የደምወዝ እየከፈለው አንደላቅቆ ያኖረው የነበረ ቢሆንም ዘንድሮ ግን አሁን የአሜሪካው ስደተኛው ሲኖዶስ በደብሯ ላይ ስብሰባ ማድረጉን ተከትሎ አጋጣሚውን በመጠቀም የምንፍቅና ሸቀጡን ለማራገፍ በመቋመጥ በይድረስ ይድረስ የተዘጋጀና ከየትኛውም የቤተክርስቲያን ዓውደምህረት ሳትወገዝ የተወገደችውን በመናፍቋ ፓስተር " ዘርፌ " አጃቢነት የቀረበ ቀረርቶ በተከበረችው ደብር ስም ለመሸጥና ዶላር ለማጋበስ ቋምጦ የነበረውን ሉንጎ ያደረገውን አሳፋሪና ፍፁም ስግብግብነት የተመላበት ሙከራ በመመልከት ይህን ሸቃጭ ነጋዴ " ቀረርቶህ በደብራችን ውስጥ አይሸጥም " በማለት ቦርዱ ወሽመጡን በጥሶ ጥሎለታል ።
የቦርዱ ውሳኔ የበጋ መብረቅ ያህል የሆነበትና የደነገጠው ሉንጎም በሁኔታው "ፍዝዝ ፣ ቅዝዝ " ከማለትና ጨጓራዬን አመመኝ ብሎ ከመተኛት ውጪ ምንም ምላሽ ያልነበረው ሲሆን የትዝታው ባለቤት ግን ጨርቋን ጥላ ፤ አቅሏንም ስታ ማበድ እስኪቀራት ድረስ ያዙኝ ልቀቁኝ ፣ ምን ሲደረግ ነው የአዝማሪው ባሌ ቀረርቶ የማይሸጠው በማለት አዋራ ስታስነሳ እንደነበር ታይታለች ። ከምር በእጄ የገባውን ቪድዮ ሳይ አሳዘነችኝ ። ለቅዱሳን ክብር አይገባም በማለት ማኅተባቸውን የበጠሱት ባልና ሚስቱ ቤተክርስቲያንን የሚፈልጓት " ለሸቀጥ ማራገፊያነት " ነውም ተብሏል ።
አሁን ከትዝታው ጎን የቆሙት ጥቂት ቤቢ ሲተሮችና የቤተክርስቲያኒቱ ቦርድ ውስጥ ካሉት አባላት መካከል አንዲት ሴት ስትሆን ፤ በተለይ ሴትየዋ በቦርድ ደረጃ የተነጋገሩትን ይዛ በመውጣት ለሉንጎ በመንገር እሱም አድማ የሚመቱ ቤቢ ሲተሮችን በማዘጋጀት እስከአሁን ሲንቀሳቀስ ቆይቷል ። አሁን ግን በትዜ ላይ ጀንበር የጠለቀች ይመስላል ። የሚገርመው ነገር ደግሞ ሴትየዋ ይህን አይነት ድጋፍ ስትሰጠው ባለቤቷ አቶ ታረቀኝ ደግሞ ከቅድስት ቤተክርስቲያን ጎን የቆመ መሆኑ ነው ።
የሚገርመው ነገር የአሜሪካው ሲኖዶስም በዘንድሮው ስብሰባው በማጠቃለያው ላይ በሰጠው ውሳኔ በ6 ተኛው ተራ ቁጥር ላይ " ተሃድሶ የሚባል አዲስ ሃይማኖት መጥቷልና " ተጠንቀቁ በማለት በድፍረት ሲናገር ተደምጧል ። ተሃድሶ የሚባል የለም ባዩን ግሪሳ ትዝታውን በተቀመጠበት ውኃ የቸለሰበት ውሳኔ ሲሆን ፣ በአንፃሩ ደግሞ ተሃድሶ ያስፈልጋል ባዮቹን አባ ወልደትንሳኤንና አባ ገብረሥላሴን ጳጳስ አድርጎ በመሾም ፣ እነ ልኡለቃልን ፣ እነሽታ ቡዝዬን ፣ እነ እንዳልካቸው ዳኘውንና ፣ እነ ፓስተር መላኩን አዝሎ እየዞረ ስለ ተሃድሶ ቢያወራ ሰሚ የሚያገኝም አይመስልም ። እርግጥ ነው ፤ ይፋ አይውጣ እንጂ በዘንድሮው ስብሰባቸው " ለአባ ወልደትንሣኤ አያልነህ " ከባድ የተባለ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ውስጥ ውስጡን ይወራል ። ለዚህም ነው በዴንቨሩ ስብሰባ አባ ወልዴ ድምጻቸውም መልካቸውም ድራሹ የጠፋው የሚሉ ሰዎች የበዙት ።
አሁን ለምድረ ተሃድሶ ሁላ አሜሪካ ውስጥ ይሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የትም ይሁን የት በሁሉም ቦታዎች መንገዶች ሁሉ ዝግ ሆነውባቸዋል ። የሚያስተምሩበት መድረክ ተነጠቀዋል ። እሰከ ዛሬ ያለ ከልካይ ሸቀጣቸውን ያራግፉበት የነበረው ዓውደምህረት ዝግ ሆኗል ። የትዝታው ዘፈን በራሱ በፕሮቴስታንቶችና የንግድ ድርጅቶች ውስጥ በይፋ መሸጥ ተጀምሯል ። ዴንቨር ኮሎራዶ የፕሮቴስታንቶች ጸጉር ቤት ውስጥ ለሽያጭ መቅረቡ ታይቷል ። እናም አሁን ሁሉም ባንኗል ። ያልባነነው ደብሯ የቦርድ አስተዳደር ብቻ ነው ።
ወይዘሮ ስፍነ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሊቀንበር ናት ። የትዝታውም ድብን ያለች ቲፎዞም ነበረች ። ኋላ ላይ ግን እየቆየች ስትመጣ ነገር ዓለሙ ሁሉ ተገለጠላት በተለይ የእመቤታችንን መዝሙር እንዲዘምር ፤ ልጆቹንም እንዲያስጠና የምትመክረውን ምክር ባለመስማት ለእመቤታችን አልዘምርም ካላት ጊዜ ጀምሮ በአንድ ጊዜ እሳትና ጭድ ሆነው ከርመዋል ።
አሁን ያበጠ ነገር የሚፈነዳ ያለ ይመስላል ። በውስጥ መስመር ከደብሯ እንደሚደርሱኝ መረጃዎች ከሆነ የደብሯ የበላይ ጠባቂ አቡነ ናትናኤል የተባሉት አባት ሉንጎን ጉድ ሳርተው መላው ዓለም ላይ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያንን ጮቤ ያስረግጣሉ እየተባለም ነው ። ሉንጎ ሉቡ ተራራ ነው ። ከደብሯ ቢባረር ጥቂት የደቡብ ልጆችና ቤቢ ሲተሮች ቢከተሉት እንጂ እሱን ተከትሎ የሚወጣ አንድም ሰው አይኖርም ።
የመረጃ ምንጮቼ እንደሚሰጡኝ መረጃ ከሆነ የቤተክርስቲያኒቱ ሽማግሌዎች እጅግ ጠንካራ ሽማግሌዎች መሆናቸው ይነገርላቸዋል ። በሃይማኖት ቢሉ በሀገር ፍቅር የሚታሙ አይደሉምም ይባላል ። እነ አቶ ጥላሁን ፣ ዲን ዮሴፍ ፣ አቶ ታሪኩ ፣ አቶ ሞላ ፣ አቶ ባዬ ፣ አቶ ናርዶስ ፣ አቶ ዳዊት ፣ አቶ ለገሰ ፣ ወጣት ነብዩ ፣ አቶ ለይኩን ፣ አቶ ኤፍሬም እና ዶር አሰፋን ፣ የያዘው ቦርድ እስከዛሬ ክፉ ደጉን አብረው ያሳለፉትን ምእመናን ብሶትና ሮሮ ሳይሰማ ጆሮውን ደፍኖ ለአንድ ተራ መናፍቅና ፀረ ማርያም ወንበዴ ጥብቅና በመቆሙ ብዙዎች ሲያዝኑ ኖረዋል ። አሁን ግን አለ ነገር እየተባለ ነው ።??? አለ ነገር.??
በመጨረሻም አዝማሪ " ትዝታው" ከዚህ በፊት እኮ ለእመቤታችን ዘምሯል ፤ እንዲያው ምን ነክቶት ነው ብለው ለሚሟገቱ " ምስኪኖች " አዎ ዘምሯል ። ምልጃዋንም አሳምሮ ዘምሯል ይሄ ሁሉ እውነት ። ነገር ግን አሁን አዝማሪው የእመቤታችንን ስም ማንሳት እንደነውር መቁጠር ከጀመረ ቆየ ። በፊት ስለ እመቤታችን ዘመረ ከተባለው ቀረርቶ መካከልም እስቴ አንዱን ጋብዣችሁ እንሰነባበት። "
ወደስኒ ካልሽኝማ " ።
★★ ★
ወድሰኒ ከልሽኝማ
አመስግነኝ ካልሽኝማ
ይልና አዝማሪ ትዝታው ፤ እንዲህ ይደረግ ፤ ምስጋና አምሮኛል ካልሽኝ ፤ መመስገኑንም ከፈለግሽ ፣ እናም ካስቸገርሽኝ ፤ የግድም ብለሽ ወጥረሽ ከያዝሽኝ ፣ ጭቅጭቅም ካደረግሽኝ እንግዲያው እኔ እንዳመሰግንሽ በቅድሚያ ማሟላት ያለብሽን ልንገርሽ ይላታል ደፋሩ ሉንጎ እመቤታችንን ። ለቅዱስ ኤፍሬም ተደረገ የተባለው እውነት ከሆነና ፤ አሁንም ልክ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም እኔም እንዳመሰግንሽ ከፈለግሽ ፦
፩ኛ፤ በደመና ውረጂና
፪ኛ፤ የእሳት አትሮንስ ይዘርጋና
፬ኛ፣ ላመስግንሽ እንደገና ፤
ያለበለዚያ በዚህ ስምምነታችም መሰረት ለቅዱስ ኤፍሬም አደረግሽ የተባለው ነገር የማይደረግ ከሆነ ስለአንቺ የመዘመር ግዴታ የለብኝም ነው " ፈረንሳይኛው " ።
እናንት የእናት ጡት ነካሾች የገባችሁበት ብትገቡ አልፋታችሁም ። አይደለም አሜሪካ ጠፈር ላይ ብትወጡ እንዲሁ በዋዛ አልለቃችሁም ። ንስሃ ትገቡ እንደሁ ብዬ በብርቱ ጠበቅኳችሁ እናንተ ግን ባሰባችሁ እንጂ የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል የመጸጸት ነገር አላሳያችሁም ። ስለዚህ አልፋታችሁም ። ምን ያህል በእናንተ ላይ የእናንተን የውስጥ አንጀት ጉበት ገልብጬ ለህዝቡ ለማሳየት ዋጋ እንደከፈልኩ ልባችሁ ያውቀዋል ።
★ ሀገሬን ★ ቤተሰቤን ★ ልጆቼንና ጓደኞቼን አጥቼማ ያለውጤት ዝም ብዬ የምቀመጥ አይምሰላችሁ ። ወዳጄ ትእዛዙ ከላይ ነውና አንላቀቃትም .!! ። የማንንም ድጋፍ አልሻም ። የሲኖዶስ ውግዘትም አልጠብቅም ፤ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርጌ፣ የብርሃን እናት ወላዲተአምላክን ይዤ ፣ በቅዱሳኑ ጸሎትና ምልጃ እየታገዝኩ አፈር ከድሜ ማስጋጥ እንደሁ አያቅተኝም ። ሲያዩዋችሁ ለተመልካች ጎልያድ ብትመስሉም እናንተን አጋድሞ ከ " ተዋሕዶ " ትከሻ ላይ ለማራገፍ የዳዊት ጠጠርና ወንጭፉ በቂ ነው ። አለቀ ። አራት ነጥብ ።
ማሳሰቢያ.! በውጪው ሲኖዶስ ሥር ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ ። ወያኔም መውደቁ ፣ አንድ ቀን ታሪክ መሆኑ አይቀርም ። በወያኔ አኩርፋችሁ እንጂ እምነታችሁ ያው የጥንቱ የጥዋቱ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ መሆኗ ይታወቃል ። ነገ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ፤ በቃችሁ ሲለንም አንድ መሆናችን አይቀርም ። ጊዜው ሩቅ እንዳይሆን መጸለይም አለብን ። እናም ገና ለገና እላይ ያሉት የሃይማኖት አባቶች ተጣልተዋል ፣ የሚታረቁም አይመስልም በሚል ሰበብ የማንም ልቅምቃሚ መናፍቅ መጫወቻና መጠራቀሚያ መሆን የለባችሁም ። ተአምረ ማሪያም የማያነቡ ፣ ሴቶችን ታቦት ማየት ትፈልጋላችሁ ወይ እያሉ በድፍረት ከመንበሩ ላይ ወስደው ለማሳየት የሚሞክሩ ፣ በሥጋወ ደሙ የሚያላግጡ ፣ ሴቶችን ታቦቱ ያለበት መንበሩ ድረስ አስገብተው ጽዳት እንዲያፀዱ የሚያደርጉ ግልፅ መናፍቅ የሆኑ ግለሰቦችን ልትቃወሙ ይገባል ። የምንለያይባቸው ብዙ ሀገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ቢኖሩም በእምነታችን ግን አንድ ነን ። እናም በአንድነት እንታገላቸው ።
እነዚህ ሰዎች በጣም ብዙ አይደሉም ፣ ነገሩ ነጭ ልብስ ላይ እንዳረፈ ጥቁር ነጥብ ሆነው ጎልተው ይታያሉ እንጂ ብዙ አይደሉም ። ከፈለጋችሁ በፎቶ አሳያችኋለሁ ። ከእነዚህ ሰዎች ራቁ ። በእውነት ራቁ ብያለሁ ። የኢትዮጵያ አምላክ ለእነዚህ አጥፊዎች የእጃቸውን ይሰጣል ፣ እንዲህ አምናለሁ ። እንዲህም እታመናለሁ ። ለዛሬ አበቃሁ ።
በቀጣይ የዘርፌን ወቅታዊ ሁኔታና ያለችበትን አሳዛኝ ህይወት እንመለከታለን ። አከተመ ።
"ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ፤ ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ሁሉ ፤ ክብሩን አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 ደግሞ የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 27/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ ።

የተከበረው የመቅደሳችን ስፍራ በሁለቱ ኃይለማርያሞች ተደፈረ ።

Image may contain: 8 people, people standing and indoor
★★★
የተከበረው የመቅደሳችን ስፍራ
በሁለቱ ኃይለማርያሞች ተደፈረ ።

" እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥" ማቴ 24፣15
በዚህ ፖስት ላይ ገብቶ የሚንበጫበጭ መናፍቅ Block በተባለው ሰይፌ ይቀጣል ። አራት ነጥብ.! ።
 Share ~ Share ~ Share ~ Comment.
★ደፋሪዎቹ አንዱ መነኩሴ አንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናቸው ።
★ደፋሪዎቹ አንዱ በኢትዮጵያ አንዱ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን መቅደሳችንን ነው የደፈሩት ።
★ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ቅዱስ ሲኖዶሳችን ደክሞት ለሽሽ ብሎ ተኝቶልናል ። አትቀስቅሷቸው ፣ አትረብሿቸው ። ይተኙበት ፣ ይረፉበት ።


..... ነቢየ እግዚአብሔር ኤርሚያስ እንዲህ ይላል ።" የመቅደሳችን ስፍራ ከጥንት ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው። " ኤር 17፣12 ። አዎ እውነት ነው የመቅደሳችን ሥፍራ ከጥንት ጀምሮ ከፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው ። አሁን ግን ይህ የክብር ዙፋን የሆነ ሥፍራ በዘመናችን ከኢትዮጵያ ማኅፀን በበቀሉ ጉደኞች የተነሳ ከጥንት ጀምሮ ከፍ ያለው የክብር ዙፋን የሆነውን መቅደሳችንን በሚያረክሱ ጉደኞች ተወርሯል ።
ደክተር አባ ኃይለማርያምና ፓትሪያርክ አባ ማትያስ በአዲስ አበባ የሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ድንግል ማርያምን ቤተክርስቲያን እንዲደፈር ሲያደርጉ ፤ በኢየሩሳሌም ደግሞ እነ አባ ፍስሐ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሚስቱና ከአምባሳደሩ ከውጭ ጉዳይ ሚንስትሩና ከሚንስትር ደኤታዎቹ ጋር ከፍ ያለውን መቅደሳችንን በጫማ ጠቀጠቁት ። ይሄ ንቀት ነው ። ይሄ ድፍረትም ነው ። ምን ታመጣላችሁም የሚል መልእክት ማስተላለፋቸውም ነው ።
አሁን ሌላው ድፍረት የተፈጸመው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሱልጣን የኢትዮጵያ ገዳም ውስጥ ሲሆን የድፍረቱ ፈፃሚ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ነው ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከነጫማው በመግበት ቅድስት የተዳፈረው መቅደሳችን ደግሞ በዴር ሱልጣን ውስጥ ከሚገኙት ሁለት ቤተ መቅደሶች መካከል አንደኛው በሆነው በአርባዕቱ እንሰሳ የመድኃኔአለም ቤተ ክርስትያን ውስጥ ነው።
ቦታው የቱሪስቶች መተላለፊያ ቢሆንም መቅደሱ ውስጥ ያውም ምንጣፉ ላይ እንዲህ በድፍረት ከነጫማው መንግሥቱ ኃይለማርያምም ቆመ የሚል አልሰማሁም ። አላነበብኩምም ።
እንደ አንድ የዚህች ታላቅ ሀገርን የመምራት እና አጋጣሚውን የማግኘታቸው ይህን የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ኩራት የሆነን ገዳም መጎበኘት መብትም ግዴታውም ነው ። በዚያ ያለውን የገዳሙን አስከፊ ይዞታ በመጎብኘት ለመፍትሄው ከግብፅና ከእስራኤል መንግሥታት ጋር ተነጋግሮም ለመፍታትም ቢሞክር ቢያስመሰግነው እንጂ አያስወቅሰውም ። ነገርግን የሚጎበኘው ገዳም ህግና ስርዓት መከበር አለበት ።
በገዳ ስርዓት ላይ ተገኝቶ ቡሉኮ መልበሱ ። በሀረሬዎች በዓል ላይ ተገኝቶ የእስላም ቆብ ማጥለቁ ፣ ትግራይም ጎንደርም ተገኝቶ የአካባቢውን ማኅበረ ሰብ ባኅል እንደሚያከብር ያሳየ መሪ ። እንዴት ዛሬ የተከበረውን መቅደሳችንን እንዲህ በጫማው ከእነ ሚስቱ ሊጠቀጥቀው ድፍረት አገኘ ።??? ፕሮቴስታንት መሆኑን አሳይቶ ኦርቶዶክስን ለማዋረድ ፈልጎ ከሆነ በፍፁም ተሳስቷል ።
ልብ እንበል.! እነ አሰግድ ፣ እነ በጋሻው ፣ እነ ያሬድ አደመ የሚደገፉት በእነዚህ ሰዎች ነው ። አከተመልን ።
አሁን ይህንም ፖስት አይቶ የፓርቲው ክብር ከእግዚአብሔር ክብር የሚበልጥበት ፤ እኔንም ዘረኛ ፣ ምናምን የሚለኝ ጉደኛ አይጠፋም.!!
እናም ይህን ሁሉ ድፍረት ባየን ጊዜ ልክ እንደ መዝሙረኛው ዳዊት እንዲህ እያልን ወደ እግዚአብሔር እንጮሃለንለን ።
1፤ አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፤ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ፥ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት።
. . .
4፤ ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና ዘበት።
. . .
10፤ አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ያወቁ፤
. . .
12፤ አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።
ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው ። ባለቤቱም ወይዘሮ ሮማን እንደዚያው ። በእውነት አቶ ኃይለማርያም መስጊድ ቢገቡ እንዲህ በድፍረት ይገቡ ነበርን.?? ወሮ ሮማንስ ሰዐውዲ አረቢያን ቢጎበኙ እንዲህ ሆነው ተገላልጠው በድፍረት ከነጫማቸው በቤተመቅደስ ይታዩ ነበርን. ???
አቶ ብርሃነ ፣ አምባሳደሩ አቶ ፣፣፣፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ፤ ሦስቱም ጥብቅ ሃይማኖተኛ ከሆነው ከትግራይ ሕዝብ ማኅፀን የፈለቁ ሰዎች ናቸው ። እናም ምን ይሰማችሁ ይሆን እንዲህ ኦርቶዶክስን ስታዋርዱ ።
ለነገሩ.! አቶ ስብሐት ነጋ በግልፅ ተናግረዋል ። ቀደም ብለውም ነግረውናል ። የኦርቶዶክስ ሃይማኖትና የአማራውን የጀርባ አጥንት አድቅቀን ሰብረነዋል ።
ይሄው እየሰበሩት ነው ።
በአዲስ አበባ በሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ውስጥ ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስና ዶር አባ ኃይለማርያም መቅደሳችንን በእምነት በማይመስሉን ሰዎች እንዲደፈር አደረጉ ። መቅደሳችን በመናፍቃን ጫማ ተጠቀጠቀ ፣ ንዋየተ ቅዱሳኑ ወጥተው በሴት ፓስተሮች ጭምር እንዲባረኩ ተደረገ ። እናም እኛም ብንጮህ ሰሚ የለም ሳንል ይኸው እስከዛሬ እንጮሃለን ።
አሰግድ ሳህሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ቢወገዝም ፤ የውግዘቱ ደብዳቤ በቅዱስ ፓትሪያርኩ አንደበት ተነብቦ በመላው ዓለም ለሚኖሩ ክርስቲያኖች በቴሌቭዥን ቢታይም " አቶ አባይ ፀሐዬ " ማን አባቱ ነው የሚያወግዘው ብለው በነፃነት ፤ ጥበቃ ተደርጎለት እንደልቡ እንዲፊነጭ ማድረጋቸው ነው እየተነገረ ያለው ። እንዲያውም ከዚህም በላይ ፓስተር አሰግድ በመንግሥቱ ድጋፍ የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን ፕሮግራም በናይል ሳት ከመጪው ሐምሌ አንድ ጀምሮ ሊጀምር እንደሆነ በይፋ ተናግሯል ።
ይህ ሁሉ ሲሆን በተለይ በሥርዓቱ ውስጥ የምትገኙ ለትግራይ ልጆች መልእክቴ በቅንነት ይድረሳችሁ ።
መቀሌ በተሃድሶ እየታመሰች ነው ። አዲግራት ምን አይነት ጭንቅ ውስጥ እንዳለች በነገው እለት በምለቀው ፖስት ማየት ትችላላችሁ ፣ ሽሬዎች ከተሃድሶ ጋር የሞት ሽረት ትግል ውስጥ መሆናቸው የሚታይ ነው ። አክሱም የችግር ጭምጭምታ እየተሰማ ነው ። አሁንም ይህ ሁሉ እየሆነ እያያችሁ የፓርቲ ፍቅር ከሀገርና ከሃይማኖት በላይ ሆኖባችሁ ፤ ውስጣችሁ እየሆነ ባለው ነገር ማረሩ እያስታወቀ በተግባር ግን ጥፋቱን እያጠፉ ያሉት ከፓትሪያርኩ ጀምሮ እስከ የመንግሥት የሥልጣን ስፍራ ያሉት የሀገራችሁ ልጆች የሚፈፅሙትን ድፍረት የተሞላበት ድርጊት እያያችሁ ዝምታን በመምረጣችሁ ስለ እውነት ከልብ አዝናለሁ ።
እንዲያውም ከዚህ በከፋ ሁኔታ በስመ ደኅንነት ለአሰግድም ሆነ ለውርጋጡ ከፍ ያለው ቱፋ የጥበቃ አገልግሎት እየሰጡት ጭምር መሆኑን ስናይ እኔ በበኩሌ እጅግ አድርጌ አዝናለሁ ።
ኢትዮጵያንም ሆነ ተዋሕዶን የሚታደግ እግዚአብሔር ነው ። አሁን ጊዜው በሰጣችሁ ሁሉን የማድረግ ስልጣን ተጠቅማችሁ ሀገሪቱንም ሆነ ቅድስት ቤተክርስቲያንን መታደግ ስትችሉ ፤ነገር ግን በቸልተኝነት ፣ በፍርሃት ፣ በይሉኝታ ተሸብባችሁ ዝም ብትሉ የቅድስት ቤተክርስቲያን አምላክ ይፋረዳችኋል ። ከፍያለው እንኳ ከአቅሙ ሽጉጥ ታጥቆ እንዲዞርና ለዘመድኩን መረጃ የሚሰጠውን አካል ባገኘው እደፋዋለሁ እያለ እንዲፎክር የልብ ልብ ስትሰጡት ሳይ አፈርኩባችሁ ።
በአኔ እምነት ሀገሬንም ሃይማኖቴንም የሚታደግ ሰው እግዚአብሔር ሳያስነሳ አይቀርም ። ትርፉ ትዝብት እንጂ ስለ እውነት እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለሀገሬ መዳንን ከሌላ ሥፍራም ቢሆን ማምጣቱ እንደሁ አይቀርም ። መርዶክዮስም እንዲህ ነበር ያለው ።
" መርዶክዮስም አክራትዮስን። ሂድና ለአስቴር እንዲህ በላት አለው። አንቺ። በንጉሥ ቤት ስለ ሆንሁ ከአይሁድ ሁሉ ይልቅ እድናለሁ ብለሽ በልብሽ አታስቢ።
.....በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? "
እግዚአብሔር ይመስገን ቁጥራቸው ጥቂት ሆነብኝ እንጂ ከእኔ ጋር የሚታገሉ የትግራይ ልጆች የሉም ማለቴ ግን አይደለም ። በሽሬ ፣ በአክሱም ሆነው ፣ በመቀሌና በአዲግራትም ተቀምጠው አይዞህ ዘመዴ ፣ ከአንተው ጋር ነን የሚሉ ወንድሞች አሉ ። እግዚአብሔር እናንተን አያሳጣን ፣ ሺህ ያድርጋችሁ ።
ለዛሬ አበቃሁ.! ።
"ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ፤ ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ሁሉ ፤ ክብሩን አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 ደግሞ የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 28/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ ።

Thursday, 25 May 2017

የመርሕ ጥያቄ ? ? ? በዲን ዳንኤል ክብረት

የመርሕ ጥያቄ
? ? ?
በዲን ዳንኤል ክብረት
★ ★ ★
በዚህ 15 ቀን ብቻ ፔጄን ያዩ የተመለከቱ ሰዎች ቁጥር 9 ሚልየን ሊገባ መሆኑን ፌስቡክ እየነገረኝ ነው ። ታዲያ በዚህ መጠን ሰው ማግኘትና መድረስ ከቻልን የምን EBC. ን መለማመጥ ነው ። ዳይ ወደ ዘመዴ ገጽ መረጃ መላክ ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ ።
Share ~በማድረግ ላላየ እናሳዩ ፤ ላልሰማም እአሰሙ ።
Comment ~በመስጠት በድርጊቱ ላይ ተወያዩ ።
Tag ~ በማድረግ በፉጨት የተሻሉ ሰዎችን እንጥራ ።
እስይ ደስ ሲል ይኸው አሁን በስተመጨረሻም ቢሆን እነ ዳኒም መጡልኝ.! እንዴ ብቻዬን ልፈንዳ እንዴ.!? ሆሆይ.! ደግሞም ባይመጡም ጉዳዬ አልነበረም ። እንደውሻ ለመጮህ ማን ብሎኝ.??? እንደ እብድ ፣ ደግሞም እንደ ውሻ እጮሃለሁ ።
በነገራችን ላይ.! የዛሬን አያድርገውና ደያቆን ዳንኤል ክብረትና ባለቤቱ ወይዘሮ ጽላት ፤ እኔ ቃሊቲ በታሰርኩ ጊዜ ልጆቼን አርብ አርብ ከቤቴ ወስደው ቅዳሜና እሁድ ከልጆቻቸው ጋር አውለው ፣ አጫውተው ፣ እሁድ ማታ ወደ ቤቴ ይመልሱዋቸው ነበር ። ምክንያቱን ባላውቀውም ያ ሁላ ነገር ግን አሁን የለም ። እንዲያም ሆኖም ግን ዳኒ በእኔ ልብ ውስጥ " ልዩ " ስፍራ ነው ያለው ።
የሚገርማችሁ ነገር ዲን ታደሰ ትናንት የግድያ ሙከራ ከተደረገበት በኋላ አርፎ ይቀመጣል ብዬ ስጠብቀው ብሶበት ቁጭ ብሏል " ። ታዴ አረ እንዴት ነው ስለውም ፤ አይደለም በመኪና ከፈለጉ በአውሮፕላን ለምን አይገጩኝም ከእንግዲህ ወዲህ መላቀቅ ብሎ ነገር አይታሰብም ብሎ አስደስቶኛል ። እናም ይኽን የዲን ዳንኤል ክብረትን ከዶክተር አባ ኃይለማርያም ጋር የገጠመውን ሙግትና የሚያቀርበውን ጥያቄ እያነበብን ከቆየን በኋላ ጊዜ ሲገኝ የታዴ አዲሱ ጦማርም ይለቀቅላችኋል ። እናንተ ብቻ ፀባይ አሳምራችሁ በያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ፦
 በፓትርያርክ አቡነ ማትያስ.!
 በአቡነ ቀውስጦስ
 በአቡነ ቄርሎስ
 በአቡነ ገብርኤል
 በአቡነ ቀሌሜንጦስ
በእነ ዚህ አባቶች ጨጓራችሁን እየላጣችሁ ፤ እርር ድብን እያላችሁ ፣ ትንፋሻችሁን ቁርጥ ቁርጥ እያደረጋችሁ ። ጠብቁኝ ። እነዚህ አምስት አባቶች ቅድስት ቤተክርስቲያንን ተማምለው ጉድጓድ ሊከቷት ያሰፈሰፉ አባቶቻችን ናቸው ። እናም አንድ እግራችሁን ከመቃብር አፋፍ ከትታችሁ ሳለ ፤ ቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ ዶር አባ ኃይለማርያምን የመሰለ 666 መልእክተኛ ፤ አባ ተክለሃይማኖትን የመሰለ የመንግሥት ቅጥረኛ ጳጳስ ለማድረግ ያሴሩ ፣ የቅዱስ ሲኖዶሱንና የመንፈስ ቅዱስን ልዕልና የተዳፈሩ አባቶች ናቸው ። ጉዳዩን እስኪያስተካክሉ መቃብር እስክገባ ድረስ በየምክንያቱ እያነሳሁ ስወቅሳቸው ዘላለሜን እኖራለሁ ።
ዲን ዳንኤል ክብረት እስከ አሁን ዝም ጭጭ ትንፍሽም ሳይል ከርሞ አሁን በስተ መጨረሻ ቢሆን ብቅ ያለ ወንድማችን ነው ። ቢሆንም አልረፈደም ። ደግሞም ከመቅረት ይሻላል ። ልክ እንደ ዲን ዳንኤል ሁሉ አሁንም ቢሆን ዝም ጭጭ ያሉ የሰላም ጊዜ ሐዋርያዎች ሞልተዋል። ዘላለም ወንድሙ የተባለ በሰላሙ ጊዜ በየአውደ ምህረቱ ምስኪን ካህናትን እየዘረጠጠ " ቄሶቹን ልክ ልካ ቸውን ነገራቸው " እየተባለ በጴንጤዎቹ ጭምር ተወዳጅ ለመሆን የበቃና አሁን ቀጭን ኢንቬስተር የሆነው አፈ ጮሌ ሰባኪ ፤ በዚህ ሰዓት ሰማይ ይውጣ ምድር የሚታወቅ ነገር የለም ። እኔ ግን እመጣበታለሁ ።
ዶር ዘበነ የተባለው ወንድማችን ፣ በሰላሙ ጊዜ ከማይመለከታቸው ጴንጤዎች ጋር በመሟገት ፤ ያንንም ሙግት ሲዲ ቪሲዲ እያደረገ መልሶ ሸቀጡን ምእመናን ላይ ሲያራግፍ የኖረ ነጋዴ አሁን ዶርበሆንኩ ካለ በኋላ የት እንደደረሰ መድኃኔዓለም ይወቅ ።
ትንሽ ውር ውር ይል የነበረው መምህር ምህረተ አብ አሰፋም አሁን ድምፁን አጥፍቷል ። መምህር አስቻለው ከበደም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከገባ በኋላ ጎመን በጤና ያለ ይመስላል ።
መር ጳውሎስ መልክዓሥላሴ ፣ ዲን ተስፋዬ ሞሲሳ ፣ ዲን ደንኤል ግርማ ፣ ቀሲስ ሱራፌል ወንድሙ ፣ መ/ር በላይ ወርቁ ፣ ዲን ታዲዮስ ግርማ ፣ ቀሲስ ያሬድ ገብረመድኅን ፣ ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ፣ ቀሲስ ብርሃኑ ጎበና ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ፣ ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ ፣ ዲን ምትኩ አበራ ፣ መጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ፣ መጋቤ እሸቱ አለማየሁ ። ለዛሬ ያልሆናችሁ ለመቼ ልትሆኑ ነው ?? ። የማንን ጎፈሬ እያበጠራችሁ ይሆን ። አንተ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያስ ትግሉን ተቀላቅያለሁ ካልክ በኋላ ምነው የበላህ ጅብ አልጮህ አለ.?? አቡኑ ማሞ የተባልክ ሰባኪስ ዝም ብለህ ፊልም እየሠራህ ብቻ መሸቀል ነው እንዴ ሥራህ.?? ተናገር እንጂ.?? አንተ የማለዳ ኮበብ የጥንት የጥዋቱ የወንጌል አርበኛ መምህር ተስፉ ግርማ (አንድምታ) የትደረስክ ። ሊቀሊቃውንት ስምዓኮነ በእውኑ በሀገር ውስጥ አለህን.!??
እመኑኝ ቅድስት ቤተክርስቲያን ምንም አትሆንም ። በመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፈ አስቴር ላይ መርዶክዮስ አክራትዮስን ወደ አስቴር ሲልከው ያለውን ነገር ላስታውሳችሁ።
" በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? " አስ 4 ፣14
ዳታንና አቤሮን ሙሴና አሮንን ከመቅደሱ አስወጥተው በሌላቸው ስልጣን ቤተመቅደስ አጥነው የርኩሰት ሥራ ፣ የድፍረት ሥራ በፈጸሙ ጊዜ ምድር ተከፍታ እንደዋጠቻቸው ዘኁል 16 ማንበብ ይቻላል ። ዮዲት ጉዲት 40 ዓመት ፣ ግራኝ አህመድ 15 ዓመት ኢትዮጵያንም ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማውደም ያልፈነቀሉት ተራራ አልነበረም ። በሰይፍ ልጆቿን ፣ በእሳት ቅርሶቿን ለመውደም ሌት ተቀን ባዘኑ ። እነ ሱ ጠፉ የለምም ፣ ቤተክርስቲያን ግን በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተች ናትና ይኸው አለች ፣ ወዲፊትም መስሯቿ ክርስቶስ ኢየሱስ በክብር እስኪወስዳት ድረስ ትኖራለች ።
ግን ትዝብት ነው ትርፉ ። ሁላችንም የመናጢ ደሃ ልጆች ነበርን ። ይሄን ጉዳይ ሰይጣንም እግዚአብሔርም እኛም እናውቀዋለን ። አንቱ የተሰኛችሁትም በዚህች ቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ ታይታችሁ ነው ። እናም የእንጀራ ቤታችሁ የሆነችው ፣ የክብር አዳራሻችሁም የሆነቻችሁ ፣ ግርማ ሞገሳችሁ የሆነች እናት ቤተክርስቲያን በዚህ መጠን ስትወጋ ጮጋ ማለታችሁ በእውነት ዝምታችሁ ያስፈራል ። ደግሞ ተወቀስን ብላችሁ ቡራ ከረዩ በሉ አሏችሁ ። ማንም አይሰማችሁም ። ደግሞስ እኔ ታናሽ ወንድማችሁ ያልወቀስኳችሁ ማን እንዲወቅሳችሁ ፈለጋችሁ ። ማንስ ይውቀሳችሁ ። በጭባጫ ሁላ.! በሉ አትንበጫበጩ ። ቱ እውነቴን ነው እናንተ ከአሰግድ ታንሳላችሁ እንዴ .?? ተብታባው ከፍያለው ቱፋ እንዲህ በነጻነት ሲፏልል እያያችሁ ከእሱ ታንሳላችሁ በማርያም.??? ሰው እሳት የሚተፋ ብእርና አንደበት ይዞ እንዴት ይፈራል ። በእውነት ያሳፍራል ። ለማንኛውም እንጠብቃችኋለን ።
አሁን ወደ ዳኒ ጦማር ልውሰዳችሁ.???

......ሰሞኑን ዶክተር አባ ኃይለ ማርያም ኦርቶዶክሳውያን ካልሆኑ አካላት ጋር ያከናወኑትን ‹የጠበልና እምነት› ጉዳይ በተመለከተ አያሌ ጥያቄዎች ሲነሡ ነበር፡፡ ነገሩን ከየምንጮቹ ብሰማቸውም በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን የነበረው የቂሣርያው ገዥ ፊስጦስ ‹ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም፣ ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጥ የሮማውያን ሥርዓት አይደለም› (የሓዋ.25፣16) ብሎ የተናገረውን መሠረት በማድረግ አባ ኃይለ ማርያም ለጉዳዩ የሚሰጡትን መልስና ማብራሪያ ጠብቄ ነበር፡፡ መልስና ማብራሪያውንም ሰጡ፡፡
አባ የድርጊቱን መከናወን አምነው የክንውኑን ዓይነት ከተወራው የተለየ መሆኑን አብራሩልን፡፡
መልሳቸውን ስናጠቃልለው፡-
1. መርሐ ግብሩ ‹ውኃ ለሁሉም› በሚል መርሕ እንደተዘጋጀ
2. ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳት እንደተገኙበት
3. ተበጥብጦ ከመጣው ውኃና እምነት ጠቅሰው በተሳታፊዎቹ ግንባር ላይ ምልክት አንዳደረጉ
4. ሰውዬው ጣቱን አስጠጋ እንጂ አንዳልቀባቸው
መርሐ ግብሩ ‹ውኃ ለሁሉም በፍትሐዊነት እንዲዳረስ› ከሆነ እንዴት ነው እምነትና ውኃ በመበጥበጥ ውኃ ለሁሉም ሊዳረስ የሚችለው፡፡ ‹ውኃ ለሁሉም› የሚለው ጉዳይ የዐውደ ጥናት፣ የምክክርና ምናልባትም የጸሎት ርእስ ሊሆን ይችላል እንጂ እምነትን በውኃ በጥብጦ በመቀባት ‹ውኃ ለሁሉም› እንዴት ለማዳረስ ይቻላል? እምነት በውኃ በጥብጦ መቀባት ለፈውስ ያገለግላል እንጂ እንዴት ከውኃ ፍትሐዊ አጠቃቀም ጋር ተገናኘ? ደግሞስ እኛ ከሌሎች እምነቶች ጋር አንድነታችንን ማምጣት ያለብን በክርስቶስ እንጂ እምነት በውኃ በመበጥበጥ ነው እንዴ?
አባ ኃይለ ማርያም በሰውዬው (የሌላ አምነት መሪ መሆኑ ከፎቶውና ከመረጃው ይታወቃል) ግንባር ላይ ሲቀቡት ምን እንዲያደርግ አስበው ነው? እንዲፈወስ የቀረበ በሽተኛ ነው? ለበረከት የመጣ ደጅ ጠኚ ነው? እንዴትስ ነው የተበጠበጠው እምነት ከ‹ ውኃ ለሁሉም› አስተሳሰብ ጋር የሚሄደው?
ሌላው አስገራሚ ነገር ደግሞ ‹ሰውዬው ጣቱን አስጠጋ እንጂ አልቀባኝም› ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹ ሁሉ የሚያሳዩት ግን ሲቀባዎት ነው፡፡ ደግሞስ ሰውዬው ለመቀባት ካላሰበ እጁን ለምን ወደ እርስዎ ያስጠጋል? ሊባርክዎ ነው? አስቀድማችሁ የተስማማችሁበት ሥነ ሥርዓት ይህንን የማይፈቅድ ከሆነስ እንዴት እጁን ወደ እርስዎ አስጠጋ? ‹እጁን አስጠግቶ ነበር› ካሉን ደግሞ ከተበጠበጠው እምነት እንደ እርስዎ ጠቅሶ ነበር ማለትዎ ነው? ለመሆኑ ኦርቶዶክሳዊ ክህነት የሌለው ሰው ከእምነት ጠቅሶ ሌላውን ሰው መቀባት፣ ያውም ቆሞሱን ይችላልን?
ሥነ ሥርዓቱ ሲከናወን ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደነበሩ አባም ነግረውናል፣ ፎቶውም አሳይቶናል፡፡ ምን ወስነው? ምን ሊያደርጉ ሄዱ? ውኃ ለሁሉ እንዲዳረስ ሊጸልዩ ወይስ ውኃ ለሁሉ እንዲዳረስ እምነት በውኃ ሊበጠብጡ? ለመሆኑ ይህንን እንዲያደርጉ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይፈቅድላቸዋል? ወይስ ሥልጣን ከቀኖና ስለሚበልጥ?
አባን ለዚህ ሁሉ ነገር የዳረጋቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ መርሕ እየተጣሰ ስለመጣ ነው፡፡ ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎችን እናንሳ፡-
ቤተ ክርስቲያናችን ኢኩሜኒካል ግንኙነትን የምትመራበት ፖሊሲና ደንብ አላት?
ቤተ ክርስቲያናችን ኢኩሜኒካል ግንኙነቶችን የምታከናውንበት ተቋምስ አላት?
የሁለቱም መልስ የላትም የሚል ነው፡፡ በሌሎች እኅት አብያተ ክርስቲያናት የኢኩሜኒካል ግንኙነትን የተመለከተ ፖሊሲና ደንብ ሲኖዶሱ ያጸድቃል፡፡ ከነማን ጋር ምን ዓይነት ውይይት ይደረጋል፣ ምን ዓይነት ውይይቶች በምን ደረጃ (በሊቃውንት፣ በጳጳሳት) ይደረጋሉ፣ ስምምነቶች እንዴት ይጸድቃሉ፣ የጸደቁት እንዴት ለሕዝብ ይገለጣሉ፣ የጸደቁትን እንዴት መተግበርና መከታተል ይቻላል፣ ስምምነት እስኪደረስ ድረስ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ምን ዓይነት ግንኙነቶች ይኖሩናል? በምን በምን እንተባበራለን? በየደረጃው ያሉ አካላት (ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን) ያላቸው ድርሻ ምንድን ነው፣ የሚሉትን የሚወስን የፖሊሲ መዝገብ አላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ግን ይህ ፖሊሲ የላትም፡፡ ፖሊሲውንም መሠረት አድርጋ የምትመራበትን ሕግ አላጸደቀችም፡፡ ስብሰባ ስትጠራ መሄድ ብቻ ነው፡፡
በሌላ በኩልም የኢኩሜኒካል ግንኙነትን የሚያካሂድ፣ ባለሞያዎችን የሚሰባስብ፣ መረጃዎችን የሚመዘግብ፣ በዓለም ላይ የሚደረጉ የኢኩሜኒካል ግንኙነቶችን የሚከታተል፣ ግንኙነቶቹን በፖሊሲውና በደንቡ መሠረት የሚመራ፣ ስሕተቶች ሲፈጠሩም የሚያርም ተቋምም የለም፡፡ ያለው የውጭ ግንኙነት መምሪያ ነው፡፡ እርሱ ደግሞ ብዙ ጊዜ እንግሊዝኛ ይችላሉ ተብሎ ስለሚታሰብ አሜሪካ በኖሩ ሰዎች የሚመራ ነው፡፡ የኢኩሜኒካል ግንኙነት ግን የአሜሪካን እንግሊዝኛ በመቻል ብቻ የሚሠራ አልነበረም፡፡ የውጭ ግንኙነት መምሪያው ወደ ውጭ ለሚሄዱ ሰዎች ሂደቶቻቸውን መከታተል፣ ከውጭ አጥቢያዎች ጋር ‹መገናኘት› የሚላኩ ሰዎችን መላክ እንጂ ራሱ እንኳን የሚመራበት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ያለው አይመስልም፡፡
ይህ በሆነበት ሁኔታ አባ ኃይለ ማርያም ያንን ነገር ቢያደርጉት የሚገርም አይደለም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በዕለቱ የነበሩት ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን መርሕ እየጣሱ ያዘዟቸውን ነው የተገበሩት፡፡ እርሳቸው ቢሆኑም ግን ፖሊሲና ሕግ በሌለበት ይህንን ተግባር ከሚያከናውኑ ‹ዱክትርናቸውን› ተጠቅመው ፖሊሲውና ሕጉ እንዲዘጋጅ ቢያደርጉ ኖሮ ይመሰገኑ ነበር፡፡ ነገ ጳጳስ የሚሆኑትን አባት ማንም እየተነሣ እጁን ወደ ግንባራቸው አይልክም ነበር፡፡ በሃይማኖት መሥመር የበላይ ያመጣውን ሁሉ በእምነት መመርመር ያስፈልጋል፡፡ የበላይ አዞኝ ነው ብሎ ቀኖና መጣስና እምነት ማፋለስ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
በጉባኤ ኬልቄዶን የክህደቱን ውሳኔ አልቀበልም ያለው ዲዮስቆሮስ በሮም ቤተ መንግሥት ተጠርቶ ‹ለምን አትቀበልም? ልዮንኮ አለቃህ ነው› ሲባል ‹ልክ ነው ልዮን አለቃዬ ነው፡፡ ነገር ግን ከእምነቱ ሲወጣ አልቀበለውም፡፡ ሳጥናኤልም ለቅዱስ ሚካኤል አለቃው ነበር፤ ከእምነቱ ሲወጣ ግን አልተቀበለውም› ያለውን እዚህ ላይ ማስታወሱ መልካም ነው፡፡ አሁንም ቤተ ክርስቲያናችን ኢኩሜኒዝምን የተመለከተ ፖሊሲና መመሪያ ካላወጣች፣ ጠንካራ ተቋምም ካልመሠረተች ነገ ከዚህ የባሰ ነገር ማየታችን አይቀርም፡፡ ከዚህ ተግባር የተማርነው ግን የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ በነቃ ኅሊና መከታተል እንዳለብን ነው፡፡
ያሳወቁንን እያመሰገንን፣ ያላወቅነው እንዲገልጥልን እንለምናለን፡፡
ይላል ዲን ዳንኤል ክብረት ከአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ፣ ማነህ እዚያ ጋር ተረኛ ቀጥል ። አሳየው ላላየው ። አከተመ ።
ያዝ እንግዲህ. ምድረ ግሪሳ ሁላ.!
"እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ይህንን ጦማር ዲን ዳንኤል ጻፈው መግቢያውንና ወቀሳውን እኔው ራሴ በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 ደግሞ የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 16/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ ።

ማን በቀደሰው ማይ ማን ይጠመቃል? ( በዲን አባይነህ ካሴ)


Share ~በማድረግ ላላየ እናሳዩ ፤ ላልሰማም እአሰሙ ።
Comment ~በመስጠት በድርጊቱ ላይ ተወያዩ ።
Tag ~ በማድረግ በፉጨት የተሻሉ ሰዎችን እንጥራ ።
...ዛሬ ደግሞ ተረኛው ዲን አባይነህ ካሴ ነው ። አንደበተ ርቱዕ ነው ። ሲጽፍ በብዕሩ ፣ ሲናገር በአንደበቱ ገዢ ነው ። ጀግና ጀግና ልጆችን በላይ በላዩ መውለድ የማይታክታት እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይኸው ዛሬ ደግሞ ልጇ ዲን አባይነህ ካሴ እኔም ጥያቄ አለኝ ብሎ ከተፍ ብሏል ።
ከዚህ ቀደም በፀረ ተሃድሶው ትግል ወቅት ግንባር ቀደም ታጋይ የነበረ መሆኑም በሁላችን ዘንድ ይታወቃል ። ለእነ " ታዴ " ተሃድሶ " የቀደመ የክብር ስማቸውን ከመዝገብ ቤት አቧራውን አራግፎ አውጥቶ ፤ ከኪዳነወልድ ክፍሌ መዝገበቃላት ውስጥ ፈልጎ " ሐራ ጥቃ " የሚለውን የቀደመ ስማቸውን ይጠሩበት ዘንድ ያስታወሰን ወንድማችን ነው ።
ዲን አባይነህ ካሴ ፦ በሙያው ኢንጂነርም ነው ። በገዛ ገንዘባችን ፣ ረቡብን ፣ በሚለው ስብከቱም ይታወቃል ። ለቅድስት ቤተክርስቲያን በርካታ መጻሕፍትን ያበረከተ ምርጥ የተዋሕዶ ልጅ ነው ።
አሁን ጀነራሎቹ እየመጡ ነው ። እንደኔ አይነቱ ከ " ፈንጅ ማምከን " ያልዘለለ ሙያ የሌለው ሰው አሁን ከሜዳው ላይ ገለል የሚልበት ጊዜም እየመጣ ነው ። በእኔ ቀፋፊ ጩኸት አንገታችሁን የደፋችሁ ወገኖች አሁን የጠላት ወረዳን ነጻ የማድረጉ ሥራ በመልካም ሁኔታ እየሄደ ስለሆነ ሥፍራውን ለሚመለከታቸውና ለሚገባቸው ሰዎች የመልቀቂያ ጊዜዬ እየደረሰ ነው ። እናም ትንሽ ጊዜ ነው የምትታገሱኝ ።
በአባ ኃይለማርያም ሺህ ሞት ላይ ጥያቄያችን ይቀጥላል ። አናቋርጥም ። የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት በድጋሚ እንዲያጤኑትም እንመክራለን ።
"ኤጲስ ቆጶስ በሚሾምበት ቀን ሰዎች ሁሉ ይገኙ። ሕዝብና ካህናት መስክረውለት ይሾም።..."ፍትሐ ነገስት በእንተ ኤጲስ ቆጶሳት ፤ አንቀጽ ፭፡፻፩ በሚለው መሠረት ህዝብና ካህናት ያልመሰከሩለት ግለሰብ አይሾምብንም ። አከተመ ።
በተለይ ይህ የህዝብ ፍላጎት ተጥሶ ይሄ መቅደሳችንን ያስደፈረ ግለሰብ በእንቢተኝነት ቢሾም ። በተለይ
ብፁዕወቅዱስ አባ ማትያስ
 ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ
 ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
 ብፁዕ አቡነ ገብርኤል
 ብፁዕ አቡነ ቀለሚንጦስ
የሕዝቡን ጩኸትና ተማጽኖ በመናቅ መቅደስ አርካሹ ዶ/ር አባ ኃይለማርያምና በመንግሥት ትእዛዝ እንዲሾሙ የሚፈለጉት አባ ተክለሃይማኖት ንጉሤ እንዲሾሙ እንዲያ መድከማችሁና ቤተ ክርስቲያንን ለውድቀት የሚዳርግና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚያሳዝን ድርጊት እንዲፈጸም አብዝታችሁ ስትታትሩ የታያችሁ በመሆኑ በዚህች ቤተ ክርስቲያንና ተከታዮቿ ላይ በጠላትነት የተነሣችሁ መሆናችሁ ይታወቅ ። እናም አዝነንባችኋል ። ሆኖም ግን አሁንም አልረፈደም ሥርዓተ ሲመቱ ከመፈፀሙ በፊት የሕዝብ ቅሬታ ተሰምቶ ጉዳዩን በድጋሚ እንዲታይ እንጠይቃለን እያልን በተቃውሞአችን እየቀጠልን በቀጥታ ወደ ዲን ኢንጅነር አባይነህ ካሴ ጦማር እንገባለን ። መልካም ንባብ ።




.......የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጁ አጥማቂ ፍለጋ ከአባቶቻቸው ይልቅ ወደ ፕሮቴስታንቶች ማዘንበላቸውን በራሳቸው አንደበት ተናገሩ፡፡ በሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደተከናወነ የተነገረው ቅብዓት አይሉት ጥምቀት በእርሳቸው ብቻ ሳይኾን በፓትርያርኩ ቡራኬ ሰጪነት የተከናወነ መኾኑ አነጋጋሪ ነው፡፡
እኛ እነርሱን ስናጠምቅም ይሁን ስንቀባ ብንገኝ ደግ በኾነ፤ አንድ ፓስተር ብድግ ብሎ አንድን በቁምስና ማዕርግ ያለ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛው አስተዳደር ውስጥ ተዋናይ የኾነን ሰው ሲቀባም ይሁን ሲያጠምቅ ማየት ከየት እንደመጣ እስካሁን ማንም አልነገረንም፡፡ ለጊዜው የነገሩ ሙሻዙር ወደ ም/ሥ/ አስኪያጁ ያጠንጥን እንጂ ዋናው ተጠያቂ መኾን ያለባቸው ፓትርያርኩ ናቸው፡፡ ሰውየው አድርግ የተባሉትን አድርገው ይኾናል፡፡ ይህም መለካዊነታቸውን ከሚያሳብቅባቸው በቀር ከተጠያቂነት ነፃ ያደርጋቸዋል ማለት አይደለም፡፡
እንኳን በማዕርገ ቁምስና በምእመን ደረጃም እንዲህ ያለ የሚፈጽም በሌለባት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይህን የኃፍረት ካባ ሊያከናንቡን መቁረጣቸው ብርቱ ጽዩፍ አድራጎት ነው፡፡ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለማን እንዴት መቼ እንደሚፈጸም በጉልህ የምታስተምርን ቤተ ክርስቲያን በቅጽሯ ውስጥ ነውረኛ ሥራ በማድረግ መሠማራት አደጋው ቀላል አይደለም፡፡ "የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል" ያለውን ልብ እንበል፡፡ ማር ፲፫፥፲፬።
ለመኾኑ እርሳቸው አሉ እንደሚባለው ጉዳዩ የተከናወነው በውኃ ነው ከተባለ፤ ጥምቀቱ ለልጅነት ነው ወይስ ለፈውስ? ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን ልጅነት የት ጥለውት ይኾን? አሞኝ ነው ካሉ ደግሞ ጠበል ቤት እንጂ ኪታ ለባሽ ፓስተር ይዞ ወደ መቅደስ መግባትን ምን አመጣው? ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በየትኛው አንቀጽ እንደሚወድቅም ሊነግሩን ይገባል፡፡ ኢኩሚኒካል ግንኙነትን ስለማጠናከር ነው ከተባለም በምሥጢር ተካፋይነት የሚፈጸም አይደለም፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንኳን ለመናፍቅ ትምህርተ ክርስትናን በመከታተል ላይ ያሉ ባለ ተስፋዎችን በቅዳሴ ጊዜ ምሥጢር ለመካፈል የበቁ አይደሉምና (ማለትም አልደረሱምና) ፃዑ ብላ ታሰናብታለች፡፡ እኒህን ጳጳስ አደርጋለሁ ብሎ . . . መነሣት ነገ ደግሞ ማንን አምጥተው በማን እንዲቀቡ ይኾን? ከአባቱ ውጭ ሌላ አባት መፈለግ . . .
በሰውየው ላይ ብዙ ችግር እንዳለ እየታወቀ ብዙ ጊዜ በዝምታ ታለፉ፡፡ አሁን ብለው ብለው በአደባባይ ቤተ ክርስቲያንን የማይመጥኑ መኾናቸውን በይፋ አጋለጡ፡፡ የሰውን ዲዘርቴሽን ግጥም አድርገው ገልብጠው ፒኤች ዲ አለኝ ሲሉ ኖሩ፡፡ ዝም ተባሉ፡፡ በሆለታ ገብርኤል አካባቢ ያለባቸውን ብዙ ነውረኛ ሥራ ሲሠሩ ኖሩ ዝም ተባሉ፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ . . .
በቅርቡ ቅዳሴ ረዘመ ብለው በሸገር ሬድዮ ሲነዛነዙ የነበሩት ፓትርያርክ አሁን ደግሞ እንዲህ ባለ ተግባር ላይ መሰለፋቸው ሒደቱን በጥሞና የሚያየው አካል ይፈልጋል፡፡ የእናት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንዲህ በዋዛ በዋዛ እየታለፈ መቀጠል የለበትም፡፡ የሃይማኖት ጉዳይ ቀስ በቀስ እንዲሸረሸር ብርቱ ጥረት የሚደረግ ይመስላል፡፡ በሰዓሊተ ምሕረት በተደረገው ይህ ኩነትም እንደ ደኅና ነገር ጳጳስ አስከትለው የደብር አለቆችን ጠርተው ታዳሚ ኾኖ መገኘት ምን ይሉታል? ቅዳሴው እንዲያጥር የሚከራከሩት ሰው ቀድሞም ቢኾን ምክሩን ያገኙት ከአንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር እንደነበር ነግረውን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ፓስተሮቹን ወደ ቤተ መቅደስ ይዘዋቸው ገቡ፡፡
በአሁኑ የግንቦቱ (፳፻፱) ሲኖዶስ ጉባኤ መካከል አንዱ ተነሥተው "መሠረት ስብሐት ለአብ መናፍቅ አይደለም" ብለው ድምፅ አሰምተዋል መባሉ ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው፡፡ አለማወቅ እንዲህ ካለ ድፍረት ያደርሳል፡፡ ክርስቶስ አማላጅ ነው ብሎ የቅዱሳንን ሥራ ለእግዚአብሔር ሰጥቶ የተናገረን ሰው መናፍቅ አይደለም ብሎ መከራከር ምን ይሉት ጥብቅና ነው፡፡ ሰውየው ሔደው የሙጥኝ ብለው የተጣበቁበት ድርጅት ምን ብሎ የሚያስተምር እንደኾነ በገሃድ እየታወቀ ለክርክር መሰናዳት ምን ይባላል?
የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን አቋም የሚሸራርፉትን በጥብቅ የሚቃወሙት አቡነ ቄርሎስ የሰጡት ምላሽ አንጀት አርስ ነው፡፡ የሚቅበዘበዝ ሀሳብ የሚያመጡትን እዚያው መገሠፁ የተገባ ለመድረኩ የሚመጥን ነውና፡፡ ግን እንዲሁ በቀላሉ መታየት አለበት ተብሎ መወሰድ የለበትም፡፡ ያንን ቃል የተናገሩት ጳጳስ ናቸውና በሀገረ ስብከታቸውም ብዙ ሃይማኖታዊ ውዝግብ እየፈጠሩ የሚገኙ ናቸውና ጉዳያቸው ለብቻ መታየት ይገባዋል፡፡ እኒህን ጳጳስ ሰውየው ራሱ ቢሰማቸው እንዴት በሳቀባቸው፡፡ ጥብቅናውን አይፈልገውም፡፡ ይብላኝ ለእርሳቸው እንጂ በአደባባይ ማንነቱን ደጋግሞ የተናገረ "ምስጉን" መናፍቅ ነው፡፡ ታዲያ ለሞተ ሰው ጥብቅና መቆሙን ምን አመጣው? ነገር ዝም ብሎ አይመዘዝምና ደጋግሞ ማጤኑ ይበጃል፡፡
እነዚህ ሦስት ጉዳዮች በለበጣ የሚታዩ አይደሉም፡፡ ይታሰብባቸው!
ይለናል ዲን ኢንጅነር አባይነህ ካሴ.!! ማነህ ባለ ሳምንት ጅግና የተዋሕዶ ልጅ ተረኛ ቀጥል.! ቀጥል.!
ያዝ እንግዲህ. ምድረ ግሪሳ ሁላ.!
"እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ይህንን ጦማር ዲን ዳንኤል ጻፈው መግቢያውንና ወቀሳውን እኔው ራሴ በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 ደግሞ የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 17/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ ።

LikeShow More Reactions
Comment

Tuesday, 23 May 2017

ቁርቁር ሲኖዶስ

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትላንትና ወይም ዛሬ የተፈጠረች አይደለችም፡፡ ሲኖዶሳዊ ታሪኳ ግን ቁርቁር ነው፡፡ ሲኖዶሳዊ አበቃቀሏ ቁርቁር በመሆኑ ሲኖዶሳዊ ገጽታዋም የተቆረቆሩ ከተሞች ገጽታ ዐይነት ነው፡፡ ለነገሩ ድሮ ድሮ ቁርቁር ከተማ እንጂ ቁርቁር ሲኖዶስ አልነበረም፡፡ ቁርቁር ከተማዎች ለመኖራቸው ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለጊዜው ከጎጃም የበዛብህ መዲና ማንኩሳ፤ ከሲዳማ ተፈሪ ኬላ ምስክሮቼ ናቸው፡፡ እኒህ ከተማዎች እግረ መንገድ በንጉሣዊ ትእዛዝ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ እናም ዛሬ ዛሬ ቁርቁር ከተማዎች አልፈው በዘመናች ነገሥታት ትዕዛዝ የሚፈጠሩ ቁርቁር ሲኖዶሶች እየበዙ ነው፡፡ ቁርቁር ከተሞች በዋናነት ተፈጥሯዊ ሒደትን ተከትለው አይፈጠሩም፡፡ አብዛኛው ጊዜ አፈጣጠራቸው የነገሥታቱን ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ኀይልን ማዕከል በማድረግ ነው፡፡ በቁርቁር ከተሞችም እንዲከትሙ የሚደረጉት በብዛት ከነገሥታቱ ጋር ማኅበረ ፖለቲካዊ ተዛምዶ ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡
ሲኖዶሳችንም አበቃቀሉ እንዲሁ ነው፡፡ ሲኖዶሳዊ የአበቃቀል ሒደትን ተከትሎ ያላደገ እንደመሆኑ የቄብ ስብስብ ነው፡፡ በዚህ የአበቃቀለ ሒደት ውስጥ በሃይማኖት ብሔርተኝነት ራስን ለመቻል የተጋደሉ አበው ቢኖሩበትም፥ የንጉሡ የፖለቲካ ኀይል ሚዛን ፍላጉት ግን ማዕከላዊ ነበር፡፡ የብልጭታ ያህል ጥቡዓን አበውም ቢኖሩበትም፥ ንጉሡም ፖለቲካዊ ፍላጎቶቼን ያስጠብቁልኛል ያሏቸውን አበው እንዲካተቱ ማድረጋቸው አይጠረጠርም፡፡
በዚሁ የታሪክ አዙሪት የቀጠለው ሲኖዶሳችን መለካዊነትን በተልዕኳዊ ቅርጽ ያዳበረ ይመስላል፡፡ በተለይ ደግሞ በዚህ ዘመን መንግሥታዊ ፈቃዳትን መፈጽም ሲኖዲሳዊ ተልእኮ ወደ መሆን ያደገ ይመስላል፡፡ መንግሥትም ፈቃዴን ያስፈጽሙልኛል ያላቸውን አባቶችን ለማስረግ የሚጋደለውን ያህል፤ሲኖዶሳችንም ፈጻሜ ፈቃድ የሆኑትን አበው አካቶ ለመሔድ እጅግ የተጋ ነው፡፡ መንግሥት በግልጽ አባ ሠረቀ ወልደ ሳሙኤል፣ አባ ኀይለ ማርያም መለስና አባ ተክለ ሃይማኖትን ሲኖዶሱ በኤጴስ ቆጶስነት አካቶ እንዲሔድ የተለያዩ ግፊቶችን አድርጎ ነበር፡፡ ቅዱስነታቸውም ይህን መንግሥታዊ ፈቃድ ለማስፈጸም ከአቶ ካሣ ተክለ ብርሃን ጋር በመሆን አስመራጭ ኮሜቴውን ማወያየታቸው አብነታዊ ማሳያ ነው፡፡ አባ ሠረቀ ከፓትርያርኩ ጋር በነበራቸው አለመግባባትና ይህን ተከትሎም በአቶ ካሳና በፓትርያርኩ መካከል በተፈጠረው ክፍተት ነጥበው ሲቀሩ፥ አባ ኀይለ ማርያም መለስና አባ ተክለ ሃይማኖትን ተካትተው ሔደዋል፡፡ በርግጠኝነት አባ ሠረቀ ከፓትርያርኩ ጋር ቅራኔ ውስጥ ባይገቡ ኖሮ ተካተው መሔዳቸው አይቀርም ነበር፡፡ ሲኖዶሳችን በመለካዊነት-በፈጻሜ ፈቃድነት አይጠረጠርምና፡፡
ቁርቁር ሲኖዶስ የቁርቁር ተሿሚዎች ስብስብ እንደመሆኑ መጠን ፥ የኤጴስ ቆጶሳት የምርጫ ሥርዐቱም ስሪታዊ ነው፡፡ በስሪታዊ የምርጫ ሥርዐት ደግሞ በአንድ በኩል የምርጫ ሕጉ ጉቦ ለተቀበሉባቸውንና ለመንግሥታዊ ተልዕኮ ለተመለመሉት እጩ ኤጴስ ቆጶሳት ማለፍ ጋሬጣ መሆኑ ከታወቀ፤ ጋሬጣ የሆነው የሕግ አንቀጽ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ የኤጴስ ቆጶሳት የምርጫ ሕግ ለጥቆማ እና ለምርጫ ቋንቋ እና ዘውግ መስፈርት ነበሩ፡፡ነገር ግን ጉቦ ለተቀበሉባቸውንና ለመንግሥታዊ ተልዕኮ ለተመለመሉት እጩ ኤጴስ ቆጶሳት ማለፍ ጋሬጣ እንደሆነባቸው የተረዱት ቀንደኛ አማሳኝ እና መለካዊ ሊቃነ ጳጳሳት ተረባርበው ከምርጫ ሕጉ እንዲወጣ አድርገዋል፡፡ ለአንቀጹ መውጣት ግን ምክንያት ያደረጉት አሰቀድመው የተቀዎሙትንና በኋላ ደግሞ ለሽፋን የተጠቀሙበትን ፥ ‹‹ አካባቢና ቋንቋ በመስፈርት መካተቱ ከመንፈሳዊ አሠራርና አንድነትን ከማጽናት አንጻር ችግር ያስከትላል፡፡ ›› የሚለውን ነው፡፡ እውነታው ግን እርሱ አነበረም፡፡ ሕጉ በአንድ ገጽታው በአቡነ እስጢፋኖስ የተደራጀው (በጎልህ መገለጫው) የመለካዉያን ጳጳሳት ስብስብ እንዲመረጡ ለሚፈልጓቸው ለአባ ተክለ ሃይማኖት ዘጋቤላ እና በሌላው ገጽታ ደግሞ በአቡነ ኤልያስ የተደራጀው (በጎልህ መገለጫው) የአማሳኝ ጳጳሳት ስብስብ እንዲመረጡ ለሚፈልጓቸው ለአባ ሔኖክ ሁኔታውን ማመቻቸት ነበር፡፡ በዚህ ሕግ መሠረት አባ ተክለ ሃይማኖትም ሆኑ አባ ሔኖክ የተወዳደሩበት ሀገረ ስብከት ቋንቋቸውም ሆነ ዘውጋቸው አይደለም፡፡ ሰለዚህ ቋንቋና ዘውግን የተመለከተው አንቀጽ መደምሰስ ነበረበት፡፡ እነርሱም እንዲካተቱ ተደረገ፡፡
በሌላ በኩል ድግሞ ስሪታዊ የምርጫ ሥርዐት ለገዳማዊ ሕይወት እና ለትምህርት ደረጃ ተገቢውን ዋጋና ክብር ሰለማይሰጥ፥ በገዳማዊ ሕይወታቸውም ሆነ በትምህርት ደረጃቸው የተመሰከረላቸውን እየገፈተረ፤ በገዳማዊ ሕይወታቸውም ሆነ በትምህርት ደረጃቸው ነቀፋ ያለባቸውን አካቶ ይጓዛል፡፡ መንግሥታዊ ድጋፍ አላቸው ያላቸውን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጪ ሲያካትት፤ መንግሥታዊ ድጋፍ ሳይኖራቸው በሊቃውንት እና በምዕመናን ዘንድ ቅቡል የሆኑትን የሚገፈትር ነው፡፡ ይህ ማለት በገዳማዊ ሕይወታቸው የተመሰከረላቸውን እና በትምህርት ደረጃቸው እጅግ የላቁትን ሊቀ ሊቃውንት እዝራን በአጣማጅ አወዳድሮ፤ በገዳማዊ ሕይወታቸውም ሆነ በትምህርት ደረጃቸው ነቀፋ ያለባቸውን አባ ተክለ ሃይማኖትን ያላጣማጅ በብቸኝነት አወዳድሮ ኤጴስ ቆጶስ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ መንግሥታዊ ድጋፍ ያላቸውን አባ ተክለ ሃይማኖትን ወይም አባ ኀይለ ማርያምን ሹሞ፤ መንግሥታዊ ድጋፍ የሌላቸውንና ቅቡል የሆኑትን ሊቀ ሊቃውንት እዝራን አለመሾም ነው፡፡
ስሪታዊ ምርጫ ቁርቁር ተሿሚዎችን መቀፍቀፍ ባሕርይው ነው፡፡ አሁን ያለው ሲኖዶሳችን የዚህ መንስኤ እና ተግብሮት ነው፡፡ ከስሞኑ የተካሔደው ምርጫ ደግሞ የተግብሮቱ ክትያ ነው፡፡ ሲኖዶሳችን ከዚህ ባሕርያዊ መገለጫው አኳያ፥ በአምስተኛው ዘመነ ፕትርክና የተሾሞ መለካውያን ኤጴስ ቆጶሳትንም ሆነ አሁን በእነዚሁ መለካውያን የተቀፈቀፉትን አዲሶቹን መለካውያን እጩ ኤጴስ ቆጶሳት አካቶ መሔዱ ግድ ነበር፡፡ ነገሩ ከእንክርዳድ ስንዴ አይለቀምምና ነው፡፡
ምእመኑ ለሚቀጥለው ትውልድና ስለነገይቱ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ሲጨነቅ፤ አንዳንዶቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ዛሬ ሊያገኙ ስለሚጓጉት ተጨማሪ ሹመት፣ ቤት፣ መኪና እንቅልፍ አጥተው ይጨነቃሉ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰብዓዊ ገጻቸው ወደ ማኅበራዊ ትምክህተኝነት እንዲዘቅጡ አድርጓቸዋል፡፡ ምጣኔ ሀብታዊ ቅርምት ውስጥም ከቷቸዋል፡፡ ውጤቱ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያኒቱ መተረማመስ አስተዋጽኦ ያደረጉ የጥፋት ኃይሎች ዛሬ ደግሞ በእነሱ ትከሻ ላይ ታዝለው እንዲመጡ ረድቷቸዋል፡፡ የሚያስጨንቀውም የእነርሱ መምጣት ሳይሆን የአባቶቻችን መለካዊነታቸው አይሎ የተውኔቱ አባላት መሆናቸው ነው፡፡ በዚህ መልኩ በሩ የተከፈተላቸው አተራማሽ ኃይለ ግብር ቁስላችንን ዘወትር እንዳሰፉት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከኦርቶዶክሳውያን መዳፍ ውስጥ ፈልቅቀው በማውጣት እና ዘላለም በሰማዕትነት ከአከበሯት አባቶቿ ብብት ውስጥ በመስረቅ አይሆኑ ሆና እንድትኖር ግዴታ ይጥሉባት ዘንድ ሢመታዊ መደላደልን ተቀዳጁ፡፡
ይህ ሲሆን ግን የእነ አቡነ ቄርሎስ፣አቡነ ቀውስጦስና አቡነ ገብርኤል ከለላ ሰጪነት፤ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ጨርሶ ወደ ጥፋት፣ ወደ ውድመት፣ ወደ ሞት የመሔዷ ማስረጃ አይደለምን? በርግጥ እንዲህ ዓይነቱን የኋላ ሩጫ ከጀመርነው ይኼውና ሃያ ስድሰተኛውን ዓመት ጀምረነዋል፡፡ ሆኖም ግን የሰማዕታቱ ቤት፣ የነጻዎቹ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ፈርሳ አላበቃችም፡፡ በእርግጥ ግን ተዋርዳለች፡፡ ውርደቷም በእርሷ ስም ያሉት መሪዎቿ መዋረድ ነው፡፡ እነሱ ምንም ይሁኑ ምን ፍርዱን ከእግዚአብሔር የሚያገኙት ሲሆን፥ የሚያሳዝነኝ ግን ለቤተ ክርስቲያኒቱ ክብር መጣኝ ባልሆኑ ድርጊቶቻቸው በሌላው ዓለም ፊት ተዋርደው የኛኑ ቤተ ክርስቲያን ማዋረዳቸው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከእነሱ መኖሪያ ቤት ክብር በታች ስትታይ ምን ይሰማችኋል? የቆራጦቹ ሰማዕታት ቤት፣ የነጻዎቹ ሊቃውንት ቤት ተዋረደች አያሰኝም?በርግጥ ነገሩ ሁሉ የተበላሸው አሁን አይደለም፡፡ ሢመተ ጵጵስናው ክብር ሲያጣ፣ የምልመላው መስፈርት ቦታ ሲያጣና ከሕግ ውጪ ያለ ምእመናን ይሁንታ ሲታደል ነው፡፡
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን መዋቅር ሁሉ የበላይ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በእንዲህ ዓይነቱ መለካዊ ግብር መታጀሉ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ለእኔ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቁርቁር ሲኖዶስ አባላት ገጽ ይኼ ነው፡፡ የእናንተን ገጻዊ ትንታኔ ደግሞ በእናንተው መንገድ አሳዩኝ፡፡ ለእኔ ግን አሁንም ቁርቁራዊ ገጹ አይሏል፡፡ መንፈሳዊ ገጹ ኮስምኗል፡፡ የዘወትር ምኞቴም ሆነ መሻቴ እንደ ዘውድ የተቆጠረው ቆብ ተገቢውን ቦታና ሰው እንዲያገኝ ነው፡፡ የዘወትር ሕልሜ እውነት ሸባቢው “ዘውድ” ወልቆ እውነት አናጋሪው ቆብ እንዲጫን ነው፡፡ ይህም እውን የሚሆነው ሲኖዶሳችን ከመለካዊነት ወይም ከቁርቁርነት ወደ ኦርቶዶክሳዊ ኵላዊነት ሲለወጥ ብቻ ነው፡፡ ይህንንም እናፍቃለሁ፡፡

Friday, 19 May 2017

የእኔ የዘመዴ ስጋትና ኑዛዜዬ ።

የእኔ የዘመዴ ስጋትና ኑዛዜዬ ።

★ ★ ★ ★ ★
ጎበዝ አደጋ ላይ ነኝ ✔ የልጆቼን ነገር አደራ.! ገዳዮቼ ጀርመን ገብተዋል ፤ መረጃው ለጠበቃዬ ደርሷል ፣ ጉዳዩ በህግ ተይዟል ። ነገር ግን ምንም አይመጣም ፣ በእኔ በኩል ሁሉን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ። እናት ቤተከርስቲያን ፍርሃትን አላስተማረችኝም ። የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስን ገድሉን ሳነብ ስባረክበትም ኖሬ ደግሞ ልፍራ.!! ወጊድ በለው ።
✔Share ~ Share ~ Share ~ Comment✔
✔ልብ ብላችሁ ስሙኝ አድምጡኝም ። ስተፈልጉ ቅዠት ስትፈልጉም ትንቢት ብነው ብላችሁ አድምጡኝ ።
✔ በተለይ የትግራይ ልጆች ጆሮ ሰጥታችሁ ስሙኝ ።
✔ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳሳት የነበሩት ታላቁ የሃይማኖት ገበሬ ብፁዕ አቡነ ሰላማ በረከታቸው ይደርብንና ከታች የተናገሩት ቃለ ምዕዳን ሰምተን እንጠቀምበት ።
ውድ ኢትዮጵያውያን ይልቅ ከወራት በፊት ቀመር ተሠርቶለት የተጠናቀቀውን የአባ ኃይለማርያምንና የአባ ተክለሃይማኖትን በመንግሥት ትዕዛዝ ቀድሞ መመረጥ እያነሳን በከንቱ ጨጓራችን መላጡንና ጊዜ መፍጀቱን አቁመን ዳይ.! ዳይ.! ዳይ.! ወደ ቀጣዩ አጀንዳ በአስቸካይ እንግባ ።
ልብ በሉ ፈረንጆቹ መጀመሪያ እንዲህ አሁን ኢየሱስ ጌታ ነው የሚል ፉከራ በየአደባባዩ ሊያሰሙን እኛን እምነት የፋራ ነው ፣ እግዚአብሔር የሚባል ነገር የለም ፣ አሉንና እኛንም ፋራ አትሁኑ እግዚአብሔር የለም በሉ ብለው ሰበኩን ፣ ፍልስፍናቸውንም ጫኑብን ። አዳሜ እውነት መስሎን እግዚአብሔር የለም እንድንል አደረጉን ፤ ፓጋንም ሆነን እንደ እንስሳም መኖር ጀመርን ። ጾም ቀረ ፣ ጸሎትም ተረሳ ፣ ማስቀደስ ፣ ካህን ማክበርም ተተወ ፣ መስቀል ተናቀ ፣ ፀበል ተጠላ፣ መዕተብ ተበጠሰ ።
ቀጠሉና ኢትዮጵያውያን ሞትን የማይፈሩት ፣ ለሃገራቸው ሲሉ ባዶ እጃቸውን ሽመል ይዘው ሚሳኤል ከጫነ ሠራዊት ጋር ተዋግተው የሚያሸንፉት.?? ምን ቢሆኑ ነው.?? ብለው ተመራምረውና አጥንተው ሲያበቁ አስኳሉን አገኙት ። ይኸውም ምንድ ነው ያልን እንደሆነ ፤ ኢትዮጵያውያን ጀግና የሆኑት ፣ በእግዚአብሔር ማመናቸው ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን መመርመራቸው፣ ገድለ ጊዮርጊስን ፣ ገድለ መርቆሬዎስን ፣ ገድለ አቡነ አረጋዊን ፣ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ፣ ገድለ ክርስቶስ ሠምራን ፣ ገድለ እስጢፋኖስን በማንበባቸው ምክንያት የሰማዕታት ህይወት ስለተዋሃዳቸው ፤ ልምምዱም ስላላቸው ነው ሞትን የማይፈሩት የሚል ሆኖ አገኙት።
ከዚያማ ምን ይጠየቃል ትውልድ ፈጠሩ ፣ ገድል ከቤተክርስቲያን ይውጣ ፣ ድርሳን ምን ያደርጋል ፣ አዋልድ መጻህፍት ምን ይሠራሉ ፣ የሚሉ ትውልዶችን ፈጠሩ ። ይኸው ዛሬ ወጣቱ የዚህ ተንኮል ምርኮኛ ሆኖ የራሱ የሆነውን ጥሎ አናንቆና ሰድቦ አረፈው ። አሁን እድሉን አጥተው እንጂ እድሉን ቢያገኙ በአንድ ቀን ሁሉን ነገር ድምጥማጡን አውጥተው መጻህፍቱን በሙሉ አቃጥለው ቢጨርሱ እንዴት ደስተኛ በሆኑ ነበር ።
ደግሞ እንዲህ አሉን ፤ ጤፍ መብላት አይጠቅምም ፣ በጤፍ ውስጥ ምንም አይነት ለሰውነት የሚጠቅም ማዕድን የለበትም ፣ ዝም ብሎ ሰጋቱራ ነገር ነው ፣ የፈረስና የከበት ምግብ እንጂ የሰው ልጅ ሊበላው የሚችለው ምግብ አይደለም። እግር ኳስ ተጫዋቾቻችሁ እንዲህ ቀጫጭን የሆኑት የማይረባውን ጤፍና የጤፍ እንጀራ በመብላታቸው ምክንያት ነው ተባለና ሰው ጤፍን እንዲንቅ ተደረገ ፣ ጤፍ ተጠላች ትውልዱ ፈረንጅ ለመሆን ሲል የፈረንጅ ምግብ ነው ወደ ተባለ ነገር ፊቱን አዞረ ። ጤፍ ይመገብ በነበረ ጊዜ ጤነኛ የነበረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አሁን የፈረንጅ የተባለ ምግብ ሲመገብ ጊዜ የሚፈልገውን ውፍረት አገኘ ፣ ፊቱም ወዛ አለ ፣ ቀላም አለ ፣ ፈረንጁንም መሰለ ፤ ነገር ግን በተቃራኒው ደግሞ በሽተኛ ሆነ ። በኢትዮጵያ ታሪክ በምንመገበው ምግብ እና በአመራረት ዘይቤያችን ምክንያት ሰው ሁሉ በከንሰር ፣ በጉበት ፣ በኩላሊት ፣ በስኳር እና በጨጓራ ምክንያት ይረግፍ ጀመር ፣ የሆስፒታል አልጋዎች ጠፍተው ዜጎች ኮሪደር ላይ ተሰቃይተው የሚሞቱባት ሀገር ሆነች ።
እና አሁን ጤፍን ከዘረፉን በኋላ ዛሬ የእነሱ ሰዎች ጤፍን በመመራመር ፕሮፌሰር ተባሉበት ፣ በጤፍ ውስጥ ያለውንም አስደናቂ ንጥረ ነገሮች በሙሉ እየተደነቁ መልሰው ይተነትኑልን ጀመር ፣ ዛሬ በአውሮፓና በአሜሪካ ጤፍን መመገብ በጤና ለመኖር እንደዋስትና ተቆጠረ ። እኛ ግን እንረግፋለን ። እነሱ አንድ ኪሎ ጤፍ የወርቅ ዋጋ ተምነውለት መልሰው በውድ ይሸጡለታል ።
እነሱ ፊደል መቁጠራችንን ፣ በቄስ ትምህርት ቤትም ማለፋችንን እንደ ፋርነት እንድንቆጥረው አደረጉን ። ግዕዝ ማጥናት ፣ መነጋገር ፣ መጻፍ የፋሮች ፣ የኋላ ቀሮችም ነው ብለው እኛን አስጣሉን ። በጎን ግን ዘረፉን ፣ አስዘረፉን ፣ ቋንቋውንም የሚያስተምሩበት ዩኒቨርስቲዎችን ከፍተው ግእዝን ያጠናሉ ፣ በግእዝ የተጻፉ መጻህፍትንም በመመርመር የተደበቁ ጥበቦችን ያፈልቁበት ጀመር ።
እኛን ጤና አዳምን እና ዳማከሴን አስጥለው እነሱ ጀሶና ከኖራ የተሰራ እንክብል አዋጡን ። በጦርነት ያልጠፋን ህዝቦች እነሱ በሰው ሰራሽ ችግሮች ፈጁን ።
2ሺ ዘመን የቆየውንና ስንታመም የሚጸልይልን ፣ ስንጣላ የሚያስታርቀንን ፣ በ40 እና በሰማንያ ቀናችን ከምስጢረ ጥምቀት የሚያካፍለንን ፣ ወንጌል ሰብኮ ፣ ቀድሶ አቁርቦ ስንሞት በጸሎተ ፍትሃት የሚሸኘንን የራሳችንን ካህን እንድንጠላ ፣ እንድንንቀው ፣ እንዳንሰማው አደረጉን ፣ እነሱ ግን ፓስተር የሚባል ስያሜ የተሰጠውን ጎረምሳ እንደ ኳስ የሚያንቀረቅበንን ፣ በአደባባይ የሚያዋርደንን ፣ የሚጫወትብንን ፣ የሚቀልድብንን ፣ ከኮሜዲያን በላይ የሚያስቀንን የእኛን ካህን የሚተካ አምጥተው አስቀመጡብን፣ አለማመዱን ፣ አሁን ትውልዱ እንደ ፓስተር የሚፈራው እና የሚያከብረው ሰው በዚያች ምድር ላይ ያለ ማንም የለም ።
የባህል ልብሳችንን አስወልቀው ታይትና ጅንስ አስታጠቁን ፣ የጸጉር አሰራራችንን ሳይቀር እንድንጠላው ተደረግን ፣ ትውልዱ ከራሴ ጀምሮ ፣ ጠጪ ፣ አመንዝራ ፣ ጫታም እና ሰካራም እንድንሆን አደረጉን ። ነፈዝ ሆንን ፣ ጀዘብን ፣ ከንቱና የማንረባ ሆንን ፣ አሁን በቁማችን ሞተናል ። ስለ ሀገር መጠየቅ ፋርነት ነው ። ማጨስ ፣ መጠጣት ግን ፋሽን ፣ ነው ዘመናዊነት ሆኖ ትውልዱ ላሽቆ እንዲቀመጥ ተደረገ ። ሐሰት ነገሠች ፣ እውነት ሀገር ለቃ ተሰደደች ። መሪዎች ሳይቀሩ ፣ ሚዲያው ሳይቀር ፣ የሃይማኖት አባቶችና ታላላቅ ሰዎች ሳይቀሩ ሐሰተኞች ሆነን ተገኘን ።
አሁን ትውልዱ ለምለሟን እና ውስጧ አረንጓዴ የሆነውን ሀገር ጠልቶ እግሬ አውጪኝ ብሎ እየተሰደደ ነው ። ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ መነኮሳት ፣ ባህታውያን ፣ ማየት የሚያስጠላው ትውልድ እንዲፈጠር በብርቱ ደከሙ ። ለጊዜው ሲያዩት የተሳካ መስሎ ታይቷል ። እግዚአብሔር ግን አሳልፎ አይሰጠንም ።
አደዋ ላይ ፣ ገጉንደት ላይ ፣ ምጽዋ ላይ ነጮቹን ድል መንሳታችን ቂም አስቋጥሮብን ይኸው ዋጋ እያስከፈለን ነው ። ሀሰት የሚል ካለ ይምጣ. ፣ ።
የምንወደውን ነገር ሁሉ እንድንጠላ እየተደከመ ነው ። ባንዲራውን ብትሉ ፣ አንድነትን መመርጥ ብትሉ ፣ እጅግ አይወደድም ፣ የተበታተነ ፣ የማይግባባ ፣ የማይተማመን ዜጋ እንዲፈጠር በብርቱ ተለፋ ፣ እናም እየተሳካ ነው ። በኢትዮጵያዊነቱ ሳይሆን በብሄሩ የሚመካ ትውልድ ተፈጠረ ፣ ጠቡ አሁን ፍሬ እያፈራ ነው ። ሰሞኑን በመቀሌ ያየነው የባህርዳር ከነማና የመቀሌ ስፓርት ደጋፊዎች ጠብ የጤና አይመስልም ። ከተለመደው እና በእስፓርት ሜዳ ከምናየው ጠብ የተለየ ነው ። ማንነትን መሰረት ያደረገ ጸብ ነው ።
ፈረንሳይ ፣ ቤልጂየም ፣ ጣሊያን ፣ ስዊዘርላንድ ፣ ኦስትሪያ እና ሆላንድን አይቻለሁ አሁንም በጀርመን እገኛለሁ ። አንዳቸውም መታወቂያቸው ላይ በጎሳው የሚጠራ አላየሁም ፣ ተሳስቼ ከሆነ እታረማለሁ ። የእኛ ግን አሰቃቂ ነው ። እግዚአብሔር ይጠብቀን ።
የመጨረሻው ታርጌት ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ ነው ። ትውልዱ እንደፋሽን የያዘውን ነገር ተመልከቱልኝ ከደቡብ ክልል የጀመረው ሃይማኖትን የማስቀየር ዘመቻ አሁን አሁን መሃል ሀገሩን ጥሶ የአማራውን ክፍል አልፎ ትግራይ ገብቷል ። ኤርትራ አስቀድማ እንድትገነጠል ተደርጓል ። አሁን ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ሙልጭ አድርገው አጥበው አዲስ የጎሳ ማንነት የተላበሰ ፣ አዲስ ሃይማኖት የሚከተል ፣ ሀገር ፣ ባህል ግድ የሌለው ትውልድ ተፈጥሯል ።
መቀሌ በተሃድሶ ፕሮቴስታንቶች እየታመሰች ነው ። ሽሬ ተሃድሶዎቹና ኦርቶዶክሶቹ የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ነው ። አዲግራት ደግሞ " አዲግራትን ለኢየሱስ " የሚል ፕሮጀክት ቀርጸው የሚንቀሳቀሱ ዲያቆናትና የሰንበት ተማሪዎችን በመመልመል በሱዳን ካርቱም ተመልምለው በአዲስ አበባ ሰልጥነው አዲግራት ድረስ ሄደው ስልጠና የሚሰጡ የተሃድሶ አባላትን ማሰማራት ጀምረዋል ። የሚገርመው አዳራሹን የሚፈቅድላቸው መንግሥት ሲሆን ፈቃዱን የሚጠይቁላቸው ደግሞ ፕሮቴስታንቶች ናቸው ። መረጃውን ሰሞኑን ጠብቁኝ ። በአይናችሁ ታይቱላችሁ ።
አሁን የቀረው ማነው ያልን እነደሆነ አክሱም ጽዮን ማርያም ። በመጨረሻም ሀገሩ በሙሉ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንዲጠላ ይደረግና ፣ ሃይማኖቱንም በሙሉ ወደ ፕሮቴስታንትነት ይቀይርና ፣ ታቦት አያስፈልግም ፣ ይውጣ የሚል ትውልድ በንደንብ ከፈጠሩ በኋላ ታቦተ ጽዮንን ከአክሱም በመውሰድ ሦስተኛውን መቅደስ ሠርተው ሲጨርሱ የለ ግርግር ታቦት የሚጠላው ትውልድ በክብር ያስረክባቸዋል ማለት ነው ።
ስለዚህ በቀጣይ በኢትዮጵያ እንዲህ ይሆናል ። በዋነኝነት ማኅበረ ቅዱሳን በውድም ሆነ በግድ እንዲፈርስ ይደረጋል። በአረጋውያኑ ጳጳሳት ምትክ አዳዲስ የተሃድሶ አራማጅ የሆኑ ወጣት ጳጳሳት ቦታውን እንዲይዙ ይደረጋል ። የሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲፈርሱና በፕሮቴስታንታዊ ቅኝት በተቃኙ የተሃድሶ ሰራዊት ይተካል ።
የካህናትን ክብር የሚያጎድፉና ካህናት እንዲጠሉ የሚያደርግ በአደባባይ የሚሰክር ፣ የሚጠጣ ፣ የሚዘርፍ እንግዳ መነኩሴና ካህናት ይፈጠራሉ ።
በዚህ መሃል ግማሹ በአዲሱ እምነት ይማረካል ። ቤተመቅደሱ ላይ የጥፋት ርኩሰት ይቆማል ። ይህንን ጉድ የሚጋፈጡ ጥቂቶች ፣ ይታሰራሉ ፣ ይገደላሉ ፣ ይሰደዳሉ ። አንዱ ሌላውን እንዳይረዳው እንኳ አስቀድሞ በግልፅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጎሪጥ እንዲተያይና እንዳይተማመን በመረረ የዘር ጥላቻ እንዲዋጥ ተደርጓልና ማንም ማንንም አይረዳም።
በአሩሲ አኖሌ በፈጠራ ታሪክ የአያቶችሁን ጡት የቆረጠው ይሄውልህ ተብሎ ያደገው ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ ለበቀል ከመሮጥ በቀር ሌላ የሚያቆመው ያለ አይመስልም ። ለረጅም ዘመናት በአንድነት ኢትዮጵያን የገነቡት ጎንደሬ ኢትዮጵያውያንና የትግራይ ኢትዮጵያውያን በግድ ጥላቻን እየተጋቱ እንዲያድጉ ስለተደረጉና አሁን ደግሞ ይበልጥ ዙሩን እያከረሩት በመምጣታቸው አያድርስና በትግራይ አንድ ችግር ቢፈጠር ፣ ደግሞም በጎንደር አንድችግር ቢፈጠር ለመረዳዳት የሚደረግ ነገር እንደ ቀድሞው ፈጣን አይመስለኝም ። ይሕ ሁሉ ሲሆን የፕላኑ አውጪዎች ግን ቁጭ ብለው ይሳቃሉ ። እዚህ ጀርመን ከህዝቡ መሃል ሃይማኖት አልባው ይበዛል ። ፓስተሮቹ ግን ህዝባቸውን ሃይማኖት አልባ አድርገው እነሱ ሻንጣቸውን ጠቅልለው ከእነ ፓስተር ዳዊት ጋር ለመሥራት ኢትዮጵያ ከትመዋል ።
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ሃብታም ለመሆን ከፈለግክ ፕሮቴስታንት መሆን ብቻ ነው የሚጠበቅብህ ። ሥራ የለም ግን ሀብት አላቸው ። ንግድ ቀዝቅዟል ፕሮዎቹ ግን የናጠጠ ኑሮ ይኖራሉ ። የእኛዎቹ እነ በጋሻውና ያሬድ አደመን እንኳ ተመልከቱልኝ ፣ የ53 ሚልየን ብር ፋብሪካ በአንድ ጀንበር ከፍት. አድረዋል ። ተሃድሶና ጴንጤ ከሆንክ የሚገጥምህ እጣ ይኽ. ነው ።
ወዳጆቼ መፍትሄ ግን አለው ።
መፍትሄውም በመጀመሪያ ልባችንን ክፍት አድርገን በዙሪያችን ምን እየተካሄደ እንደሆነ ማየት ይገባናል ። ከዚያም ለፍቅርና ለእርቅ እንዘጋጅ ። ውይይቱን በቤተሰብ እንጀምር ።
አሁን በተፈጠረው ነገር አኩርፋችሁ ከቤት እንዳትቀሩ አደራ ፣ እናንተ ከቀራችሁ ፤ ቤተክርስቲያኑን ባዶውን ስለሚያገኙት ይወርሱናልና በምንም ተአምር እንዳትቀሩ ። አደራ ከቤተክርስቲያን እንዳትቀሩ ። በምንም መልኩ ቢሆን ድንጋይ መወርወር ፣ ጮክ ብሎ መሳደብ የተዋሕዶ ልጆች መገለጫ አይደለምና እንዳታደርጉት ተጠንቀቁ ። ዝም ብሎ እውነትን ይዞ መሟገት ብቻውን በቂ ነው ። አሸናፊም ያደርገናል ። ከሁሉ አስቀድመን ግን ሁላችንም ንስሐ እንግባ ፣ ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት እንቅረብ ። እንወያይ እንደማመጥ ፣ እንከባበር ፣ እንዋደድ ።
ከመካከላችን አንድ ሙሴ እንምረጥ ። ወይም መርጦ እንዲሰጠን ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ ፣ ሱባኤ እንግባ ፣ አባቶቻችንም እኛም በድለንሃል ብለን እናልቅስ ። አይናችን እያየ በታሪክ እርስ በእርስ በሃይማኖት ምክንያት አደጋ ላይ ከመውደቃችን በፊት እንምከር ፣ እንመካከር ።
እንደ አርቲስት ቴዲ አፍሮ አይነቱን ህዝቡን በኢትዮጵያዊነት የፍቅር ገመድ አስተሳስሮ አንድነትን የሚሰብክ የፍቅር ሰዎችን ያብዛልን ።
በእኔ በኩል የትግራይ ልጆችን አደጋው ከባድ እንደሆነ ለማስረዳት ብዙ ደክሜያለሁ ፣ ቀላል የማይባሉ የትግራይ ልጆችም ይህንን ተንኮል የምትሠራው ህውሓት ናት የሚል ሃሳቤን በማቅረቤ ምክንያት በብዙዎች ዘንድ የትግራይን ህዝብ እንደምጠላ ተደርጌ ፕሮፓጋንዳ ስለተሠራብኝ ሊሰሙኝ እየፈለጉ ነገር ግን ዘረኛ እየመሰልኳቸው ጆሮ ዳባ ልበስ ሲሉኝ ቆይተዋል ። እኔም ድርቅ ብዬ ህዝብና ፓርቲ አንድ አይደለም ። እናም እባካችሁ ግድየላችሁም ብዬ ተጨቃጭቄ ዛሬ ላይ ቁጥሩ ቀላል የማይባል የትግራይ ልጆች ከጎኔ ቆመዋል ። መረጃዎች በሰነድ የተደገፉ ወደ እኔ በመጉረፍ ላይ ናቸው ።
አሁንም የትግራይ ልጆች ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ከልባችሁ ስሙኝ አድምጡኝም ። ከአነጋገሬ ስህተት ሳትረዱኝ ቀርታችሁ የተቀየማችሁኝ ካላችሁ ፤ እንዲያው በተሰቀለው መድኃኒዓለም ፣ በታቦተ ጽዮን ፣ በአክሱሟ ማርያም ፣ በጻድቁ አቡነ አረጋዊ ፣በአብርሃወአጽብሃ ይዣችኋለሁ ፣ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም እግራችሁ ስር ተደፍቼ እለምናችኋለሁ ። አጥፍቼ ከሆነ ማሩኝ ፣ ይቅርም በሉኝ ።
ፖለቲካ ሃላፊ ነው ። ፖለቲከኞችም እንዲሁ ። የማታልፍ እና ጌታ እስኪመጣ የምትቆየው ሀገር ናት ። እባካችሁ እባካችሁ ተለመኑኝ ፣ ኢትዮጵያን ታደጓት ።
ስለ እኔ ኢትዮጵያዊነት ለማወቅ ከሀገር እስክወጣ ድረስ በአክሱም ከተማ ውስጥ ከመንግሥት ተረክቤ አስተምራቸው የነበሩትን የአክሱም የድሃ ልጆች ቤተሰቦችና የከተማውን ከንቲባ ጽ/ቤት ጠይቁ ። ደብረ ዳሞ ሂዱና ፣ አቡነ መድኃኒነ እግዚም ሂዱና ፣ አብርሃ ወአጽብሃ ፣ ገርአልታ አቡነ ይምአታ ፣ ማኅበረ ዶጌና ራሷ አክሱም ጽዮን ሄዳችሁ ዘመድኩን ማነው ብላችሁ ጠይቁ ። በሊቢያ የተሰውትን ሰማዕታት ቤተሰቦች ኢንቲጮና ገዛ ገረሥላሴ ሄዳችሁ ስለ እኔ ጠይቁ ። ይነግሯችኋል ።
እኔ አሁን ብዙም የደኅንነት ስሜት አይሰማኝም ሆኖም ግን ሌላ አማራጭ ስለሌለኝ የማይቀረው ነገር እስኪመጣ ድረስ እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ የቻልኩትን ያህል ለመታገል እሞክራለሁ ። እይታዎቼንም ወደ እናንተ አቅም በፈቀደ መጠን ለማድረስ እሞክራለሁ ።
በስልኬ ላይ ስለምጽፍ እንጂ በቻልኩት መጠን ቶሎ ቶሎ በመጻፍ ወደ እናንተ ባደርስ ምንኛ በወደድኩ ነበር ። ለመድረስ እሞክራለሁ ። የሚፈጠረው አይታወቅምና ድንገት የማያምር ነገር መጥፎ የሆነም ዜና በእኔ ላይ ቢፈጠርና ብትሰሙ የለጆቼን ነገር.! አደራ.! አደራ.! አደራ.! አደራ በሰማይ አደራ በምድርም አደራ ። የእናንተ ልጆች ናቸው ። አሳድጉልኝ ፣ አስተምሩልኝ ፣ ለቁምነገር አብቁልኝ ። አሁን እየደረሱኝ ያሉት ዛቻዎች ደስ አይሉም ። ነገር አንድ ጊዜ የነብሩን ጭራ ይዧለሁና መልቀቅ ብሎ ነገር አይታሰብም እዚህ ጀርመን ድረስ እዚሁ ሆነው የተቆጡብኝ ስላሉ ምንም። ምንም አይነት ነገር በእኔ ህይወት ላይ ቢፈጠር አደራ ሃይማኖታችሁን ከመጠበቅ ወደ ኋላ እንዳትሉ ። ታቦተ ጽዮንም በእኔና በእናንተ ዘመን እንዳትነጠቅ ። ቅዥት ቢመስልም ግን እውነታው ይሄው ን. ።
በቀጣይ ጽሑፌ በእስከ አሁኑ ሂደታችን ተሸንፈናል ወይስ አሸንፈናል የሚለውን ለማየት እንሞክራለን ።
የኢትዮጵያ ቡናና ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በሚያሰሟት የጋራ ዜማቸው እንሰነባበት ።
አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
 አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
 አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
 አሆሆ አሃሃ መሸነፍ የለም.!
እንኳንም ተሰደድኩ ፣ እንኳንም አስጨንቀው ከሀገሬ አስቀሩኝ ። ስለእውነት እንነጋገር ከተባለ አሁን እንደምፈነጨው በሀገሬ ብሆን እፈነጭ ነበርን? ። መንፈራገጤ አይቀርም ነበር ። ነገር ግን ኮማንድ ፖስቱ ዋጋዬን ሰጥቶ አደብ ያስገዛኝ ነበር ። ወይ አንቀጽ ጠቅሶ ሸዋሮቢት ፣ ወይ ደግሞ አከናንቦ ሰማይ ቤት ይልከኝ ነበር ። አሁን ግን ለጊዜው ሰላም ወረዳ ነው ያለሁት ፤ እናንተ መረጃዎችን ላኩልኝ እኔ እንደሚሆን እንደሚሆን አደርገዋለሁ። እስከ ጊዜው ድረስ ።
" እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
አንቺ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሆይ.! ጌታ በደሙ የመሰረተሽ ነሽና ደሙ ይፍረድልሽ ። አከተመ በቃ.!
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ፌስ ቡክ What's on your mind? ስላለኝ ይህንንም ራሴው ከአእምሮዬ አቅንቼ በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 11/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

ከብፁዓን አባቶቻችን ለእምዬ ተዋሕዶ ልጆች የተላከ የደስታ መልእክት


★ ★ ★ ★ ★
✔Share ~ Share ~Share በማድረግ ይኅንን መልእክት ላልሰማ አሰሙ ። ላልደረስው አዳርሱ ። ✔ Comment ~ Comment ~ Coment በመስጠት ደግሞ አዳዲስ ሃሳብ አፍልቁ ።
✔እባካችሁ አትደውሉልኝ ። መልእክት በቻ ጻፉልኝ ። እረ ልፈነዳ ነው ። ተባበሩኝ ጓደኞቼ.!!
✔በመሃል እየገቡ ያልሆነ የብስጭትና ከርእሳችን ውጪ አጀንዳውን ለመጠምዘዝ የሚሞክሩትን እንደበፊቱ አልታገሳቸውም ። መብቱ በእጄ ስለሆነ ይህን ከመሰለ ጮማ የሆነ ጦማት ከሚኮመኩሙበት ገበታ አስወግዳቸዋለሁ ። እመ አምላክ ምስክሬ ናት ።
✔ አሁን እኛ ስለ ራሳችን የምንመካከርበት ግዜ እንጂ የእነሱን ቅርሻት የምንጠርግበትና እሱንም ለማጽዳት ጊዜ የምናጠፋበት ወቅት ላይ አይደለንም ። አራት ነጥብ ። እስቲ ወንድ የሆንክ አሁን እኔ ፔጅ ላይ አፍህን ክፈት ። አሳይሃለሁ ። Block በተባለ ሰይፍ ነው ቆርጬ ከፔጄ ላይ የማስወግድህ ። ሰምተሃል.!
✔ትግላችሁ እንዳይቆም.! በፍፁም ኦርቶዶክሳዊ ጨዋነትና ጥበብ አጠናክራችሁ ቀጥሉ ተብላችኋል ።
✔ ብረትን መቀጥቀጥ እንደጋለ ነውም ብለዋል ። እናም የእምዬ ልጆች ዝግጁ ናችሁ. !???
የተከበራችህ ውድ የእምዬ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ ። የቅድስት የቤተክርስቲያናችንም ሆነ የኢትዮጵያ ሀገራችን ትንሳኤ የቀረበ መስሎ ይሰማኛል ። ደግሞም እንደዚያም ነው ።
በሰሞኑ በእኔና በእናንተ የተቀናጀ እና ውጤታማ ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ ትግል የተነሳ አስደናቂ እና የሚያኮራ ተግባር መፈጸማችን ይታወቃል ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ እንዲህ አይነት የሚያስደንቅ ፣ የሚያኮራ ፣ እንባና ሲቃ ፣ እልህና ቁጭት ተፈጥሮ በያገባኛል ባዮችና ፣ መብቴነው በሚሉ የተዋህዶ ልጆች አስደማሚ ተሳትፎ ምክንያት ታሪካዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ወርቃማ ገድል ፈጽመናል ።
በዘህ እንቅስቃሴ መንግሥት ደንግጧል ፣ መናፍቃን ተበሳጭተዋል ። ሌላው ቢቀር የጀርመን ዜግነት ያላቸው ነጭ ጸሐፊዎች እንኳን " የዘመድኩን ውሸት " በማለት በአካል ባያውቁኝም በስማበለው በሰሙት መጥፎና ወሽመጥ ቆራጭ ዜና አማካኝነት ተናደው አርቲክል አዘጋጅተው ለንባብ አብቅተዋል ። ከመናፍቃኑ ወገን አባ ኃይለማርያም እና አባ ተክለሃይማኖት እንዲሾሙ ፕሮቴስታንቶችና ፓስተሮች ሳይቀሩ የፆም አዋጅ እስከማወጅ ደርሰዋል ። ለጊዜውም ቢሆን አባ ኃይለማሪያ በሴራና በተንኮል ። አባ ተክለሃይማኖት በጠመንጃ አፈሙዝ በግልጽ መሾማቸው በተሰማ ጊዜ በእኛ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ የድንጋጤ ፣ የተስፋ መቁረጥ ፣ የሀዘን ፣ የመከዳት ፣ የመሸጥ ፣ ስሜት ሲያድርብን ፣ በአንጻሩ ደግሞ በተሃድሶዎቹና በመናፍቃኑ ዘንድ ስሜታቸውን መቆጣጣጠር አቅቷቸው በድስታ የዓለም ዋንጫ እንደበላ ሀገር ሲፈነጥዙ ታይተዋል ።
ለማንኛውም ይህ የመናፍቃኑ ደስታ እና የእኛም ሀዘን ብዙም አልቆየም ። ወዲያው በድርጊቱ የተበሳጩ የተዋሕዶ ልጆች ለእረፍት ለምሳ ወጥተው የነበሩትን አባቶች በስልክም በአካልም መቆሚያ መቀመጫ በማሳጣት በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አንድ በሐሰትና በቁማር ያውም በጨበጣ የተሾመን ጳጳስ ሹመቱ ይቆይ አስብለናል ። በዚህ ነው ፈረንጆቹ ፣ ተሃድሶዎቹና ፕሮቴስታንቶቹ የተበሳጩት ። እኛ ግን ደስ ቢለንም ገና ትግላችንን አልጨረስንም ። አይደለም እንዴ.??? ዋሸሁ እንዴ.???
አሁን አብዛኛዎቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሁኔታችን ፣ በምእመናን ትብብር ፣ ጫና መፍጠር ፣ በእጅጉ ኮርተዋል ። በተለይ ልጅ እግሮቹ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከሚገባው በላይ ደስተኞች ሆነው ተገኝተዋል ። እናም በዚህ ምክንያት ምእመናን ድርሻቸውን እንዲህ አውቀው ፍፁም በሆነ መንፈሳዊ ስነስርዓት አሁን ካለው በበለጠ ሁናቴ ተጠናክረው ከቀረቡ የማይለወጥ ነገር የለም ብለዋል ።
ትናንት ተሰባስበው መረጃ የሰጡኝና መልእክቱን ለህዝብ አስተላልፍልኝ ያሉት ብፁዓን አባቶች አንተ ዘመዴ አንደበት ስለሆንከን ፣ መተንፈሻችንም ስለሆንክ እጅግ አድርገን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን ብለዋል ።
አሁን ከዚህ ፖስት በመቀጠል በእዚህ ጉባኤ ትልቁን ሴራ በመሥራት ዶር አባ ኃይለማርያምና አባ ተክለሃይማኖት እንዲመረጡ ግፍ የሰሩ በተለይ ሁለት አባቶችን አዳፋሪና አንገት የሚያስደፋ ተግባር ለህዝብ ይፋ አድርገው ብለው ልከውልኛል ። ያበጠው ይፈንዳ ።
እኔም ይሄን እንደመግቢያ አድርጌ የተንኮለኞቹን አባቶች ስምና ፎቶ ፣ መጀመሪያ የእጅ ስልካቸውን እሱን አላነሳ ካሉና ከዘጉ ደግሞ የቢሮና የቤት ስልካቸውን እለጥፈዋለሁ ። አሁን ይህን 2009 ዓመተ ምህረትን ቤታችንን ጽድት አድርገን 2010 ዓመተ ምህረትን ተንኮለኛ ፣ ሴረኛ ፣ ሙሰኛ ፣ ዘማዊ ፣ ፖለቲከኛና ፣ ካድሬ ካህናትና መነኮሳትን መስመር አስይዘን የደስታ ፣ የፍቅር ጉዞ እንጀምራለን ።
ከእንግዲህ ወዲያ መደራደር የለም ፣ እስቲ 60 ሚልዮን የሚገመተውን የእምነቱን ተከታይ የመንግሥት ወታደሮች ሲያስቆሙት እናያለን ።
ይሄ ሌባ ሌባው ወንበዴና ዘራፊ ሆኖ ሳለ በደብር አስተዳዳሪነት ፣ በፀሐፊነት ፣ በገንዘብ ቤት ፣ በቁጥጥጥር ስም ተመራርጠው በየደብሩ የተሰገሰጉ ሌቦችንም መንጥረን እናወጣለን ። አንዳቸውንም አትፍሯቸው ። እያንዳንዳቸውን እናውቃቸዋለን ። ትናንት ከገጠር ሲመጡ ምን ይመስሉ እንደነበሩ እናውቃቸዋለን ፣ ፎሮፎር የወረሰው ጭንቅላት ፣ ወርጭ ያደረቀውና ጭርት ያበላሸው ፊት ፣ የተበጫጨቀ ኮትና ነጠላ ፣ ሙጀሌና የሞላው ባዶ እግር ፣ እንቅፋት የነቀለው ጥፍር ፣ መግል የቋጠረ እግር ፣ እከክ የወረሰው ገላ ይዘው ነው ወደ እኛ የመጡት ። እያንዳንዱን እናውቀዋለን። ከሁሉም ጋር እንተዋወቃለን ። ከሁሉም ጋር ። አዳሜ እከኩን ካራገፈ በኃላማ ፣ ሙጀሌውን ካወጣ በኋላማ አሁን በዘረፈን ገንዘብ ተንደላቅቆ መኖሩ ሳያንስ የክህደት መርዙን አያቀረሽብንም ። በፍፁም ። ቱ ሞተናታላ. ። በእኛ ዘመን ቤተክርስቲያን አትፈርስም ። እንዲህ አይነት ቆሻሻ ታሪክም በዘመናችን አይፈፀምም ።
አሁን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ እንደየ አደገኝነታቸው እና እንደነበራቸው አፍራሽ ሚና ያርፉ እንደሆን እንዲያርፉ ፣ የማያርፉ ከሆነ ግን ቀልድ ስለሌለ እረፍት የሚነሳ ተቃውሞ የምናነሳባቸውን የከዱንና ከመንግሥት የደኅንነት ኃይሎች ጋር እስከ ሌሊቱ 8 ሰዓት በመዶለት በጥርነፋ ገብተው ሌሎቹ በፁዓን አባቶች ላይ ተፅእኖ የፈጠሩ አባቶችን ክፉ ስራ ተራ በተራ ለማየት እንሞክራለን ።
ጎበዝ ጨከን ብለን በድፍረት ካልተነጋገርን ለፀላ ምንም አይነት መፍትሄ እንደሌለን እወቁ ። አማራጭ የለንም ። ቤተክርስቲያን የህእብ ናት ። እናም ለህዝቡ የሚሾሙትን አባቶች መምረጥ ያለበት ህዝቡ እንጂ ኢህአዴግ አይደለም ። ኢህአዴግ ከፈለገ ዶር አባ ኃይለ ማርያምንም ሆነ አባ ተክለሃይማኖትን በለመደው መንገድ ይጠቅሙኛል ብሎ ካመነበት ለፓርላማ አቅርቦ ያወዳድራቸው ። አለቀ ። በቃ ይኸው ነው ። አከተመ።
ምነው ሸዋ.! አለ ሌሊን ። ሆሆይ!
" እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
አንቺ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሆይ.! ጌታ በደሙ የመሰረተሽ ነሽና ደሙ ይፍረድልሽ ። አከተመ በቃ.!
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው ነገር እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ፌስ ቡክ What's on your mind? ስላለኝ ይህንንም ራሴው ከአእምሮዬ አቅንቼ በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 11/2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

አዝማሪ ትዝታው የራሱንና የቤተሰቡን የአንገት ማዕተብ ከበጠሰ ቆየ ።

ግሪሳ ትዝታው ( ሉንጎ )  መቅሰፍት ሊወርድበት  ነው ★ ★ ★ ✔  Share ~ Comment ~ Like ~ Tag ★ አዝማሪ ትዝታው የራሱንና የቤተሰቡን የአንገት ማዕተብ ከበጠሰ ቆየ ። ★በኮሎራዶ.! ...